በነፋስ ስልክ ላፍቶ ከተማ ቤቶች መፍረስ ጀመሩ፤ ፖሊስ እሪ ያሉ ወጣቶችን በቆመጥ ደበደበ
(ዘ-ሐበሻ) ነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ቀበሌ 1 በተለምዶ ስሙ ሃና ማርያም ጀርባ በሚገኘው ልዩ ስሙ ቃሬሳና ኮንቶማ ሰፈር ወደ 5000 የሚጠጉ ቤቶችን መንግስት ለማፍረስ ቀይ ቀለም የቀረባ ሲሆን ክፍለከተማውን ነዋሪውን አናውቃችሁም ትነሳላችሁ ማለቱን ተከተሎ ከ 1000 በላይ ኢትዮጵያውያን መድረሻ አጣን በሚል የኢሕ አዴግ ተለጣፊ ነው ወደ ሚባለው ወደ ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በማምራት ሰልፍ የወጡ ሲሆን፤ ኮሚሽነሩ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን መጥቶ ቪድዮ እስከሚቀርጽ ድረስ ከተበቁ በኋላ የሕዝቡን እሪታ “የሰብአዊ መብት መጣስ ጉዳይ መሆኑን ወደ ፊት የምናየው ይሆናል፤ ለአሁኑ ግን 10 ኮሚቴ መርጣችሁ ተነጋግረን መልስ እንሰጣችኋለን” ማለታቸውን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከአዲስ አበባ አስታውቀዋል።
የጉዳዩ ባለቤቶች ከአዲስ አበባ በፎቶ ግራፍ አስደግፈው በላኩልን መረጃ መሰረት በነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቤት ማፍረሱ የተጀመረ ሲሆን ሕዝቡ ካለምንም መተኪያ መድረሻ አታሳጡን እያለ እሪታውን ቢገልጽም ፖሊስ በአካባቢው መጥቶ ወጣቶችን በቆመጥ እንደደበበደ ታውቋል። በአካባቢው ያለው ውጥረት አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን ሕዝቡ እየተቃወመ መንግስትም ካለምንም መተኪያ “አናውቃችሁም፤ ከአካባቢው ልቀቁ” በሚል ማፍረሱን መቀጠሉን ነዋሪዎቹ ለዘ-ሐበሻ ጠቁመው፤ ወጣቶቹም ከፖሊስ ጋር ግብግብ ላይ መሆናቸውን ገልጸውልናል።
No comments:
Post a Comment