Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, September 5, 2016

የሰውን ልጅ ባህሪያት እና ተግባራት የተጎናፀፉ አምስት እንስሳትን እናስተዋውቅዎ.

የሰውን ልጅ ባህሪያት እና ተግባራት የተጎናፀፉ አምስት እንስሳትን እናስተዋውቅዎ..

የሰውን ልጅ ባህሪያት እና ተግባራት የተጎናፀፉ አምስት እንስሳትን እናስተዋውቅዎ..
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቅርቡ የተሰሩ ጥናቶች እኛ ከምናስበው በላይ የሰውን ልጅ ባህሪ እና ተግባር የሚጋሩ እንስሳት መኖራቸውን ይፋ አድርገዋል።
እነዚህ እንስሳት በተፈጥሮ ከተሰጡት የተግባር እና የማሰብ ክህሎት ባሻገር የሰውን ልጅ ተግባር እና ፍላጎት እንዲሁም ባህሪ ተላብሰው ተገኝተዋል።
በዚህም ተግባራቸው ሰዋዊ ድርጊትን የሚፈፅሙ እንስሳት ተብለዋል።

1. አይጥ 

አይጥ ከሰው ልጅ የሚያመሳስላት በርካታ ነገሮች አሉ። 
ይህቺ በቤት እና በዱር የምትኖር ትንሽ እንስሳ ከሰው ልጅ ጋር የሚያመሳስላትን ባህሪ ሳይንቲስቶች ይፋ አድርገዋል። 
አይጥ ልክ እንደ ሰዎች ፒዛ በጣም ትውዳለች።
ደረጃዎችን መውጣትም በጣም ያስደስታታል ተብሏል።
ሰሞኑን ይፋ የተደረገው የተመራማሪዎች ግኝት አይጥ እንደ ሰው ስትኮረኮር ትስቃለች ይላል።
2. የሌሊት ወፎች
ሴት የሌሊት ወፎች ሰዎች የተቃራኒ ጾታቸውን ጠረን በማሽተት እንደሚነቃቁ ልክ እንደዚህ ሁሉ ሴት የሌሊት ወፎችም በወንድ ጓደኞቻቸው ጠረን ወይም ሽታ ከተኙበት የሚነቁ ሲሆን መንፈሳቸውን በማደስ ደስ ይሰኛሉ ነው የተባለው።
በዚህም የጓደኞቻቸውን ሽታ በመለየት ከሰው ይመሳሰላሉ።
3. ፈረሶች
ሰዎች እኛ ማድረግ የማንችለውን ወይም አዲስ የሆነብንን ነገር ሌሎች እንዲረዱን እንደምንጠይቅ ሁሉ ፈረሶች ችግር ላይ ሲወድቁ ሰውን እርዳታ ይጠይቃሉ። 
የአሜሪካ ተመራማሪዎች የሰው ልጅ ብቻ ሊያገኘው የሚችለውን ምግብ በባልዲ ውስጥ አድርገው የፈረሶችን የማሰብ አቅም የለኩ ሲሆን፥ ፈረሶቹ ምግቡን የት እንዳለ ቢውቁም ማግኘት እና መመገብ ሳይችሉ ይቀራሉ።
ይህን ጊዜ ታዲያ ምግቡን ከያዘው ባልዲ አጠገብ ሆነው ተንከባካቢያቸውን አይን አይን ያዩታል፤ በዓይናቸው ይማፀኑታል፤ በአገጫቸውም እየነኩ ምግቡን እንዲሰጣቸው ምልክት ያሳዩታል።
ፈረሶች ተንከባካቢያቸው ምግቡን በቀላሉ ባያገኘው እና ለመስጠት ቢቸገር ያለበትን በመጠቆም እንደራባቸው በምልክት በማሳየት እና በመተሻሸት መለመናቸው የሰውን ልጅ ባህሪ መላበሳቸውን ያሳያል ነው የተባለው።
4. ውሾች 
ውሾች በአቅራቢያቸው የሚገኙ ሰዎች በቅርብ ጊዜ ምን እንደሰሩ ያውቃሉ፤ የማስታወስ ብቃታቸውም ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡ 
ውሻ ያላችሁ ሰዎች ይህን ልብ ብላችሁት ይሆን? ከውሻዎቻችሁ ፊት የሰራችሁትን ስራ ውሻችሁ ረስቶታል ብላችሁ ብታስቡ ተሳስታችኋል የሚል ግኝትን ይዞ የመጣ አንድ ጥናት ውሻ ልክ እንደ ሰው የማስታወስ ችሎታ አለው ብሏል።
ተመራማሪዎች ይህን ለማወቅ ውሻውን "ልክ እኔ እንዳደረኩት እናንተም አድርጉ" የሚል ዘዴን ይጠቀማሉ፤ በተግባርም በመተኛት እና በመነሳት ለውሾች ያሳያሉ፡፡ 
ከ1 ሰዓት ክፍተት በኋላም ሰዎች ሲሰሩት የቆይቱን እንዲደግሙ ውሾችን ሲያዝዟቸው ያለምንም ስህተት በተግባር ፈጽመውታል፤ ይህም የሰውን ልጅ ባህሪ እና የተግባር መላመድ እንዲያሳይ አስችሏዋል ነው የተባለው፡፡
5. አሳነባሪዎች
ወጣት ወንድ አሳነባሪዎች ከሰው ጋር የሚያመሳስላቸው ነገር የሚል ጥናትም ይፋ ሆኗል።
የሰው ልጅ ቤቱን እንደሚወድ ሁሉ ወጣት አሳ ነባሪዎችም ከቤታቸው ሳይርቁ መኖር ደስ ያሰኛቸዋል ነው ያለው።
ከ1 ሺህ በላይ የአሳ ነባሪዎችን ውሎ እና አዳር የያዙ ፎቶግራፎች ላይ እንደታየው የሰው ልጅ ከቤቱ ወጥቶ ሲያድር እንደሚጨንቀው ሁሉ አሳ ነባሪዎችም ከቤታቸው መራቅ ይከብዳቸዋል፤ ቤታቸውን ትተው መራቅ አይሆንላቸውም ተብሏል፡፡ 
ጥናቱ ይህን የወጣት አሳ ነባሪዎችን ተግባር ቤታቸውን ለሰከንድ ትተው መውጣት ከማይፈልጉ ወጣት የኮሌጅ ተማሪ አሜሪካውያን ጋር አመሳስሎታል፡፡

ምንጭ፦ www.psychologytoday.com/

No comments:

Post a Comment

wanted officials