Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, September 20, 2016

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ ምሁራን የመጀመሪያ ቀን ውይይት ሰው አየሞተ እና ህዝብ ለተቃውሞ እየወጣ political crisis ውስጥ ገብተን ስለትምህርት ጥራት እና ተደራሽነት መወያየት አኔን ያሳፍረኛል”

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ ምሁራን የመጀመሪያ ቀን የውይይት ውሎ በከፊል(መስከረም 9፣ 2009 ዓ.ም)፡-
በዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ካሳ ተ/ብርሀን አጠቃላይ የውይይት መድረኩ መነሻ አሳብ ትረካ እና የእለቱ የውይይት አጀንዳ በሆነው ያለፉት 25 ዓመታት የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ጉዞ ዙሪያ የሚያጠነጥን ገለፃ በኃላ በምርጦቹ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የተነሱ አስተያቶች እና የአካሄድ ጥያቄዎች:-
1. የመጀመሪያ ተናጋሪ፡-
1.1 “የዚህ ወይይት አጀንዳ ከጠበኩት በታች ወርዶብኛል በወላይቲኛ አንድ አባባል አለ ያቺ እንትን'ኮ ወደቀች ቢሏት፤ ቀድሞም አቀማመጧ ለመውደቅ ነው አለች”፡፡
1.2 “ካሳ! አንተ ሚኒስትር ነህ በዛ ላይ የዩኒቨርሲቲያችን የቦርድ ሊቀመንበር በዚህ ሁሉ ኃላፊነት ውስጥ ሆኖ PhD candidate መሆን አይቻልም ስለዚህ ስራህን ልቀቅ”
1.3 “ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ይምጣና ያወየን፣ እናንተ ውረዱና ከእኛ ጋር ተቀመጡ”
2. ሁለተኛ ተናጋሪ
2.1 “ይቺ ሀገር አንደ ሀገር አንደትቀጥል ከተፈለገ እኛ አድማጭ እናንተ ተናጋሪ የምትሆኑበት አካሄድ ማክተም አለበት፣ በዚህ ስብሰባ አኛ የእናንተን እንከን እናውራ እናንተ ደግሞ ዝም ብላችሁ አድምጡን”፡፡
3. ሦስተኛ ተናጋሪ
3.1 “የዛሬ ዓመት በተመሳሳይ የውይይት መድረክ ብዙ ቁም ነገሮች ተነስተው ነበር ነገር ግን አንዳቸውም ሳይተገበሩ ዛሬ ደግመን ተገናኘን”
3.2 “አቶ ካሳ የመንግሰት ስልጣን ይዘህ ለግል ጥቅምህ በማዋል የዩኒቨርስቲውን ህግ ጥሰህ PhD candidate ሆነሐል”
3.3 “ውይይቱን የመምራት ሞራል የለህም”
* የአቶ ካሳ መልስ፡-
1. “እኔ ውይይቱን የመምራት ችግር የለብኝም፣ ከእኔ የምትበልጡ ትልልቅ ምሑራንና ባለዕውቀቶች እንደላችሁ እሙን ነው ነገር ግን በአጋጣሚ የቦርድ ሰብሳቢ ሆኜ እስከተቀመጥኩ ድረስ ወይይቱን የመምራት ኃላፊነት አለብኝ”
2. “ይህ የውይይት መድረክ በመላ ሀገሪቱ ባሉ የትምህርት ተቋማት የሚደረግ እና መድረኩም አንዲመራ የተያዘለት ፕሮግራም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳይሆን በቦርድ ለቃነመናብርት ነው”
3. “አኔ ብማር ክፋቱ ምንድን ነው? እኔም'ኮ አንድ ዜጋ ነኝ፣ ትምሀርት የመጀመሩን እድል አግኝቼ ነበር ነገር ግን ጊዜ በማጣት ምክንያት ብቻ class attend ባለማድረጌ ለመቀጠል አልቻልኩም፣ ጊዜ ሲኖረኝ ግን ታሰተምሩኛላችው”
በመቀጠልም ከተሰብሳቢ ምሁራን አንዱ አጁን በማውጣት ማሳሰቢያ እንዳለው ተናገረ፤ አንዲናገር ዕድሉ ሲሰጠውም “በመጀመሪያ ይሄ ስብሰባ ሲጀመር በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ እና በኮንሶ በአልሞ ተኳሾች ለተገደሉ ንፅሑን ዜጎች የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ ሊሆን ይገባ ነበር” በዚህ ጊዜ የስብሰባው አዳራሽ ለረጅም ደቂቃ ባልተቋረጠ ጭብጨባ ተስተጋባ ሲቀጥልም “ሁሌም ተደጋጋሚ አጀንዳ ነው ይዛችው የምትመጡት ካችአምና የትምሀርት ጥራት አምና እና ዘንድሮም የትምህርት ጥራት መንም አዲስ ነገር የለም፣ ለዚህ ስበሰባ የተመደበው በጀት ተቀንሶ በተለያዩ ክልሎች በተነሱ ግጭቶች የቤተሰባቸውን አባላት ላጡ ወገኖች ይሰጥ ለእኛ የሶስት ቀን ውይይት ይበቃናል”
*ቀጣይ ተናጋሪ
-› “ሰው አየሞተ እና ህዝብ ለተቃውሞ እየወጣ political crisis ውስጥ ገብተን ስለትምህርት ጥራት እና ተደራሽነት መወያየት አኔን ያሳፍረኛል”
-› “ታልሞ የተመጣው ነገር ለኢቢሲ ዜና የሚሆን ነገር ለመቃረም ነው”
* ሌላ ተናጋሪ
-› “Next time I don’t want to see these board members (አቶ ካሳን ጨምሮ መድረኩን እየመሩ ያሉትን የዩኒቨርሲቲውን የቦርድ አባለት ነው)
-› “ዶ/ር አድማሱ ባለፈው ጊዜ አሜሪካን ሀገር ውስጥ በሱፐር ማርኬት ውስጥ የደረሰብዎትን አይተናል እነርሱ እዛ ወላፈኑ ገና ለገና ይደርስብናል ብለው ይህን ካደረጉ አኛስ እዚህ እንፋሎቱ ውስጥ የምንቀቀለው ምን እናድርግ?”
(ሱራፌል ሀቢብ)

No comments:

Post a Comment

wanted officials