Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, September 1, 2016

በብዙ የጎጃምና የጎንደር አካባቢዎች መንግሥት ፈርሷል፤ የጎበዝ አለቆች ክፍተቱን እየሞሉ ነው

በብዙ የጎጃምና የጎንደር አካባቢዎች መንግሥት ፈርሷል፤ የጎበዝ አለቆች ክፍተቱን እየሞሉ ነው
• ባሕር ዳር፣ መራዊና ዳንግላ ከተሞች በጪስ ታፍነው ተኩስ ሲናጡ ውለዋል Muluken Tesfaw
• ‹‹በአዴት ከተወለዱ በጤና እያለ አንድስ እንኳ እቤት የዋለ የለም›› የአዴት ሪፖርታዥ
• ከወረታ ከተማ አቅራቢያ ጉማራ ላይ በገበሬውና በትግረው መከላከያ መካከል ከባድ ጦርነት ሲደርግ አድሯል
• ቋሪት፣ አገው ምድር፣ ጋይንት፣ በለሳ፣ አብዛኛው የደበርቅና የጃናሞራ አካባቢዎች ከመንግሥት ቁጥጥር ውጭ ናቸው
• በአንዳቤትና በፋርጣ የጎበዝ አለቆች አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል
ባሕር ዳር፤ በባሕር ዳር ከተማ በሕዝብ የተጠረውን የቤት ውስጥ አድማ ለማደናቀፍ በሞከሩ የወያኔ አባላትና ቅጥረኛ ባንዳዎች ንብረት ላይ ዐማራው እርምጃ እየወሰደ ነው፡፡ የዐማራው ሕዝብ ቆራጥነቱን በተግባር ያሳየበት ከዛሬ የበለጠ ቀን አልነበረም፡፡ ጠዋት አካባቢ አድማውን ችላ በማለት ሥራ የጀመረ አንድ የከተማ አውቶቡስ ሾፌር መኪናውን ሰባብረው ልጁን እንዲማር መጠነኛ አካላዊ ጉዳት ደርሶበት አሰናበቱት፡፡ ሥራ የጀመረው የንግድ ባንክም ሕንጻ መስኮቶች ተሰባብረዋል፡፡ በሕዝብ አስቀድመው የተለዩ የሕወሓት አባላት እና የዐማራ ቅጥረኛ ባንዳ ሰዎች ስም ዝርዝር አስቀድሞ የተሰራ ሲሆን ተራ በተራ ሲቃጠል ውሏል፡፡ ባሕር ዳር አሁን ከዝናቡ ጋር በጭስ ታፍናለች፡፡ ከቦታው አስተያየቱን እንዲሰጠን የጠየቅነው የከተማዋ ነዋሪ ‹‹የጥይት ሩምታው ይሰማሃል? የቤት ጣራ ላይ ሆኜ ነው የማወራህ አንድ ሁለት… ወደ ዘጠኝ ቤት ሲቃጠል ይታየኛል እኛ ሰፈር እንኳ፡፡ የአምቡላንስና የጥይት ድምጽ እየረበሸኝ ነው›› ሲል የነበረበትን ሁኔታ ገልጦልናል፡፡ ቀበሌ 08 የሚባለው ሰፈር በርካታ ቤቶች የተቃጠሉበት ነው ተብሏል፡፡
በባሕር ዳር በዛሬው የዐማራ ተጋድሎ ቀበሌ 06 ሦስት ዐማሮች ተሰውተዋል፡፡ ቀበሌ 14 ኤፍራታ እሚባለው አካባቢ ደግሞ ለታጋይ ዐማሮች ውሃና ምግብ ለማቅረብ ሲሄዱ የነበሩ እናት ወድቀው መሰዋታቸውን ሰምተናል፡፡ በርካታ ተሸከርካሪዎች የተቃጠሉ ሲሆን ዐማራው በየሰፈሩ የጎበዝ አለቃዎችን እየመረጠ በመታገል ላይ መሆኑን ሰምተናል፡፡ ያልተዘጋ መንገድ የለም፡፡ የዐማራ ፖሊስ ሕዝብን በመጠበቅ ያደረገው ተጋድሎ የሚደነቅ መሆኑን ሰምተናል፡፡ በባሕር ዳር ዛሬ የተደረገው ተጋድሎ እጅግ የሚያኮራና ከተማዋን ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ሕዝቡ የተቆጣጠረበት ሁኔታ እንዳለ ሰምተናል፡፡ የባሕር ዳር ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች በግቢ የዐማራን ተጋድሎ ሲያንጸባርቁ ውለዋል፡፡
ከባሕር ዳር ከተማ 17 ኪሎ ሜትር አካባቢ ያለችው የመሸንቲ ከተማና የይባብ ኢየሱስ ቀበሌም የዐማራ ተጋድሎ ከዋለባቸው ቦታዎች ውስጥ ናቸው፡፡ መሸንቲ ያለው የሕወሓት አባል የድንጋይ ጠጠር ማምረቻ ፕላንትም ተቃጥሏል ተብለናል፡፡
መራዊ፤ በመራዊ ከተማ የዐማራ ሕዝብ ለተጋድሎ የወጣው በጠዋት ነበር፡፡ የሜጫዋ መራዊ ከተማ እንደ ባሕር ዳር ሁሉ በጢስ ታፍና ውላለች፡፡ ለተጋድሎ የወጣው የዐማራ ሕዝብ ከጉያው ተሸጉጠው ሲያንገላቱት የነበሩትን የሕወሓት አባላትና ቅጥረኛ ባንዳዎች ሀብትና ንብረት ተለቅሞ ተቃጥሏል፡፡ የገብረ ሥላሴ ኃይለማርያም ክሊኒክና ፋርማሲ፣ የገ/ድህን ክሊኒክ፣ ፒታ ዳቦ ቤት፣ ኃይሌ ፎቅ፣ የኢትዮጵያ እህል ንግድ ድርጅት፣ ብአዴን ጽ/ቤትና በርካታ የሰላዮች መኖሪያ ቤትና ንብረት ወድሟል፡፡ የዐማራ ሕዝብ ከተማዋን ይህ ሪፖርት እስከተሠራበት ጊዜ ድረስ ተቆጣጥሯት ይገኝ እንደነበር ለማወቅ ችለናል፡፡
አዴት፤ የይልማና ዴንሳዋ አዴት ከተማ በዐማራ ተጋድሎ ስትናጥ ውላለች፡፡ ከአዴት ከተማ የሚገኘው ሪፖርተራችን የላከልን መረጃ እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡ የአዴት ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ወያኔን ሲቃወም ዋለ፡፡ በአዴት ከተወለዱ በጤና እያለ አንድስ እንኳ እቤት የዋለ የለም፡፡ ከወጣት እስከ ሽማግሌ፣ ሴትና ወንድ፣ እስላምና ክርስቲያን ሁሉ በቁጣ ገንፍሎ ወጥቷል፡፡ ሰልፉን የሰሙ የይልማና ዴንሳ አርሶ አደሮችም ከወንዳጣ ድረስ እየመጡ በወኔ ተጋድሎውን ተቀላቅለው ውለዋል፡፡
‹‹ወያኔ ሕወሓት ሌባ ነው፤ ቅጥረኛው ብአዴን አይወክለንም፤ ድንበራችን ተከዜ ነው፤ ወልቃይት ዐማራ ነው፤ በዐማራ ላይ የሚደርሰው ጭቆና ይቁም፤ የሃይማኖት ጣልቃ ገብነት ይቁም፤ …›› እና ሌሎችም መፈክሮች ሲሰሙ ውለዋል፡፡ የዐማራው ሕዝብ ወደ ባሕር ዳር በኩል 2 ኪሎ ሜትር መንገድ በመጓዝ አቦላ ተራራ አካባቢ ያለውን መንገድ መዝጋት ቅድሚያ የሠጠው መርሃ ግብር ነበር፤ ይህም የወያኔን አልሞ ተኳሾች እንዳይመጡ መንገዱን ማበላሸት ሲሆን ይህን የሰሙት የባሕር ዳር አናብስት ወጣቶች ሰባታሚት አካባቢ መንገዱን ጠርቅመው በመዝጋት የአዴት ዐማሮችን ተባብረዋል፡፡ ሰልፈኞች ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩ ወጣቶችን ሰብረው በመግባት አስፈትተዋል፤ የአስተዳደር ቢሮው ተሰባብሯል፡፡ የገንዘብና ኢኮኖሚ ጽ/ቤት ኮምፕዩተሮች በእሳት ጋይተዋል፡፡ አካለ መንግሥቱ የሚባለው የወያኔ ቅጠረኛ ዐማሮችን ሲሰልልና ሲያሰቃይ የሰነበተ ሲሆን የሕንጻ መሣሪያ መደብሩ ወድሞበታል፡፡
ክሊኒክና ፋርማሲ በመክፈት የአዴት ዐማራን ጊዜው ባለፈበት መድኃኒት ሲበዘብዙና ሲሰልሉ የነበሩት የገ/እግዚአብሔር ቤተሰቦች ከሳምንታት ቀደም ብለው ከአዴት ቢወጡም ንብረታቸውና መኖሪያ ቤታቸው በእሳት ከመጋየት አልዳነም፡፡ የገ/እግዚአብሔር ልጅ የሆነው አቶ አማኑኤል ዐማሮችን በሽጉጥ ሲያስፈራራ የሰነበተ ሲሆን ዛሬ ተፈልጎ የገባበት ሳይታወቅ ቀርቷል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ የወያኔ ቀኝ እጅ የሆኑት የሃይማኖት አባቶች ሰልፉን ለመገላገል ቢገቡም እናንተን አንሰማም ብሎ አሳፍሮ መልሷቸዋል፡፡ ይልማና ዴንሳ በህዝብ ቁጥጥር ስር ውላለች፡፡ ለዘጋቢያችን ምስጋና ይድረሰው፡፡
ዳንግላ፤ የአገው ምድሯ ዳንግላ ከተማ የዐማራን ተጋድሎ የተቀላቀለችው ትናንት ነበር፡፡ ትናንት ነሃሴ 22 ቀን 2008 ዓ.ም. ከጠዋቱ 1፡00 ጀምሮ የዳንግላ አገው ዐማራ ሕዝብ ለተጋድሎ ወጣ፡፡ የዐማራውን ጥያቄዎች አንግቦ ወደ ወኅኒ ቤቱ አቅጣጫ ሲሄድ መዘጋጃ ቤት አካባቢ ሲደርስ የወያኔ አባል የሆነው የመዘጋጃ ቤት ሠራተኛ አቶ ሀብተወልድ ወደ ሕዝብ በመተኮስ ሁለት ሰዎችን አቆሰለ፡፡ ሕዝብ ተቆጣና የአቶ ሀብተወልድን ቤት ሙሉ በሙሉ አቃጠለው፡፡
ወደ መሃል ከተማ ሲመጣ አንድ ቅጥረኛ የሆነ ያረጋል የሚባል ፖሊስ የዳሸን ቢራ ማስታወቂያን ከሚቀዱት የአገው ዐማራ ወጣቶች ላይ ጥይት አርከፈከፈ፡፡ ፖሊሱ የቤቱን አጥር ጉድብ ይዞ ሁለት ሰዎችን ገደለ፡፡ ከሕዝብ ጋር በሚያደርገው ትንቅንቅ ጥይት ጨረሰ፡፡ ሕዝቡ ሊይዘው ሲል ጎረቤቱ አንድ ካዝና ጥይት ሲሰጠው አናብስቶቹ አዩት፡፡ ባንዳው ጎረቤቱ ተጨፍጭፎ ተገደለ፡፡ ፖሊሱ ቢያመልጥም ቤቱ ከመቃጠል አላመለጠም፡፡ ይህ ሙሰኛ ፖሊስ መኖሪያ ቤት ውስጥ 50 ኩንታል ስኳርና 20 ጀሪካ ዘይት ተደብቆ ተገኘ፡፡ ሁሉም ንብረት አብሮ እንዲወድም ተደረገ፡፡ መኪናም ነበረችው፤ ወደመች፡፡
ዳንግላዎች ወደ ቤታቸው ገቡ፡፡ ነሃሴ 23 ቀን ጠባ፡፡ ዳግም ለተጋድሎ ተሰለፉ፡፡ ከዚያም ዳንግላ ከተማ ከክረምት ጉም እኩል የእሳት ጭስ አፈናት፡፡ የህወሓት አባላትና የቅጥረኛ ባለሥልጣናት ቤት ሙሉ በሙሉ ወደመ፡፡ ከተማዋም በሕዝብ ቁጥጥር ሥር ሆነች፡፡ የከንቲቫው (አቶ ሙላት እሸቴ) በሙስና የተከማቹ ሦስት ቤቶች፣ የጥቃቅን ኃላፊው አቶ ያለው ዘለቀ፣ የብአዴን ኃላፊው አቶ ዳዊት ብርሃኑ፣ የማዘጋጃ ኃላፊው አቶ መንግሥቴ ቢተው፣ የትራፊክ ፖሊሱ አቶ አይተነው፣ የደኅንነቱ አቶ ይመኑ፣ እና ሌሎችም ዛሬ ወደ አመድነት ከተለወጡ በቶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
የአጋዚና የፌደራል ፖሊስ አባላት ከተማዋን ቢወሯትም ሕዝብን ግን እስካሁን ማሸነፍ አልተቻለም፡፡
በባህር ዳር የቤት ውስጥ የመቀመጥ ኣድማ ወደ ተቃውሞ ሰልፍ ተለውጦ ሕዝቡ አደባባይ ወጥቷል። በዛሬው እለት በአዊ ዞን አንከሻ ጔጉሳ ወረዳ ግምጃቤት ማርያም ከተማ ከባድ የሆነ ሰልፍ ለሁለተኛ ቀን ነበረ። መፈክሩም፡ 1- ለወያኔ አንተዳደርም ወይም አንገዛም 2- ወያኔ ሌባ ነው በማለት 3- ወያኔ ከግምጃቤት ማርያም የወሰደውን ስልካችንን ይመልስ በማለት 4 - ወልቃይት የጎንደር ናት 5 - ወልቃይት የአማራ ናት 6 -ወያኔ በንፁሐን ዜጎች ላይ የሚያደርገውን ግድያ እና አፈና ይቁም 7 - የአዊን መሬት 25 አመት በአላሙዲ ስም ነግዶባታል ተንግዲህ ግን የአዊን ህዝብ አፈናቅሎ ላባረራቸው ይመልስ፡። በማለት አሰምተዋል የወያኔ የአዊ ምክር ቤት በደንጋይ ተወግሯል። ወደ ፓሊስ ጣቢያዎች ህዝቡ ደንጋይን ወርውረዋል ህዝቡ በግምጃቤት ማርያም አደባባይ ላይ ከመሀል ኮከብ አርማ የሌለውን ሰንደቅ አላማ ሰቅለዋል ።
ዱርቤቴ፤ የዱርቤቴ እና የሰሜን አቸፈር ወረዳዋ ይስማላ ከተማዎች በዐማራ ተጋድሎ ሲናጡ ውለዋል፡፡ የአቸፈር ገበሬዎች የይስማላ ከተማን መቆጣጠራቸው የታወቀ ሲሆን በዱርቤቴ ደግሞ የጎበዝ አለቃዎች ምርጫ ተካሒዷል፡፡ ዝርዝር መረጃዎችን በኔትወርክ ምክንያት ማቅረብ አልቻልንም፡፡
እንጅባራ፤ በእንጅራባራ ከተማ ትናንት ነሃሴ 22 ቀን 2008 ዓ.ም. በተካሔደው የዐማራ ተጋድሎ ከመቶ ሺህ በላይ ሕዝብ ወጥቷል፡፡ የሕዝቡን ብዛት ሲገልጹ በባሕር ዳር፣ በጃግኒና በአዲስ አበባ መውጫ መንገዶች እስከ ሦስት ኪሎ ሜትር ድረስ የሚረዝም የሰው ጎርፍ ነበር ብለዋል መረጃዎቻችን፡፡ ወልቃት ዐማራ ነው፤ የታሠሩ ኮሚቴዎቻችን ይፈቱ፤ ዐማራነት ወንጀል አይደለም፤ የሚሉና ሌሎችም መፈክሮች ተሰምተዋል፡፡
በእንጅባራ በዞኑ ጸጥታ ዘርፍ የሚሠራ አንድ ታፈረ የሚባል አገው ዐማሮችን በማሰቃየት የታወቀ ቅጥረኛ በሕግ አምላክ እየተባለ አንድ ሰው ገደለ፡፡ ከዚያ የትግሬ አጋዚ ሠራዊት ደርሶ ሌሎች 5 አገው ዐማሮችን የገደለ ሲሆን 19 ሰዎችን ደግሞ አቁስሏል፡፡ ሕዝቡ በንዴት እና በደም ፍላት አቶ ታፈረ የተባለውን ባንዳ ሊገድል ቢሞክርም በማምለጡ ልጁ ተገድሏል፡፡ ሕዝብ በንዴት ወደ ቤት ሳይገባ በውጭ አድሯል፡፡
የእንጅባራ የዐማራ ተጋድሎ ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን በርካታ የሕወሓት አባላትና የቅጥር ባንዳዎች መኖሪያ ቤቶችና ንብረቶች ተቃጥለዋል፡፡ እንጅባራም በጭስ ታፍነው ከዋሉ ከተሞች አንደኛ ሆናለች፡፡ የአገዚ ጦር ዛሬ ሌሎች 6 ወንድሞቻችን በሞት ነጥቆናል፡፡ የአባቶቻችን ሰንደቅ ዓላማ ዛሬም እየተውለበለበ ሲሆን የእንጅባራ ከተማ አሁንም በሕዝብ ቁጥጥር ሥር ነው፡፡ በርካታ መኪናዎች እየተቃጠሉ ነው፡፡
የተጋድሎው መቀጠል አለመቀጠል በተመከተ ለአንድ የእንጅባራ ነዋሪ ላቀረብንላቸው ጥያቄ ‹‹ገና ገና ገና ይቀጥላል!›› ሲሉ በሙሉ ልብና በእርግጠኛነት ተናግረዋል፡፡ እኚሁ አስተያየት ሰጪ እንደሚሉት ‹‹የዐማራ ጥያቄ ሳይመልስ መቼም ቢሆን እኛ አናቆምም፤ መንግሥቱን አፍርሰነዋል፤ ቀጣይ ሥራችንም የጎበዝ አለቆችን መምረጥ ነው፤ ወቅቱ የአዝመራ ጊዜ ቢሆንም ገበሬው ከነጻነት በኃላ ይደርሳል እያለ እየተቀላቀለን ነው›› ሲሉ አክለው ገልጸዋል፡፡
ስማዳ፤ የስማዳዋ ወገዳ ከተማ ዐማሮች ዛሬ በጠዋት ነበር ተጋድሏቸውን የጀመሩት፡፡ ዛሬ ሦስት አካበቢ የተጀመረው የዐማራ ተጋድሎ የዐማራውን ሕዝብ ጥያቄ ሲያስጋባ ከዋለ በኋላ የአባቶቻችን ሰንደቅ ዓላማ በክብር ተውለብልባለች፡፡ በወረዳው የወያኔ ቅጥረኛ የሆነ አንድ ፖሊስ ሦስት ያክል ሰዎችን ገድሎ ከዐሥር በላይ ደግሞ ማቁሰሉን ከቦታው አረጋግጠናል፡፡ ዛሬ በስማዳ የተሰው ዐማሮች ጠቅላላ አምስት ደርሷል፡፡ የአስተዳደር ቢሮ ተሰብሮ ቅጥረኛው ኃላፊ ከከተማዋ ተሰውሯል፡፡ ማንኛውም ዓይነት እንቅስቃሴ የቆመ ሲሆን በአቅራቢያ ባሉ የሙጃና የሦስቻም የገጠር ቀበሌዎችም ላይ ተጋድሎ እንደነበር ለማወቅ ችለናል፡፡
ጃግኒ/ መተከል፤ ዛሬ በጃግኒና በመተከል ባሉ ከተማዎች የዐማራ ተጋድሎ ቀጥሎ የዋለ ቢሆንም በስልክ ችግር የተሟላ መረጃ ማቅረብ አልቻልንም፡፡
አንዳቤት/ጃራ ገዶ፤ የአንዳቤት ዐማሮች ዛሬ ሳይነጋ ሌሊት ዘጠኝ ሰአት ነበር የዐማራውን ተጋድሎ የጀመሩት፡፡ የጃራ ገዶ ከተማ ከወልሽ ከተማ 10 ኪሎ ሜትር የምትርቅ ሲሆን በሌሊት የወጣው ዐማራ አንዳቤት ወረዳን ድብልቅልቅ አድርጓት ውሏል፡፡ የወልሽ ከተማ ነዋሪዎች ወደ ጃራ ገዶ በመሄድ የጃራ ገዶ ደግሞ ወደ ወለሽ በመምጣት አዳማ የሚባለው አካባቢ ተገናኝተዋል፡፡ የአንዳቤት ዐማሮች የጎበዝ አለቆችን እየመረጡ ሲሆን ቀጣይ ቀናት ወረዳው ሙሉ በሙሉ በሕዝብ ቁጥጥር ሥር ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በአንዳቤት 5 ዐማሮች በቅጥረኛ ታጣቂዎች የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ቢሆንም የሰው ሕይወት አለመጥፋቱን ሰምተናል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ የእስቴዋ መካነየሱስ ከተማ በቤት ውስጥ አድማ መመታቷን ሰምተናል፡፡ የእስቴ መካነየሱስ መንገዶች በሰውና በመኪና ድርቀት ተመተው ውለዋል፡፡ የእስቴን ጤፍ ዘርገቶ የሚይዘው የመካነየሱስ ገበያ አእዋፋት ብቻ ወረውት ውለዋል፡፡ የመካነየሱስ የቤት ውስጥ አድማ ነገም ይቀጥላል፡፡
ጋይንት/ ነፋስ መውጫ፤ ትናንት ነሃሴ 24 ቀን የተጀመረው የቤት ውስጥ አድማ በጽጥታ አካላት ጣልቃ ገብነት ደፈረሰ፡፡ የጋይንት አናብስት ተቆጡ፡፡ ተኩስ ተጀመረ፡፡ አንድ ቅጥረኛ ፖሊስ ሦስት ዐማሮችን በጥይት አቆሰለ፡፡ ሕዝቡ ሊገድለው ሲል አመለጠ፡፡ ቤቱ ሔዱ፡፡ ተከራይ ሆኖ አገኙት፡፡ የቤቱን ሙሉ እቃ አውጥተው አስፓልት ላይ አቃጠሉት፡፡ ዐማሮች ከተማዋን ተቆጣጠሩ፡፡
የጋይንት ዐማሮች ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ዋለ፡፡ በጨጭሆ በኩልና በደብረ ታቦር መምጫ መንገዶች በሚገባ ተዘግተዋል፡፡ የነፋስ መውጫ ከተማ ሙሉ በሙሉ በዐማሮች እጅ ከሆነች ሁለተኛ ቀኗን አስቆጥራለች፡፡ የጋይንት ወጣቶች በአድማው የሚበሉትን ላጡ ሰዎች የምግብ እና የመጠጥ እርዳታ አድርገዋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ የታች ጋይንት ዐማሮችም ለተጋድሎ መውጣታቸውን ብንሰማም ከቦታው ያገኘነው መረጃ ባለመኖሩ ማካተት አልቻልንም፡፡
ደብረ ታቦር፤ የደ/ታቦር ዐማሮች የቤት ውስጥ አድማ ከመቱ ሁለተኛ ቀናቸው ነው፡፡ አንዳንድ ቅጥረኞች ሥራ ለመጀመር ትናንት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ያን የተቃወሙት የታቦር ልጆች በቅጥረኛ ወታደሮች ሁለት ወንድሞቻችን ተነጥቀዋል፡፡
በደብረ ታቦር 94 ቅጥረኛ ሰላዮች የተለዩ ሲሆን በሚቀጥሉት ቀናት ዐማራው ሕዝብ እርምጃ እንደሚወስድ ይጠበቃል ሲሉ አስተያየት የሠጡን ሰዎች ገልጸዋል፡፡ የታቦር ዐማሮች የፌደራል ፖሊሶችን መሣሪያም መንጠቃቸውን ሰምተናል፡፡ በጎበዝ አለቆችም መደራጀት ተጀምሯል፡፡ ደብረ ታቦር ግማሽ ነጻነት ላይ ያለች ከተማ ናት፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ የጋሳይና የክምር ድንጋይ ዐማሮች የካቢኔ አመራሮችን በሙሉ ማስወገዳቸውም ተገልጧል፡፡ ጋሳይና ክምር ድንጋይ መንገዶች ዝግ ናቸው፡፡
ወረታ/ ጉማራ፤ የወረታ ከተማም ትናንት ጀምሮ የቤት ውስጥ አድማ ላይ ናት፡፡ ትናንት ቅጥረኛ የሆኑ ሥጋ ቤታቸውን የከፈቱ 2 ግለሰቦች የወረታ ዐማሮች አዘግተዋል፡፡ መከላከያ ሠራዊት አስለቃሽ ጪስ በመጠቀም ወጣቱን የበተነ ቢሆንም መንገዶችን ሙሉ በሙሉ በመዝጋት የገባውን መከላከያ እንዳይወጣ አስጨንቀውት ሰንብተዋል፡፡ ትናንት ለዛሬ ሌሊት ጉማራ ላይ በገበሬውና በትግሬ መከላከያ መካከል ከፍተኛ ተኩስ አድሯል፡፡ በተኩስ ልውውጡ ሦስት የፎገራ ዐማሮች የተሰው ሲሆን ከሦስት በላይ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ተገድለዋል፡፡ ጉማራ ድልድይ መንገድ ተዘግቷል፡፡
ደባርቅ/ ጃናሞራ፤ ከደባርቅ ከተማ እስከ ጃናሞራና ደረስጌ ያለው አካባቢ ሙሉ በሙሉ ከመንግሥት ቁጥጥር ውጭ መሆኑን ዛሬ ሰምተናል፡፡ የፖርክ ጠበቂ የነበሩ ሚሊሻዎችን በማባረር ዐማራው ራሱን በራሱ እያስተዳደረ ነው፡፡
በለሳ/ አርባያ፤ የአርባያ በለሳ ሕዝብ መንግሥትን ካባረረ ዛሬ ሦስተኛ ቀኑ ነው፤ ሆኖም በስልክ ችግር ምክንያት የተሟላ መረጃ ማቅረብ አልቻልንም፡፡
በየቦታው መረጃ በማቅረብ ለምትተባበሩን ቁርጥ የዐማራ ልጆች ሁሉ በዐማራ ሕዝብ ስም ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials