በሰላም በር ከተማ ቁጫ ወረዳ 12 የአንድነት አባላት ታሰሩ
ፍኖተ ነፃነት
በራሪ ወረቀት በማደልና የመኪና ላይ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ የነበሩት 12 የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት፣ በቁጫ ወረዳ፣ ሰላም በር ከተማ በሕግ ወጥ መንገድ ታሰሩ። የቁጫ ወረዳ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች፣ ጌታቸው ኮይራ፣ ኢሳያስ ሉቃስ፣ ጋሰላ ጋሌቦ፣ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ሰልፉን ለማስተባበር የሄዱት ስንታየሁ ቸኮል፣ ደረጄ ጣሰው፣ ኃይሉ ግዛው እና የቅስቀሳ መኪናዉን ሲያሽከርክር የነበረዉ ነጻነት ዘገየን ጨምሮ 12 የፓርቲዉ አመራሮችና ባላትን ፖሊስ በሕገ ወጥ ሁኔታ አስሮ ቃላቸዉን እንዲሰጡ በመጠየቅ ላይ መሆኑን ከስፋራዉ የደረሰን ዜና ያመለክታል።
የታገቱ የአንድነት ቀስቃሾች፣ የወረዳው ፖሊስ ቃል እንዲሰጡና እና ብሄራቸዉን እንዲናገሩ ለማስገደድ ቢሞክሩም፣ ሁሉም ቃል ለመስጠጥ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። «ብሄራችን ኢትዮጵያዊ ነው» በማለታቸው ፖሊስ ታሳሪዎቹን ምን ማድረግ እንዳለበት የበላይ ትእዛዝ እየጠበቀ መሆኑን፣ ታጋቶቹ ከመርማሪዉ ተረድተዋል።
በተያያዘ ዜና አብዛኞቹ የቁጭ ወረዳ የካቢኔ አባላት፣ ቢሯቸዉን ለቀዉ በአስቸኳይ ሰብሰብ ላይ እንደሚገኙ የታወቀ ሲሆን፣ የአካባቢው ሕዝብ በመንግስት እየደረሰበት የሚገኘዉን መጠነ ሰፊ ግፍ፣ በአደባባይ ለመቃወም በነቂስ እንደሚወጣ መገመቱ የካቢኔ አባላቱን ሲያሰጋ እንደቆየ.....

No comments:
Post a Comment