Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, June 28, 2014

የደሞዝ ጭማሪ እንደሚኖር መነገሩን ተከትሎ የእቃዎች ዋጋ ወደ ላይ እየወጣ ነው

የደሞዝ ጭማሪ እንደሚኖር መነገሩን ተከትሎ የእቃዎች ዋጋ ወደ ላይ እየወጣ ነው

ሰኔ ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :
-አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ በሃምሌ ወር መጨረሻ የደሞዝ ጭማሪ ይኖራል በማለት ከተናገሩ በሁዋላ ደሞዙ ሳይለቀቅ፣ የቤት ኪራይ እንዲሁም የምግብ እና የአላቂ እቃዎች ዋጋ ጭማሬ እያሳየ ነው።
ጭማሪው በመላ አገሪቱ የሚታይ ሲሆን በአንዳንድ እቃዎች ላይ ከፍተኛ የሚባል ጭማሪ እየታየ ነው።
መንግስት ስለጭማሪው ተጨማሪ ማብራሪያ ባይሰጥም፣ ነጋዴውና ቤት አከራዮች ጭማሪ በማድረጋቸው የደሞዙን ጭማሪ ለማየት በሚጓጓው ሰራተኛ ላይ ፍርሃት እንዲነግስ አድርጓል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials