Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, June 20, 2014

በአዋሳ ፖሊስ የአንድነት ስራ አስፈፃሚ አባልንና በቅስቀሳ የትስማሩ አባላቶቹን አሰረ፤ እስከአሁን ቃላቸውን እንዲሰጡ አልተደረገም፡፡ – የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት

“እስሩ ቅስቀሳውን አያስተጓጉለውም”
አንድነት ፓርቲ በአዋሳ ከተማ የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ የፓርቲው ብሄራዊ ምክር ቤት አባልና በአንድነት ፓርቲ የሴቶች ጉዳይ ስራ አስፈፃሚ የሆኑትን ወ/ሪት እልፍነሽ ከበደን የተሳፈሩበትን ሚኒባስ በማስገደድ ወደ ምስራቅ ክ/ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል ፡፡ ሀላፊዋ ከጠዋቱ 4፡00 ጀምሮ በጣቢያው ታስረው የሚገኙ ሲሆን በምን ምክንያት ቁጥጥር ስር እንደዋሉና እስከመቼ በእስር እንደሚቆዩ ለማወቅ እንዳልቻሉ ገልፀዋል ፡፡ የጣቢያውን ሀላፊ ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ በስብሰባ ምክንያት ሊሳካ አልቻለም፡፡
በሌላ በኩል አንድነት ፓርቲ እሁድ ሰኔ 15 ቀን 2006 ዓ.ም “የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት” በሚል መሪ ቃል በሃዋሳ ከተማ ለሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ በራሪ ወረቀት በማደልና ፖስተር በመለጠፍ ላይ የነበሩት የአንድነት ፓርቲ አመራርና አባላት ታሰሩ፡፡ ሲዳማ ዞን የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ ሲዳ ኃይሌ እንዲሁም ከማዕከል ለሰልፉ እገዛ ለማድረግ ከሄዱ የፓርቲው አባላት መካከል አቶ ኃይሉ ግዛውና ወጣት ደረጄ ጣሰው ላይ ህገወጥ እስር መፈፀሙን ከስፍራው ለፍኖተ ነፃነት የደረሰው መረጃ አመላክቷል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ባለስልጣናት ሰልፉን ለማደናቀፍ የሚያደርጉት የተቀነባበረ እንቅስቃሴ ያልበገራቸው ሌሎቹ የቅስቀሳ ቡድኑ አባላት የተጠናከረ ቅስቀሳ ለማድረግ መዘጋጀታቸው ታውቋል፡፡
አስካሁን ድረስ በቅስቀሳ ወቅት የተያዙ የአንድነት አባላት እስከአሁን ቃላቸውን እንዲሰጡ አልተደረገም፡፡1511415_655210944563843_5317006338479666664_n
10250321_655210947897176_4657445496451664582_n

No comments:

Post a Comment

wanted officials