ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸው መንግስትን ይቅርታ አልጠየቅሁም አለ
ኢሳት (መስከረም 2 ፥ 2009)
የህዝበ ሙስሊሙን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ሲዘግብ በአሸባሪነት ተከሶ በእስር ቤት ላይ የቆየው ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸው መንግስትን ይቅርታ አለመጠየቁን ገለጸ።
ጋዜጠኛ ዩሱፍ ሙያውን ሽፋን በማድረግ ህዝብን ለአመጽ በማነሳሳት በሚል ክስ 7 አመት ተፈርዶበት በእስር ቤት አመታትን አስቆጥሯል።
ከ4 አመታት በላይ በእስር የቆየው ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸው በመክሮ ሊፈታ ወራት ሲቀሩት ከአዲሱ ዓመት ጋር በተየያዘ በምህረት በሚል ከተለቀቁት መካከል ነው።
ወደፊት ስራውን እንደሚቀጥልና መንግስት ዜጎችን በማፈን ሃሳባቸውን እንዳይገልጹ የሚያደርገውን ተፅዕኖ እንዲያቆምም ጥሪ አቅርቧል

No comments:
Post a Comment