ምእራብ ሸዋ ዞን በኦሮሚያ ክልል በግንደበረት ወረዳ በተማሪዎች እና በወያኔ የፖሊስ ሃይሎች መካከል በተከሰተ ግጭት አንድ  
ተማሪ ሞቶ አራት መቁሰላቸውን የአከባቢው ምንጮች ገልጸዋል.  
ከትላንትና ጀምሮ ሲንከባለል የመጣው ግጭት ከዚህ ቀደም በኦሮምያ ክልል ውስጥ ከተነሱ የተማሪዎች አመጽ ጋር ተያያዥነት ያለው እና ጥያቂውም  
የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እና የሞቱ የኦሮሞ ተማሪዎች ጋር የተያያዘ ሲሆን ዛሬ በቀጠለው ተቃውሞ ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች እና  
የወረዳው ነዋሪ በጋራ ሰልፍ በመውጣት ቁጣቸውን የገለጹ ሲሆን አስተዳደሩ ድረስ በመሄድ ድምጻቸውን ሲያሰሙ የፌዴራል  
ፖሊስ በመምጣት የበተናቸው ቢሆንም  
ቀኑን ሙሉ በከተማው ከባድ ረብሻ እንደነበር እና ከቆሰሉ ተማሪዎቹም አንዱ መሞቱን የወረዳው ነዋሪዎች ተናግረዋል ሲሉ  
ምንጮቹ ጠቁመዋል.  
በነገው እለት የ 12 ኛ ክፍል መሰናዶ ፈትና ከወሰደ በኋላ የተገደለውን ተማሪ ለመቅበር ይወጣል የተባለው ሕዝብ ተቃውሞ  
እንዳያሰማ የወረዳው እና የከተማው ባለስልጣናት በመስጋት ፖሊሶች ያሰፈሩ ሲሆን ሕዝቡ ቁጣው እንዳልበረደ እና በስፋት  
ተቃውሞው እንደሚቀጥሉ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል.