ሀይለኛ ፍቅር ሲይዘን የምንይዘውን የምንጨብጠውን የማጣት፣ ሰዎች የሚሉንን ያለመስማት ችግር እንደሚያጋጥመን ብዙዎቻችን ደርሶብን አይተነው ይሆናል።
ከማህበረሰቡ ልማድ የማፈንገጥ፣ ሃይማኖታዊ አስተምህሮን የመልቀቅ እና የቤተሰብ ምክርን እስካለመስማት እና አለመቀበል የሚደርስ ተፅዕኖ ያለው ፍቅርም ያጋጥማል።
ለዚህም ነው ፍቅር አይን የለውም የሚባለው፤ ከወደ ፈረንሳይም ይህን አባባል እውን የሚያደርግ ዜና ተሰምቷል።
ሊሊ የተሰኘች የቴክኖሎጂ አፍቃሪ እስከ ህይወቷ ፍፃሜ ከአንድ 3D ሮቦት ጋር አብራ ለመኖር ቀለበት ማሰሯ ነው የተነገረው።
ሊሊ ኢንሞቫተር የሚል ስያሜ የተሰጠውን 3D ሮቦት ራሷ ነች የሰራችው።
ባለፉት አመታትም ከዚሁ ሮቦት ጋር እየኖረች መሆኑን ገልፃለች።
ከልጅነቷ ጀምራ የሮቦቶችን ድምፅ መስማት እንደምትወድ የገለፀችው ሊሊ፥ ከሮቦቱ ጋር ኑሮ መጀመሯ በቤተሰቦቿ እና ጓደኞቿ ተቀባይነት ማግኘቱን አስታውቃለች።
ፈረንሳይ ግኡዝ አካል የሆነውን ሮቦት ማግባትን አትፈቅድም።
በመሆኑም አንድ ቀን ሀገሪቱ ሮቦት ማግባትን ህጋዊ ፈቃድ ስትሰጠው ከኢንሞቫተር ጋር ጋብቻ ለመፈፀም ማቀዷን ነው ሊሊ የተናገረችው።
ምንጭ፦ www.techworm.net/
No comments:
Post a Comment