Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, September 14, 2016

የኮንሶ መንደሮች የ987 ነዋሪዎች መኖሪያ ቤታቸው በከባድ መሳሪያ አመድ በአመድ ሆኗል



የኮንሶ መንደሮች አይሎታ ዶካቱ እና ሉሊቶ ትግሬ-ወያኔዎች እና አሽከሮቻቸው ጋዩ:: ከፍጅቱ ማምለጥ የቻሉ ሲያመልጥ አቅመ ደካሞች እንዲሁም ሴቶችና ህፃናትን ጨምሮ ብዙዎች ተገለዋል። ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብም በሽሽት ኮንሶ ካራት ከተማን አጥለቅልቋት በረሀብና በጥም እንየተንገላታ ነው።
የኮንሶ ህዝብ ማንኛውም ወገን ሰበዓዊ ድርጅቶች እርዳታ እንዲለግሱዋቸውም እየጠየቁ ነው።
ከ3000 በላይ ወታደር ከነሙሉ ትጥቁ ሰፍሮ ጥይት እያርከፈከፈ ህዝቡን እየፈጀው ነው።


በደቡብ ክልል አመራሮች ድጋፍ የሃገር መከላከያ ሰራዊት በኮንሶ ህዝብ ላያ በከፈቱት የዘረ ጭፍጨፋን ተከትሎ 65 ሰው ህይወት ስያልፍ 45 የሚሆኑትን በራሳቸው በሰራዊቱ መኪና ጭነው የት እንዳስገቡ አይታወቅም የ987 ነዋሪዎች መኖሪያ ቤታቸው በከባድ መሳሪያ አመድ በአመድ ሆኗል። በሰአቱ አቅም ያለው ሲያመልጥ አቅም የሌላቸው ብዙ ህፃናት ቤት ውስጥ መቃጠላቸው መረጃዎች ሲጠቁሙ ከስምንት ቀበሌ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ወደ መዲና ከተማቸው ለማምለጥ ሲጥሩ መግቢያ መንገዶች ሁሉ በሰራዊት ታጥረው ከመፍራታቸው የተነሳ ወደ አረባምንጭ መስመር ሲጓዙ የነበሩ እናቶች ከነ ህፃናታቸው በረሀብና ጥማት እያለቁ ይገኛሉ።በኮንሶ በርካታ ዜጎች ተገደሉ : አካባቢው የጦርነት ቀጣና ሆኗል ተባለ።

የመከላከያ ሰራዊት እና የደቡብ ክልል የልዩ ሃይል አባላት በኮንሶ ህዝብ ላይ እየፈጸሙት ባለው ጥቃት በርካታ ዜጎች ተገድለዋል። እስካሁን ድረስ ባለው መረጃ ከ25 ያላነሱ ሰዎች ተገድለዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች ግን የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ይሆናል ይላሉ። ከተገደሉት መካከል አንድ አራስ ሴት በጥይት ተደብድባ ስትገደል፣ ህጻኑ በወታደሮች ተወስዷል በማለት የአገር ሽማግሌዎች ገልጸዋል።

ትናንት ብቻ ከ4 ሺ 50 በላይ ሰዎች የተሰደዱ ሲሆን፣ ዛሬም ስደቱ ቀጥሎአል በማለት የአገር ሽማግሌዎች ይናገራሉ።


ጭፍጨፋውና እልቂቱ ሊቀጥል እንደሚችል የአገር ሽማግሌዎች ስጋታቸውን ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials