የምስራች ለተዋህዶ ልጆች በሙሉ – ቦይኮቱ በሚገባ እየተሳካ ነው | ዘመድኩን በቀለ
✔# የሙዳይምጽዋቱና ✔# የአስራትበኩራት እቀባውም እየተሳካና መስመሩን ይዞ እየሄደ ነው ።
✔በውስጥ መስመር እየደረሱኝ የሚገኙት መልእክቶች እጅግ ደስ የሚያሰኙና ከስኬት ጫፍ የሚያደርሱን መሆናቸውን እያየሁ ነው ። በተለይ በየከተማው የምትገኙ የጽዋ ማኅበራት አጀማመራችሁ መልካም ነውና በዚሁ ቀጥሉበት ።
✔ ወጣቶች ከቤተሰብ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ በደንብ ምከሩበት ። ለወላጆችም በቤት ውስጥ ሁሉን አስረዷቸው ።
✔ ባለ ጊዜዎች ሆይ! በቫይበርና በስልክ እኔን መወትወቱና መለመኑ ዋጋ የለውም ።እስትንፋሴ እስክትቆም ድረስ ቅድስት ቤተክርስቲያን ከዘር ፖለቲካም እስክትጸዳ ድረስ እሟገታችኋለሁ ። ወላዲተ አምላክ ምስክሬ ናት አንላቀቅም ።

በአዲስ አበባና በሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች በሚገኙ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት የምንገኝ ምእመናን ለሚቀጥሉት ሦስት ወራት ሙዳየምጽዋትና አስራት በኩራታችንን በእጃችን ላይ በማቆየት እነዚህን በእኛው ገንዘብ እንደ ሐረር ሰንጋ እየደለቡ የወገናቸው ሞት የማይሰማቸውን የሃይማኖት ሳይሆን የፖለቲካ ሹመኞች የገቢ ምንጫቸውን ልናደርቅ ይገባል ።
“ልጆቻችሁ አርፈው እንዲቀመጡ አድርጉ ። ያለበለዚያ ግን ወጋችሁን ነው የምንሰጣችሁ ” አይነት ንግግር በመናገር ልባችንን ያደሙትን ፓትርያርክ አባ ማትያስን አዲስ አበባ ቁጭ አድርገን የምንቀልበው እኛው ነን ። ንቡረእድ ኤልያስን ከመሬት ተነስቶ ባለፎቅ ያደረግነው እኛው ነን ። ትናንት ባዶ እግራቸውን ያለምንም ሳንቲም ባዶ እጃቸውን ሲዞሩ የምናውቃቸውን ዛሬ ግን ያለምንም የሙያ መስፈርት የአንድ ብሄርና የአንድ ቋንቋ ተናጋሪ በመሆናቸው ብቻ ወደ ኢንቨስተርነት የተለወጡትን ፣ አስመጪና ላኪም የሆኑ የደብር አለቆች ፣ ጸሐፊ ፣ ቁጥጥርና ፣ ሒሳብ ሹም ፣ ወዘተ በአንድ ቋንቋ እያወሩ ከደሃው ህዝብ ተሰብስቦ በሚገባው ገንዘብ ዓለማቸውን በሚቀጩ ዘራፊዎች ላይ እቀባው ተጠናክሮ ይቀጥላል ።
እመኑኝ በአሁኑ ጊዜ የአስራት ገንዘቡን ዘወትር በማኅሌትና በሰዓታት በኪዳን ጸሎትና በቅዳሴ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል የሚያመሰግነው ምስኪኑ ካህን ፍርፋሪ አይደርሰውም ። ቤሳ ቤስቲን አልኳችሁ ምንም አይደርሰውም ። በተለይ ካህናቱና ዲያቆናቱ አማራ ፣ ኦሮሞ ፣ ጉራጌና የደቡብ ተወላጅ ከሆኑ ዋጋ የላቸውም ። እጣፈንታቸው የቀጭን ጌቶቹን ጫማ በመሸከም እንደውሻ እግራቸው ስር ከመለጥመጥ በቀር አንዳች ማድረግ አይቻላቸውም ።
የሚገርመው አንድም ቀን በማኅሌቱ ላይ ሳይታዩ ቅዳሴም ሳይገቡ ቤተክርስቲያንም ሳይደርሱ እቤታቸው ቁጭ ብለው ከሁለትና ከሦስት አብያተክርስቲያናት ደሞዝ የሚበሉ ደፋሮች አሉ ። ምክንያቱም ” ምርጥ ዘርና ባለጊዜዎች ” ነን ብለው ለራሳቸው ልዩ ያልተጻፈ ህግ አውጥተው ስለሚኖሩ ።
እነዚህ አለቆች አብዛኛዎቹ የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ታጋይ ወታደሮችም ጭምር ስለሆኑ ፖሊስን ያዛሉ ፣ አግአዚን ይጠራሉ ፣ ሰንበት ትምህርትቤቶችን እንደፈለጉ ይዘጋሉ ሲፈልጉ ያሳስራሉ ይበትናሉ ። ምክንያቱም እነሱ ካድሬና የፓርቲ አባል አይነኬ አይጠጌ ስለሆኑ ማለት ነው ።
እናም እነዚህ ሰዎች አፍ አውጥተው መንግሥትን ህዝቡን አትግደል ፣ በእስር ቤት አጉረህ በእሳት አቃጥለህ አትጨፍጭፍ አይሉትም ። ምክንያቱም እነሱም የፓርቲው አባላት ስለሆኑ ፓርቲያቸውን ከመታደግ አንጻር ምህላና ጸሎት ያዛሉ ተብሎም አይጠበቅም ። እንዲያውም እነዚህ ሰዎች ራሳቸውን ቀይረው ማታ ማታ በየ መሸታ ቤቱ እንደሚንዘላዘሉት የፖሊስ ልብስ ለብሰው ሰላማዊ ሰልፈኞችን በመግደሉ በኩል ተሳታፊ አይሆኑም ብዬ ላለማመን አልሞክርም ።
እናም ወገኖቼ እነዚህን ደም መጣጮች፣ መዥገሮችና የቤተክርስቲያን ነቀርሳዎችን ከቤተክርስቲያን ትከሻ ላይ አራግፈን የመጣያው ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው ።
ለእነዚህ ዘረኞች የሆኑ ምድብ ፖለቲከኛና በስመ የሃይማኖት አባትነት በቅድስት ቤተክርስቲያን ተሰግስገው ለተቀመጡ ሰዎች የአስራት ገንዘቡን ገታ አድርገን ካልያዝነው ለእነሱ ለክ እንደ አባይ ወንዝ ያለ ነው ። ልክ እንደ ሳውዲ አረቢያ የነዳጅ ጉድጓድ ያለ ነው ። ከአሜሪካ ዶላሩ ፣ ከእንጊሊዝ ፓውንዱ ፣ ከአውሮጳ ዩሮው ፣ ከእስራኤል ሸክሉ ፣ ከስዊዝ ፍራንኩ ፣ ከአረቢያ ምድር በየሰው ቤት በእሳት ተቃጥለው የሚልኩት ሪያል የእነዚህ ማደለቢያ ነው ።

እና አስራቱን ምን እናድርግ ?
ለሱ መፍትሄው ቀላል ነው ።
1ኛ፦ ምስኪን ካህናትና ተንከራታች ደጅ ጠኚም ሆነው ረሃብ የሚያሰቃያቸውን አባቶችን እስከ ጊዜው ድረስ እነሱንም ቤተሰባቸውንም መርዳት ። በተለይ በተለይ ቤተሰብ ያላቸውንና በቤትኪራይ ውስጥ የሚኖሩትን ፣ ልጆቻቸውን የሚያስተምሩ ካህናትን በንስሐ ልጆቻቸው በኩል መርዳት ።
2ኛ፦ የቤተክርስቲያን ተተኪ የሚያፈሩትን የአብነት ትምህርት ቤት መምህራንን እና ተማሪዎችን በመርዳት ጉባኤ ቤቶች እንዳይፈቱ ማድረግ ።
3ኛ፦ እንደ ዋልድባ ያሉትን በችግር ላይ የወደቁና ሊበተኑ የደረሱ ስመጥር ገዳማትን የሚያስፈልጋቸውን በማቀረብ ገዳማቱ ሳይፈቱ እና ገዳማውያኑም ሳይበተኑ በአስራት ገነረዘቡ መርዳት ።
4ኛ፦ እንደ ደጆችሽ አይዘጉ አይነት የሚታይና የሚዳሰስ አሳማኝ ሥራ የሚሠሩ ማኅበራትን በሚገባ በተጠናከረ መንገድ መርዳትና መደገፍ ።
5ኛ፦ እንደ መቄዶንያ የአእምሮና የህሙማን መርጃ ማእከል ያሉትን ፣ ጌርጌሶኖን ፣ የወደቀ አንሱ የመሳሰሉት በየጎዳናው በረሃብ የሚሰቃዩትን አረጋውያን እና ህጻናትን እርዱበት ።
ይሄን በማድረግ በዝባዦችን እንቅጣ ።
ይህን እቀባ በመቃወም በዚህ በእኔ ፔጅ ላይ ፒሪሪም ፓራራም ታራራራም እያሉ የሚያላዝኑ እነ ገብረምናምንን ፈጽሞ አልሰማችሁም ።
አሁን በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ስላለው ግፍና መከራ ለመናገር እውነት እውነት እላችኋለሁ ሰባኪም ፣ ፖለቲከኛም ፣ አትሌትም ፣ ሆነ ግንበኛ ፣ መሆንን አይጠይቅም ። ” ጉዳዩን ለመቃወም ሰው መሆን ብቻውን በቂ ነው ” ።
እኔን የየሚደንቀኝ ይህን መልእክት እንኳ እያዩ እየተመለከቱ ሼርና ኮመንት ለመስጠት እንኳ በፍርሀት ቆፈን መታሠራቸው ነው ።
ጉዞው እስከ ቀራንዮ ነው ፣ ድል ለእምዬ ተዋህዶ !!! ወድቀት ለዘረኞች ።
ይህንንም ራሴው ዘመድኩን በቀለ ጻፍኩት ።ለማንኛውም በነጻነት እንወያይ ከስድብና ከዛቻ በራቀ መልኩ እንነጋገር ። +251911608054 የቫይበር ስልኬ ነው ። በተለይ ይህን መልእክቴን በተመለከተ ደግሞ ✔Coment መስጠትና
✔Share ማድረግ በእጅጉ ይበረታተል ።
ሻሎም ! ሰላም !
ዘመድኩን በቀለ ነኝ
ጷግሜን 4 /13/2008 ዓም
ኮሎኝ – ጀርመን

No comments:
Post a Comment