Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, September 6, 2016

ኤልፎራ በበሽታ የተጠቁ ዶሮዎችን ለአዲስ ዓመት ገበያ ለያቀርብ ነው


ላምበረት በሚገኘው የሚድሮክ ኢትዮጵያ ኤልፎራ የዶሮ ተዋፅኦ ማምረቻ ውስጥ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ዘንድሮ ለአዲስ ዓመት ለገበያ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ሚቀርቡት ዶሮዎች መካከል ምርመራ የተደረገላቸው ከአንድ መቶ ሰባ በላይ በሳልሞኔላ ባክቴሪያ የተጠቁ ዶሮዎች ተገኝተዋል።
ይህ ባክቴሪያ ወደሰው ልጆች ተላልፎ ሳልሞኔሎሲስ የተሰኘ በሽታ የሚያሲዝ ሲሆን በበሽታው የተጠቃ ግለሰብ እስከ 7 ቀን የሚደርስ ከፍተኛ ትኩሳት እና ማስመለስ የሚያጋጥመው ሲሆን በሽታው ከሰው ወደሰው የሚተላለፍም ነው፤ በቶሎ ካልታወቀ በሽታው እስከሞት ያደርሳልም ተብሏል። 
ይህ ባክቴሪያ ዶሮዎቹ ላይ መገኘቱ እየታወቀ ዶሮዎቹ ለገበያ ይቀርባሉ ተብለን ጉዳዩን የምናውቅ ሰዎች ተጨንቀናል ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ ያልፈጉ ምንጮቻችን ገልጸዋል።
የመረጃ ምንጮቻችን አክለውም እናም እባክህ መልእክቱን ለኢትዮጵያ ህዝብ በማሳወቅ የኢትዮጵያን ህዝብ ከሳልሞኔሎሲስ እንታደገው ዘንድ በአጽንኦት ጠይቀዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials