Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, September 12, 2016

የትግርኛ ዘፋኙ ዝግጅት በስዊዘርላንድ ተስተጓጎለ ከዛም ተሰረዘ




ጴጥሮስ አሸናፊ

የኢትዮጵያ አምላክ ይፈርዳል ሳይውል ሳያድር
ይጥልላታል ጠላቷን ከባንዲራዋ ስር

በስዊዘርላንዷ ቢል-ቢዬን ከተማ የትግርኛ ሙዚቃ ተጫዋቹ ዳዊት ነጋ (ወዛመይ) የአዲስ አመት የሙዚቃ ዝግጅት እንዲሰርዝ በተደጋጋሚ ቢጠየቅም አሻፈረኝ በማለት ቅዳሜ ማታ ዝግጅቱን ለማቅረብ ወደተዘጋጀለት አዳራሽ ቢያመራም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በርካታ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በዕለቱ ለመታደም ባለመፈለጋቸው በምሽቱ ከ 50 ሰው ያነሰ ብቻ በመገኘቱ በአስመጭዎቹና በዘፋኙ መካከል ቀሪዬን ገንዘብ ክፈሉኝ አንከፍልም ግብግብ የተፈጠረ ቢሆንም ጥቂት ሳይቆይ ከየት እንደተነሳ ባልታወቀ መልኩ ጭስ አዳራሹ ውስጥ በመታየቱ የከተማው ፖሊስ የሙዚቃውን ዝግጅት ለመሰረዝ ተገዷል።

ይህንንም ተከትሎ ዘፋኙ የፊታችን ቅዳሜ ሴፕቴምበር 16 ቀን በሌላዋ የስዊዝ ከተማ ዙሪክ ሊያቀርበው የነበረውን የሙዚቃ ዝግጅት መሰረዛቸውን የዙሪክ አዘጋጆች ማምሻውን በማኅበራዊ ኔትዎርኮች እየገለፁ ይገኛሉ።

አሁንም እንላለን:
ሙዚቀኞችና የሙዚቃ አዘጋጆች ከሕዝብ ጋር ቁሙ!
ለሚያልፍ ቀን ከሕዝብ ጋር እልህ አትጋቡ!
ሕዝብ ምንጊዜም አሸናፊ ነው!
የኢትዮጵያ አምላክ አያንቀላፋም!

No comments:

Post a Comment

wanted officials