Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, June 15, 2014

ሶስት ጋዜጠኞች እና ሶስት ጦማሪያኖች ለሐምሌ 5 ቀን 2006 ዓ.ም በድጋሚ ተቀጠሩ

ሶስት ጋዜጠኞች እና ሶስት ጦማሪያኖች ለሐምሌ 5 ቀን 2006 ዓ. ም በድጋሚ ተቀጠሩ
ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ወደ ፍርድ ቤቱ ሲገባ በእልህ ስሜት የታሰረበትን የብረት ካቴና አሳየ
=================
በዛሬው ዕለት በአራዳ ፍ / ቤት ቀርበው የነበሩት ሦስት ጋዜጠኞች እና ጦማሪያኖች (ኤዶም, ናትናኤል, አጥናፍ, ተስፋለም, አስማማውና ዘላለም) የ 28 ቀናት ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ለሐምሌ 5 ቀን 2006 ዓ. ም በድጋሚ እንዲቀርቡ ፍ / ቤቱ ትዕዛዝ ሰጠ.
የፖሊስ መርማሪዎች በጥቅሉ በርካታ ሥራ መስራታቸውን እና በርካታ የምርመራ ሥራ እንደሚቀራቸው ለፍ / ቤቱ ተናግረው ነበር. ፍ / ቤቱም << ዝርዝር ጉዳይ ማቅረብ ያስፈልጋል >> በሚል በጥያቄ ግፊት በማድረጉ መርማሪዎቹ የተወሰኑ ምስክሮችን መስማታቸውን, የተወሰኑ ተባባሪዎችን ቤት መፈተሻቸውን , የተወሰነ የትርጉም ሥራ መስራታቸውንና ከባንኮች መግለጫ ጠይቀው የተወሰነ መልስ ማግኘታቸውን ለችሎቱ አስረድተዋል.
ፍ / ቤቱም ከዚህ በኋላ ተባባሪ ለማያዝ, ምስክር ለመስማት, ሰነድ ለመተርጎምና የቴክኒክ ፎረንሲክ ምርመራ ለማድረግ በሚል ጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ እንደማይቀበል ለፖሊስ አጽንኦት በመሽጠት አሳስቧል.
በተጨማሪም ጋዜጠኛ አስማማው, በበኩሉ የወገብ ሕመም ስላለበት በታሰረበት ክፍል ውስጥ ወንበር ገብቶለት መቀመጥ እንዲችል ለፖሊስ አስተዳደሩ ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርብም እስከአሁን ድረስ መፍትሔ አለማግኘቱን ለፍ / ቤቱ አቤቱታውን አቅርቧል.
መርማሪውም ጋዜጠኛ አስማማው የወገብ ሕመም እንዳለበት እንደነገረው, ነገር ግን የወንበር ይግባልኝ ጥያቄ አለማቅረቡን ጠቅሶ ምላሽ ሰጥቷል.
ፍ / ቤቱም የግራ ቀኙን አስተያየት ካደመጠ በኋላ የተጠርጣሪው መብት እንዲከበር ሲል ትዕዛዝ ሠጥቷል.
እንዲሁም ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ መሳሪያ በታጠቁ ፖሊሶች ታጅቦ ወደ ፍርድ ቤቱ ሲገባ (የፍርድ ቤቱ ሕንጻ አጠገብ) እልህ በተናነቀው ስሜት የታሰረበትን የብረት ካቴና ከፍ በማድረግ ለተወሰንን ሰዎች በሚታይ መልኩ ካቴናውን በእልህ እያነቃነቀ አሳይቶናል.
ጋዜጠኛ ኤዶም, ጦማሪያኑ አጥናፍ እና ናትናኤል ፈገግ እና ሳቅ እያሉ በፍ / ቤቱ ቅጥር ግቢ የነበርነውን ታዳሚያን ሰላምታ ሰጥተውናል.

No comments:

Post a Comment

wanted officials