ስደተኞችን አስገድዶ በአውሮፕላን የሚጭነው የኖርዌይ ኢሚግሬሽን ፖሊስ ለፍርድ ሊቀርብ ነው።
ባለፈው አመት አስገድዶ ሰዎችን በአውሮፕላን መጫን ጉዳይ፣ አንድን ሰው እንዴት በግዴታ እንዳይወሰድ ማድረግ እንደሚቻልና በመንግስት ስለሚያስከትለው የህግ ተጠያቂነት እዚሁ ፌስ ቡክ ላይ ጽፌ ነበር። ግንቦት 22 ቀን 2014 ይሄው ነገር በተግባር ታየ።
በአለም አቀፍ ህግ አንድ ልኡዋላዊ ሃገር ዜጎች ያልሆኑ ህገ ወጥ ነዋሪዎችን በግዴታ ወደ ሃገራቸው የመላክ መብት አለው።
ነገር ግን ይህ አስገድዶ የመላክ መብት አስገዳጅ ቅድመ ሁኔታዎችም አሉት።
1. ከሃገር የማስወጣትና የመጓጓዣው ሂደት ኢ-ሰብዓዊ መሆን የለበትም
2. የአንድ ሃገር ሰዎችን በጅምላ ማባረር ክልክል ነው “collective expulsions is prohibited” – European Court of Human Rights, Article 4 of Protocol No. 4
3. ሃገራቸው ዜጎቼ ናቸው ብሎ ለመቀበል መስማማት አለበት (Return Agreement)
4. ሌላው ዋነኛው ተቀባዩ ሃገራቸው በተመላሾች ላይ ኢ-ሰብዓዊ ብቀላ የማያደርግ መሆን አለበት። (European Court of Human Rights Article 3)

ሰሞኑን የተፈጠረው ነገር አንድ ናስር ካኔ የተባለ የ38 ዓመት የኢራቅ ዜጋን ወደ ሃገሩ ለመሸኘት እጁ በካቴና ታስሮ በሶስት የሲቪል ፖሊስ ታጆብ አውሮፕላኑ በር ላይ ሲደርስ እጁ የታሰረ ሰው በአየር መጓዝ ስለሚከለከል ካተናውን ውስጥ ሳይገቡ ይፈቱለታል። ወንበሩ ላይ ያስቀምጡታል። አውሮፕላኑ ውስጥ ሌሎችም ተሳፋሪዎች ገብተው በየቦታቸው ተቀምጠው ነበር። አስተናጋጆቹ ቀበቷችሁን እሰሩ ብለው ትዕዛዝ ሰጥተዋል። ፖሊሶቹ ቀበቶውን አስረውለት በየቦታቸው ሲቀመጡ ቀበቶውን ፈትቶ ኡኡኡ በማለት የዋይታ ድረሱልኝ ጩኸቱን ጀመረ ካፕቴን ይርዱኝ Captain Help Me .. Help Me!! በማለት በጠበጠው። ተሳፋሪው ተረበሸ። ፖሊሶቹ ድምጹን ለመቀነስ ተነስተው ተረባረቡበት። በዚህ ወቅት አፉንና አንገቱን በመያዛቸው ካፕቴኑ አራቱንም ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ አዘዘ። በህግ የሰውን አንገት መያዝ የተከለከለ ነው። በህጉ መሰረት ፖሊስ በአውሮፕላን ውስጥ በጉልበት ሰውን የመያዝ ስልጣን የለውም። ይሄን የማድረግ መብት ያላቸው በአውሮፕላኑ ውስጥ በሚሰሩት ብቻ ናቸው። ከአውሮፕላኑ ከወረደ በኋላ ፖሊስን በመክሰሱ ፖሊስ ራሱ በምርመራ ላይ እንደሆነ ዳግብላደት የተባለው ጋዜጣ ዘግቧል። እኔም ናስር ካኔንን ስለነበረው ሁኔታ በዝርዝር እንዲነግረኝ አዋርቼው አንድ ሰው በቆራጥነት ከወሰነ በግዴታ ሰዎችን ማጓጓዝ በጭራሽ እንደማይቻል ነግሮኛል። ናስር ካኔን በዚህ መልኩ ከአውሮፕላን እንዲወርድ የተደረገው ለሶስተኛ ጊዜ ነው። በመሰረቱ በግዴታ ወደ ሃገሩ እንዲመለስ የሚገደደው ሰው ቀበቶ ለማሰር ፈቃደኛ አለመሆኑ ብቻ ከአውሮፕላኑ እንዲወርድ ያስገድደዋል። በናስር ካኔ ጉዳይ ፖሊስ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ የመኖሪያ ፈቃድ ያገኛል ማለት ነው።
by Girum Zeleke
No comments:
Post a Comment