Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, September 25, 2016

በጎንደር ጸዳ ወረዳ ይኖሩ የነበሩ አቶ አለምነህ ዋሴ የተባሉት የሃገር ሽማግሌ በደህንነቶች ታፈኑ


ኢሳት ( መስከረም 13 ፥ 2009)
በጎንደር ጸዳ ወረዳ አካባቢ የሃገር ሽማግሌ የነበሩት በህወሃት ደህንነቶች ታፈኑ።  አቶ አለምነህ ዋሴ የተባሉት የቀድሞ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት የጸዳ ወረዳ ተወካይ በደህንነቶች የታፈኑት አዲስ አበባ ለስራ በሄዱበት ሆቴል ውስጥ ነው።
እስካሁን የት እንዳሉ ያልታወቁት አቶ አለምነህ፣ ቤተሰቦቻቸው እየፈለጓቸው እንደሆነ ተነግሯል።
ህወሃት መራሹ መንግስት በርካታ ዜጎች በተለያየ ስፍራ እየታፈኑ እየተወሰዱ ሲሆን፣ የት እንዳሉ የማይታወቁ በርካቶች ናቸው።
አቶ አለም ነህ ዋሴ በጎንደርና አካባቢው በህብረተሰቡ ውስጥ ሆነው ለሃገር ሽማግሌነት የሚያገለግሉ ሲሆን፣ በስጋት ውስጥ የሚገኘው ህወሃት ዜጎችን ማፈኑን ቀጥሏል።
ስርዓቱ ከአማራ ክልል አዲስ አበባ የሚመጡና ሆቴል የሚያርፉትን እንዲያሳውቁ ትዕዛዝ መስጠቱ ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials