Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, June 28, 2014

ሰርካለም ፋሲል በቴዎድሮስ ባህሩ ላይ የመሰረተቻቸው ክሶች

ሰርካለም ፋሲል በቴዎድሮስ ባህሩ ላይ የመሰረተቻቸው ክሶች

የህወሐት ገዥ አካል እርሷን እና ባለቤቷን እስክንድር ነጋን ወደ እስር ቤት እስከወረወረበት ጊዜ ድረስ በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት ጋዜጠኛ እና አሳታሚ ሆና ስትሰራ በቆየችው ሰርካለም ፋሲል በቴዎድሮስ ባህሩ ላይ በጣም ጠንካራና ማስረጃ የሞላው ክስ አቅረባለች፡፡ ሁለቱም ሰርካለም እና እስክንድር (በአሁኑ ጊዜ በሀሰት የሸፍጥ ክስ ተመስርቶበት የ18 ዓመታት እስራት ተበይኖበት ከመሀል ከተማ በጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በሚገኘው በታዋቂው የ “መለስ ዜናዊ የቃሊ እስር ቤት”በመማቀቅ ላይ ያለው) በዘመናዊ የአፍሪካ የነጻ ጋዜጠኞች ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በገዥው አካል ጥቃት የተፈጸመባቸው እና ከፍተኛ የሆነ ዓለም አቀፋዊ አድናቆትን ያገኙ ሰላማዊ ጋዜጠኞች እስክንድርና ሰርካለም ናቸው፡፡ ባለፉት ሶስት ዓመታት ውሰጥ እስክንድር እያንዳንዱን ታዋቂ እና ታላላቅ ዓለም አቀፋዊ የፕሬስ ሽልማቶች አሸናፊ ነበር :: ከሁለት ሳምንታት በፊት በተወካዩ አማካይነት የተቀበለውን የ2014 ወርቃማ የብዕር የነጻነት ሽልማት ጨምሮ በዓለም ታዋቂና ተወዳጅ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ ሰርካለምም እንደዚሁ “ዓለም አቀፍ የሴቶች ሜዲያ ፋውንዴሽን” ከተባለው ዓለም አቀፍ የፕሬስ ድርጅት አደጋ ተደቅኖ ባለበት ሁኔታ የተለዬ ጀግንነትን ለሚያሳዩ ጋዜጠኞች ”ለደፋር ጋዜጠኝነት ሽልማት“ የሚለውን ጨምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ የፕሬስ ሽልማቶችን አግኝታለች፡፡ በተቀዳ የድምጽ/ኦዲዮ ቃለ መጠይቅ ሰርካለም ቴዎድሮስ ባህሩ በቀላሉ “ትዕዛዝን ብቻ በመቀበል” የሰራ አይደለም፡፡ ይልቁንም ከፍርድ ቤቶች ውጭ ወደ እስር ቤት እንዲገባ እና እንዲወጣ ትዕዛዝ ከሚሰጡት ሰዎች አንዱ ነበር ብላለች፡፡ ሰርካለም በተጨባጭ እንዳስቀመጠችው ባህሩ ባለቤቷን የገዥውን አካል ትዕዛዝ ተቀብሎ ከመተግበርም ባሻገር “ሆን ብሎ እና ስሜታዊነት በተሞላበት ሁኔታ” ሲያሰቃየው እንደደነበረ ገልጻለች፡፡ እንደ ሰርካለም አባባል ከሆነ ባህሩ ቁጡ፣ ጨካኝ፣ ችግር ፈጣሪ፣ ምህረት የለሽ እና ሩህሩህነት የማይሰማው አረመኔ አቃቤ ህግ ነበር ብላለች፡፡ እንደ ባለሙያ ዓቃቤ ህግ የሚገባውን ህጋዊ ስርዓት ተከትሎ የሚሰራ ሳይሆን እንደ ፖለቲካ አቃቤ ህግ ተከላካዮችን ያድን ነበር፡፡ ባህሩ ተከላካዮችን አሳንሶ ለማሳየት በፍርድ ቤቱ ችሎት ፊት ሁሉንም አጋጣሚዎች ሁሉ ያደርግ ነበር፡፡ ተከላካዮች ምንም ዓይነት ወንጀል ያልሰሩ ነጻ መሆናቸውን ሊያስረዱ የሚችሉ ሰነዶችን እና ምስክሮችን በሚያቀርቡበት ጊዜ ሁሉ እነዚህን በሚያስተባብል መልኩ ተቃውሞዎችን እያቀረበ ይከላከል ነበር፡፡ ተከላካዮች ፍትሀዊ ብይን እንዳያገኙ እና ማለቂያ በሌለው ረዥም ቀጠሮ እየተመላለሱ እንዲጉላሉ በማሰብ እንዲሁም የፍርድ ሂደቱን ስርዓት በማጣመም ከፍትህ አካላት የአሰራር መርህ ውጭ በሆነ መልኩ ፍትህን ሲያዛበ ነበር፡፡ የጥፋተኝነት ውሳኔ ለማሰጠት በማሰብ የተፈበረኩ እና የሀሰት ማስረጃዎችን ያቀርብ ነበር ብላለች፡፡ ሰርካለም በተለየ መልኩ ቴዎድሮስ ባህሩ በእራሱ አቅም እና እንደ መንግስት ዓቃቤ ህግ እያወቀ ሆን ብሎ እና የያዘውን ስልጣን ለእኩይ ተግባር በማዋል በእርሷና በባሌቤቷ የክስ ሂደት ላይ የህግ የበላይነትን ሲያጣምም ቆይቷል በማለት ውንጀላ አቅርባበታለች፡፡ እ.ኤ.አ በ2011 ባህሩ በባለቤቷ ላይ መሰረተ ቢስ ክስ በመመስረት፣ የሀሰት ማስረጃ እና የሀሰት ምስክር በማቅረብ እውነታውን እያወቀ ሆን ብሎ ሲያጣምም ነበር በማለት ወንጅላዋለች፡፡ ሰርካለም ውንጀላዋን በመቀጠል ባህሩ እስክንድርን የግንቦት ሰባት ድርጅት አመራራ በመሆን ወጣቶችን እየመለመለ ለሽብር ጥቃት ሲዳርግ ነበር ብላለች፡፡ ባህሩ ይህንን ውንጀላ ለማስተባበል የሚያስችል ምንም ዓይነት ማስረጃ ለማቅረብ አልቻለም፡፡ ሆኖም ግን የሸፍጥ ስራውን ለማከናወን ከዳኞች ጋር የሸፍጥ ዱለታ በማካሄድ ጥፋተኛ እንዲባል አስደርጓል፡፡ ሰርካለም ባህሩ እና ብርሀኑ ወንድምአገኝ የተባሉ ሁለት ዓቃብያነ ህጎች በግል የቤተሰቦቿን ንብረቶች፣ ቤቶቻቸውን፣ መኪኖቻቸውን እና ሌሎችን የግል መጠቀሚያ ቁሳቁሶችን ጨምሮ ከህግ አግባብ ውጭ እንዲነጠቁ በማድረጉ ሂደት ላይ ተባባሪ ነበሩ በማለት ውንጀላ አቅርባባቸዋለች፡፡ ባህሩ እያወቀ ስልጣኑን ከህግ አግባብ ውጭ በመጠቀም ሆን ብሎ እና ሌሎችን የኢትዮጵያን የነጻውን ፕሬስ ጋዜጠኞች ለማጥቃት እንደ ሰርካለም አባባል ዓለም አቀፍ የፕሬስ አሸናፊ ተሸላሚ የሆኑትን እነ ርዕዮት ዓለሙ፣ ውብሸት ታዬ እና ሌሎችም ፍትሀዊ ዳኝነት እንዳያገኙ በማድረግ ደባ ፈጽሟል ብላለች፡፡ ሰርካለም በቴዎድሮስ ባህሩ ላይ ያቀረበችው ውንጀላ በተለይም የህግ የበላይነትን ከማስጠበቅ አኳያ እና የመንግስት ዓቃብያነ ህጎች ንጹሀን ዜጎች የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ሰለባ እንዳይሆኑ በመከላከል ሂደት ላይ የሚጫወቱትን ቁልፍ ሚና በሚመለከት በርካታ የህግ ጥያቄዎች እንዲነሱ አድርገዋል፡፡ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ህግ ዓቃብያነ ህጎች የሰብአዊ መብት ጥበቃ ንቁ ተከላካይ መሆን እንዳለባቸው እና የአገር እና ዓለም አቀፍ ህጎች ታማኝነት እና የሰብአዊ መብት መርሆዎች በከፍተኛ ደረጃ መጠበቅ እንዳለባቸው ይጠይቃል፡፡ ዓቃብያነ ህጎች ለፍትሀዊ ዳኝነት ሂደት እና ለፖለቲካ ዓላማ ሲባል ኃላፊነቶቻቸውን በአግባቡ ሳይወጡ የሚቀሩ ቢሆን የህግ የበላይነት መርሆዎችን ብቻ አይደለም እየጣሱ ያሉት፣ ሆኖም ግን ቆመንለታል የሚሉትን የፍትህን ጠቅላላ መጨንገፍ የሚያመላክት ስለሆነ የእነርሱ መኖር በእጅጉ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ሁለቱም ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ እና ዓለም አቀፍ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ስምምነቶች/ሲፖመስ (ዩናይትድ ስቴትስ ሲፖመስን በኢትዮጵያ ህገመንግስት አንቀጽ 13(1)) ላይ የተቀመጠውን “እያንዳንዱ ሰው በነጻ እና ገለልተኛ በሆነ የፍትህ አካል ችሎት ፍትህን የማግኘት እና የመደመጥ መብት እንዳለው እና ማንኛውም በግለሰቦች ላይ የሚመሰረትን የወንጀል ክስ ለመከላክል መብት እንዳለው የሚደነግገውን እና እ.ኤ.አ በ1992 ያጸደቀችውን፣(ሰፖመስ በአንቀጽ 14፡ የአፍሪካ ቻርተር ሰዎች እና በህዝቦች መብቶች (አቻሰህመ) ከአንቀጽ 6-8 የተዘረዘሩትን መመልከት ይቻላል)፡፡ የሮማ ዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይሲሲ) የወንጀለኞች ፍትህ የማግኘት መብት መርሆዎችን በግልጽ ያስቀምጣል (ከአንቀጽ 22-33) እና የፍትሀዊ ዳኝነት (ከአንቀጽ 62 – 67) በግልጽ ተመልክቷል፡፡ ለሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ሰላባዎች ካሳ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ህግ እና ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ህግ መጣስን አስመልክቶ (በተባበሩት መንግስታት የጠቅላላው ጉባኤ የዴሴምበር 16/2005 ጉባኤ ውሳኔ ቁጥር 60/147) እንደሚገልጸው መንግስታት በሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ወንጀል ፈጽመዋል በሚል የተጠረጠሩትን እና ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶችን ጥሰዋል የሚባሉትን መብት ደፍጣጮች የመዳኘት ኃላፊነት እንዳለባቸው በግልጽ ተደንግጓል፡፡“በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን ፈጽመው በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ተደብቀው በሚገኙ የኢትዮጵያ ወንጀለኞች ላይ ጥቆማ እንዲደረግ የቀረበ ጥሪ፣ እ.ኤ.አ ጃንዋሪ 2012 “የአፍሪካ አምባገነኖች፡ የትም ሮጠው ሊያመልጡ አይችሉም፣ የትም ተደብቀው ሊያመልጡ አይችሉም!“ በሚል ያቀረብኩት ፅሁፍ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶችን ደፍጥጠው ወደ ውጭ በመኮብለል በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ እየኖሩ የሚገኙትን መብት ደፍጣጮች አሳድዶ በማደን ስማቸውን እና ያሉበትን ልዩ ቦታ ለአሜሪካ ባለስልጣኖች ጥቆማ በመስጠት የዜግነት ግዴታዎቻችሁን እንድትወጡ እና የወገኖቻችሁ ደም ደመከልብ ሆኖ እንዳይቀር የሚል ጥሪ አስተላልፌ ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ እየተጠናከሩ በመጡት ምርመራዎች እና የሰብአዊ መብቶችን በመደፍጠጥ ወደ አሜሪካ በማታለል እና በህገወጥ መልክ የገቡትን ወንጀለኞች አሳድዶ በመያዝ በተለይም ለአሜሪካ ባለስልጣኖች ለህግ ማቅረብ በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡ እነዚህን የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ለዜግነት እና ለጉምሩክ አስፋጻሚ ፣ ለአገር ውስጥ ደህንነት ጉዳይ ፣ ለሰብአዊ መብት ደፍጣጮች እና ለጦር ወንጀለኞች ቡድኖች እና ለብሄራዊ ደህንነት የምርመራ ክፍል መ/ቤቶች መጠቆም ትችላላችሁ፡፡ ያሜሪካ መንግስት የጦር ወንጀለኞች፣ የዘር ማጥፋት ወንጀለኞች፣ የአሰቃዮች እና ሌሎች በዓለም ላይ ግጭትን ሊያመጡ የሚችሉ የሰብአዊ መብቶች ደፍጣጮች ኮሚሽን መደበቂያ ገነት እንዳትሆን ለመከላከል ጠንካራ ምርመራዎችን ያደርጋል፡፡ የውጭ ተጠርጣሪ የጦር ወንጀለኞች፣ አሰቃዮች እና የሰብአዊ መብት ድፍጣጮች ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የግዛት ክልል ውስጥ መኖራቸው በሚታወቅበት ጊዜ የምርመራ ቡድን ሙሉ የህግ ኃይሉን እና ስልጣኑን በመጠቀም ለማጣራት፣ ለመዳኘት እና በሚቻልት ሁኔታ ሁሉ እንደዚህ ያሉ ሰብአዊ መብት ደፍጣጮችን ከአሜሪካ ለማስወገድ ጥረት ያደርጋል፡፡ ባለፉት አስርት ዓመታት ያሜሪካ መንግስት በመቶዎች በሚቆጠሩ ከሰብአዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ መልኩ በወንጀለኛ እና/ወይም ስደተኞች ምርመራ ላይ ስኬታማ ሆኗል፡፡ የዚህ ቡድን የዳታ መሰረት በርካታ የታወቁ ተጠርጣሪ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮችን ስም ዝርዝር አካትቶ ይዟል፡፡ የዳታ ቋቱ የታወቁ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ለማድረግ ጠቃሚ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ዜጉአ ወደ100 አካባቢ ከሚሆኑ ከተለያዩ አገሮች የመጡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ላይ ክትትል በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ባለፉት ስምንት ዓመታት በመቶዎች የሚቆጠሩ ከሰብአዊ መብት ድፍጣጮች እና ከተለያዩ የወንጀለኛ እና/ወይም ከስደተኝነት ጋር በተያያዘ መልኩ በቁጥጥር ስር አውሎ ሌሎች በመቶዎች የሚቆጠሩትን ታዋቂ ወይም ተጠርጣሪ ግለሰቦችን ደግሞ ከዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በማስወጣት ወደ አገራቸው እንዲጋዙ አድርጓል፡፡ በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን የፈጸሙ እና በአሜሪካ እየኖሩ ያሉ የኢትዮጵያወንጀለኞች ለምርመራ ለዜጉአ ሰመደጦወቡ ጥቆማ መቅረብ ይኖርባቸዋል፣ በኢትዮጵያ በሰው ልጆች ላይ የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ድፍጠጣዎች እና የጦር ወንጀሎች መረጃዎች በተሟላ ሁኔታ ተተንትነው እና ተጠቃለው ተዘጋጅተው ተይዘዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2007 በኢትዮጵያ ያለው የህወሐት ገዥ አካል አጣሪ ኮሚሽን ባቀረበው ዘገባ መሰረት የ2005 ድህረ ምርጫ ውዝግብን ተከትሎ በአገሪቱ ውስጥ ከህግ አግባብ ውጭ በዘፈቀደ 193 ሰላማዊ ዜጎች የተገደሉ፣ ሌሎች 763 ሰዎች ቁስለኛ እና ሌሎች ወደ 30 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ ከህግ አግባብ ውጭ ለዘፈቀደ እስራት የተዳረጉ መሆናቸውን በተጨባጭ መረጃ አስደግፎ አቅርቧል፡፡ በዚህ የወንጀል ድርጊት ውስጥ ተዋንያን የነበሩ 237 ግለሰቦች ታውቀዋል፣ እንዲሁም ከዚሁ ጋር ንክኪ ያላቸው ተጠርጣሪዎች ተለይተዋል፡፡ እ.ኤ.አ ዴሴምበር 2003 በኢትዮጵያ በጋምቤላ 424 ንጹሀን ዜጎች ከህግ አግባብ ውጭ በዘፈቀደ ለህወሐት ታማኝ በሆኑ የደህንነት ኃይሎች ተገድለዋል፡፡ በኦጋዴን ላይ በሚደረገው ጭቆና እ.ኤ.አ በ2008 ሂዩማን ራይትስ ዎች ባወጣው ዘገባ መሰረት “150 የተገደሉ ግለሰቦች“ እና ሌሎች 37 ተጨማሪ ሰላማዊ ዜጎች በጦር ወንጀለኝነት ተጠያቂ በሚሆኑ በኢትዮጵያ ወታደሮች ትዕዛዝ እና ተሳታፊነት በተደረገ ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ስም ዝርዝር ተመዝግቦ ተይዟል፡፡ ይህንን የጦር ወንጀል የሚያወቁት ወይም ደግሞ እንደዚህ ያለ ወንጀል እንደሚፈጸም ማወቅ ያለባቸው ሆኖም ግን ምንም ዓይነት እርምጃ ያልወሰዱ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እና የሲቪል ባለስልጣኖች እንደ ትዕዛዝ ሰጭነታቸው በወንጀሉ ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ የተስፋፋው እና ስልታዊ በሆነ መልክ በሶማሊ ክልል በእያንዳንዱ መንደር ላይ እየተካሄደ ያለው ከህግ አግባብ ውጭ በዘፈቀደ የሚደረገው ግድያ፣ ማሰቃየት፣ አስገድዶ መድፈር፣ እና አፍኖ መሰወር በስልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ ገዥ አካል የመጨረሻውን ተጠያቂነት ሊወስድ የሚችልባቸው እና ሊጠየቅባቸው የሚችሉ በሰው ልጆች ላይ እየፈጸማቸው ያሉ ወንጀሎች ጠንካራ ማስረጃዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ከብዙው በጥቂቱ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ተደብቀው በሚገኙ የኢትዮጵያ ወንጀለኞች ላይጥቆማ ለማድረግ ለምን ተነሳሽነት ማሳየት እንዳለብን፣ ምናልባትም ባለፉት በርካታ ዓመታት በኢትዮጵያውያን/ት ዘንድ በተደጋጋሚነት ሲቀርቡልኝ ከነበሩት ጥያቄዎች ውስጥ “እኔ እንደ ግለሰብ በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብት ለማሻሻል ምን ማድረግ እችላለሁ?“ የሚሉ ነበሩ፡፡ ኢትዮጵያውያን/ት የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ለአሜሪካ የዜጎች እና ጉምሩክ አስፈጻሚ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች እና የጦር ወንጀለኞች ቡድን ለምን መጠቆም እንዳለባቸው በማስረጃ እና በመረጃ የተደገፉ በርካታ ምክንቶች አሉ፡፡
1ኛ) በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ወንጀል ሰርተው በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ሄደው ተደብቀው የሚኖሩትን መጠቆም በምንም ዓይነት ሊታለፍ የማይችል በቀጥታ የጥቃቱ ሰለባ የሆነው የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ/ት ወይም ደግሞ በሌሎች ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመ ለመሆኑ እውቀቱ ያለው የሞራል ሰብዕና ተግባር በመሆኑ ነው፡፡ በሰው ልጆች ላይ እንደዚህ ያለ ወንጅልን የሚፈጽሙ ወንጀለኞች መጋለጥ እና ከአሜሪካ ህብረተሰብ መካከል መወገድ ይኖርባቸዋል፡፡
2ኛ) በእነዚህ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች ላይ ጥቆማ ማካሄድ በኢትዮጵያ በስልጣን ወንበር ላይ ተጣብቀው ላሉት ባለስልጣኖች አሜሪካ የሰብአዊ መብትን እየደፈጠጡ ለሚመጡ ወሮበላ ወንጀለኞች የሀሰት እና የተጭበረበረ የጥገኝነት ቪዛ እያመጡ በሰላም ለመኖር አሜሪካ በተጨባጭ መደበቂያ ገነት የማትሆን መሆኗን የሚገልጽ ጠንካራ መልዕክት ያስተላልፋል፡፡ እነዚህ ወንጀለኞች አሜሪካ ቢገቡ እንኳ ወደ እስር ቤት እንደሚጋዙ ዝግጅት ማድረግ አለባቸው ምክንያቱም ለፖሊስ ጥቆማ በማቅረብ ለፍትህ ይቀርባሉ፡፡
3ኛ) በዚህ ጥቆማ ላይ የሚደረግ ሰፊ የሆነ ተሳትፎ ኢትዮዮጵያ በስልጣን ላይ ላሉት የገዥው አካል አባላት አስቀያሚ የሆነ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈጽመው ወደ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በመሄድ አሜሪካንን የሚረግጡ ከሆነ በአሜሪካ ባንኮች የደለበውን የባንክ ሂሳቦቻቸውን ብቻ አይደለም የሚያጡት፣ ሆኖም ግን የእራሳቸውን ነጻነትም እንደሚያጡ ጠንካራ የሆነ መልዕክት ያስተላልፋል፡፡ የመጨረሻዎቹን ቀናት በአሜሪካ እስር ቤቶች ሊያሳልፉ እንደሚችሉ ዝግጅት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
4ኛ) የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ደፍጣጮች አሜሪካ የእነርሱ መደበቂያ ገነት ዋሻ እንደማትሆን እሰካመኑ ድረስ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሰብአዊ መብቶችን ጥሰት ከመፈጸም እኩይ ተግባራት ይታቀባሉ፡፡ ሁሉም የገዥው አካል አመራር አባላት በሚባል መልኩ እና የእነርሱ ታማኝ ሎሌዎች በአሁኑ ጊዜ ነገሮች በዚህ ሁኔታ የሚቀጥሉ ከሆነ እና በኢትዮጵያ ለውጥ ከመጣ ወደ አሜሪካ የሚያደርጉትን የፍርጠጣ ጉዞ በመሰረዝ ወደ ሌላ አዲስ ቦታ ጉዞ እንደሚያርጉ ይታመናል፡፡ እንደገና ቢያስቡ የተሻለ ይሆናል!
በኢትዮጵያ ወንጀል ፈጽመው ወደ አሜሪካ በመሄድ ተደብቀው የሚኖሩወንጀለኞች እንዳሉ እያወቁ አለመጠቆም እና ለፍትህ እንዲቀርቡ አለማድረግእና እንዲኖሩም መፍቀድ በእራሱ ወንጀል ነው፡፡ ወንጀል ከተሰራ በኋላለወንጀለኞች ተባባሪ መሆን ወንጀል ከመስራት ጋር እኩል ነው፡፡ እነዚህ በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን ፈጽመው በአሜሪካን አገር ተደብቀው የሚገኙ ወንጀለኞች ፍትህ እንደዘገዬ ባቡር መሆኑን ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ የጥቃት ሰለባዎች ለጥቂት ጊዜ መታገስ ይኖርባቸዋል፣ ሆኖም ግን በመጨረሻው ሰዓት ፍትህ በሙሉ ኃይሉ ታጅቦ ይመጣል፡፡ እ.ኤ.አ ሜይ 23/2014 ከፈለኝ ዓለሙ ወርቁ የተማረው ይህንን ሀቅ ነው፡፡ ያ በአሜሪካ ግልጽ ተደብቆ እየኖረ ያለው እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ/ት የሰብአዊ መብት ደፍጣጭ በየዕለቱ ሊማርበት የሚገባ አብይ ትምህርት ነው፡፡ ያ ሁኔታ አሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብትን እየደፈጠጡ ያሉ እና አሜሪካ ሄዶ ከመደበቅ ይልቅ ወደ ሌላ አዲስ ቦታ ለመሸሽ ዕቅድ የሚያወጡት ወንጀለኞች ሊማሩበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡
Ewnetu Taye

No comments:

Post a Comment

wanted officials