Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, September 20, 2016

ኖኪያ አፕል ላይ ክስ መስረተ


ኖኪያ አፕል ላይ ክስ መስርቷል
 ቀደም ባለው ጊዜ በተንቀሳቃሽ ስልክ የገዘፈ ስምና ዝና የነበረው ኖኪያ ከአፕል ኩባንያ ጋር እሰጥ አገባ ውስጥ ገብቷል።
ኩባንያው እዚህ ሁኔታ ውስጥ የገባው፥ የአፕል ኩባንያ የድርጅቴ የሆኑ የፈጠራ ስራዎቼን በባለቤትነት ሲጠቀም የሚገባኝ ጥቅም አልሰጠኝም በሚል ነው።
ሁለቱ ኩባንያዎች በፈረንጆቹ 2011 ላይ የኖኪያ የሆኑ 32 አይነት የፈጠራ ስራዎችን አፕል ገዝቶ በባለቤትነት እንዲጠቀም ተስማምተው ነበር።
በስምምነቱ አፕል የሚያመርታቸው የአይ ፎን ተንቀሳቃሽ ስልኮች ላይ፥ እነዚህ የኖኪያ የፈጠራ ውጤቶችን እንዲጠቀም ነበር የተስማሙት።
በዚህም አንቴናዎችን ጨምሮ የቪዲዮ፣ የስልኩን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር የሚረዱ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚያደርጉ እንዲሁም ሌሎችም የኖኪያ የሆኑ የፈጠራ ስራዎች አፕል በአይ ፎን ላይ ይጠቀምባቸዋል።
ለተጠቀመበት የፈጠራ ስራ እና ውጤትም አፕል በምላሹ ለኖኪያ ገንዘብ እንዲሰጥ ነበር የተስማሙት።
ይሁን እንጅ ይህ ስምምነት በተባለው መሰረት አልተተገበረም በማለት ኖኪያ የፍርድ ቤት ክሱን መጀመሩን ገልጿል።
በአሜሪካና በጀርመን በከፈተው ክስ ፥ ኖኪያ ከአፕል ኩባንያ ለእነዚህ የፈጠራ ስራዎች ወደ 750 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚገባውም ነው የገለጸው።
በአንጻሩ ደግሞ አፕል ለተጠቀምኩበት የፈጠራ ውጤት ተገቢውን ክፍያ እፈጽማለሁ ብሏል።
የአሁኑ የኖኪያ አካሄድ እና አዝማሚያ ግን ገንዘብ ለማጋበስ የታለመ ነው ሲልም በቃል አቀባዩ አማካኝነት ገልጿል።
ግዙፍ ተቋማትና ኩባንያዎች ብዙ ጊዜ ከፈጠራ ውጤት ባለቤትነት ጋር ተያይዞ መሰል ንትርክ ውስጥ ሲገቡ ይስተዋላል።
ቀዝቀዝ ብሎ የቆየው የዘርፉ አጋጣሚ እና ክስም በሁለቱ ኩባንያዎች የተጀመረ ይመስላል።
ከዘርፉ ረዘም ላለ ጊዜ ርቆ የቆየው ኖኪያም፥ ደንበኞቸ በሚያውቁኝ ዘመኑን ታሳቢ ያደረገ ምርት ወደ ገበያ እየመጣሁ ነው ሲል መግለጹ የሚታወስ ነው።
ምንጭ፦ fossbytes.com

No comments:

Post a Comment

wanted officials