Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, June 23, 2014

ኢትዩጵያ ስለዐምሐራነት ስትፈርድ! Ami-hara means -Free people

ኢትዩጵያ ስለዐምሐራነት ስትፈርድ!


Image
ዐምሐራ የአንድ ጎሳ ወይም የብሄር መገለጫ ሳይሆን ዐምሐራ የኢትዩጵያዊነት መገለጫ ሲሆን ዐምሐራ ቃሉ ከግዕዝ ሲተረጎም “ዐም” ማለት ሕዝብ ሲሆን “ሐራ” ማለት ደግሞ ነጻ ማለት ሲሆን “ዐምሐራ” የሚለዉ የቃል ለቃል ትርጉም “ነጻ ህዝብ” ማለት ነዉ፡፡
ከኢትዩጵያ የዓለሙ መፋረጃ በሚል ርዕስ በንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደኢየሱስ በፃፈዉ መፅሐፍ ዉስጥ ስለ ዐምሐራ ህዝብ አጠራርና መጠሪያ ቃል የሰጣቸዉን ታሪካዊ እና ሃይማኖታዊ ትንታኔዎችና ገለፃ በተመለከተ እንዲህ አቅርቤላችኃለዉ ፡፡
አሹ ዋሴ ከጎንደር
“ዐምሐራ” የሚለዉ ቃል መልእክትና ትርጉም ባለዉ ምክንያት በኢትዩጵያ ምድር ለሚኖረዉ ለአብዛኛዉ የአገሪቱ ነባር ህዝብ የተሰጠ ትዉፊታዊ ስያሜ ነዉ፡፡ ቃሉ ከግዕዝ ተገኝቷል፡፡ በግዕዝ “ዐም” ማለት ሕዝብ ሲሆን “ሐራ” ማለት ደግሞ ነጻ ማለት ሲሆን “ዐምሐራ” የሚለዉ የቃል ለቃል ትርጉም “ነጻ ህዝብ” ማለት ሲሆን ይህም ትርጉም የእዉነተኛ ኢትዩጵያዊን ማንነት ከሚገልጹት ዓበይት ባሕሪያት መካከል አንዱ መሆኑን በግለጽ ያመለክታል፡፡ በአጠቃለይ ቅዱስ ኪዳነ ሃይማኖት እየተማሩና እያወቁ በፈቃዳቸዉ ሲገረዙና ሲጠመቁ ዐምሐራ ወይም ክርስቲያን እየተባሉ የእግዚአብሄር ህዝብ ሆኑ፡፡ በዚያ ጊዜ ያ ግለሰብ ዐምሐራ ሆነ ይባልል፡፡ ነፃ ወገን ሆነ ማለት ነዉ ሲሆን ነፃነቱም ከባዕድ አምልኮ ከዲያብሎስና ከሰዉ ተገዥነት ፤ከኃጢያት ቀንበር ከሞት ባለዕዳነት ተላቅቆ በእግዚአብሄር ልጅነት ለመኖር መብቃት ነዉ፡፡ ቋንቋዉን ፊደሉም ይኸዉ ኢትዩጵያዊ ህብረተሰብ ተስማምቶ የፈጠረዉ ዐምሐርኛ ወይ ኢትዩጵያኛ ይሆናል፡፡ ግዕዝ ራሱን የቻለ ፊደል ያለዉ የኢትዩጵያዉያን የመጀመሪያ እናት ቋንቋቸዉ መሆኑ በዓለም ሕዝቦች ዘንድ ሳይቀር በይፋ የታወቀ ነዉ፡፡
የዐምሐራዉ ኅብረተሰብ መነጋገሪዉ ያደረገዉ ቋንቋ ዐምሐርኛ ተብሏል፡፡ የዚህ ኅብረተሰብ የቃል ብቻ ሳይሆን የጽሕፈት መገናኛዉ ጭምር የሆነዉ ይህ ልሳን ግንድ ቢሆንም በጋብቻና በልደት እንደተዋሃደዉ እንደቋንቋዉ ባለቤት ሁሉ ዐምሐረኛም ብሄር አቀፍ ሁኖ በሃገሪቱ ዉስጥ በሚነገሩት አያሌና የተለያዩ በሆኑ ልሳናት ራሱን ሲያበለጽግ የኖረ ቋንቋ መሆኑ የቃላቱ ቤተ-መዛግብት ያረጋግጣል፡፡
ዐምሐራ የሚለዉ ስም ለምሳሌ አገዉ፤አርጎባ፤አፋር፤ኦሮሞ፤ጉራ፤ጋፋት፤ሓዲያ፤ ወላይታ፤ከምባት፤ ኩናማ ወይም ትግሬ እንደሚባለዉ በየጎጣቸዉና በየክልላቸዉ በየእምነታቸዉና በየቋንቋቸዉ ተለያይተዉና ተወስነዉ በየስማቸዉ እንደሚታወቁት ብሄሮች ወይም ሴማዉያን ፤ካማዉያን ያፌታዉያን ተብለዉ በመላዋ ምድር ተሰራጭተዉ እንደሚኖሩት እንደሦስቱ የሰዉ ዘር የትዉልድ ቅርንጫፎች ይህም ኅብረተሰብ “አንድ ነጠላ ጎሳ ወይም ነገድ ነዉ” ተብሎ ለእርሱ መለያና መታወቂያ ይሆን ዘንድ የተሰጠ ስያሜ አይደለም፡፡
በሌላ አገላለጽ ዐምሐራ የአንድ ጎሳ ወይም የአንድ ነገድ ወይም የአንድ ዘር ወገን አይደለም ማለት ነዉ፡፡ የቃሉ ፍቺ እንደሚያመለክተዉ ዐምሐራ በኢትዩጵያ ምድር የሰፈሩ ፤ከተለያዩ ጎሳዎች፤ነገዶች፤ዘሮች፤ ቋንቋዎች፤ባህሎችና ሃይማኖቶች የተዉጣጡ ወንዶችና ሴቶች እርስ በርሳቸዉ በመጋባት በሥጋ አንድ የሆኑበት ህልዉና ነዉ፡፡ በመንፈስ ቀድሞ በኪዳነ ልቦና ፤ቀጥሎ በኪዳነ ኦሪት፤ በመጨረሻም በኪዳነ ምህረት የክርስትና ተዋህዶ ሃይማኖት ከእግዚአብሄር በመወለድ ስጋቸዉና ነብሳቸዉ እነርሱም ሁላቸዉ በአንድ መንፈስ ቅዱስ ፍጽም አንድ የሆኑበት ህይዎት ነዉ፡፡ በአጠቃላይ ኢትዩጵያዊነት የተባለዉን ዘላለማዊ የህልዉና ዓላማ በሕያዉነት ከግብ ለማድረስ መለኮታዊዉ ጥሪ በፈቃዳቸዉ ተቀብለዉ ለእርሱ በጋራ ቃልኪዳን የገቡና ለሰዉም ሆነ ለዲያብሎስ ተገዢ ከመሆን ነጻ ወጥተዉ በእግዚአብሄር ሕገ መንግስት በእኩልነት ፍትሕ በመምራት እየተዳደሩ እንደ አንድ ቤተሰብ የሚኖሩበት ስርዓት ሃገር ነዉ፡፡
ዐምሐራዉ ከላይ እንደተገለፀዉ የእኒያ እያንዳንዳቸዉ የየግላቸዉ ብሔረኝነትና ጎሠኛነት ፤አምልኮና ልሳን በፈቃዳቸዉ ትተዉ ኢትዩጵያዊነትን ከፍጹም ሁለንተናዉ ጋር በፈቃዳቸዉና በሃይማኖት የተቀበሉ ፤ የኢትዩጵያ ጥንታዉያን ባለገሮች ኅብረተሰብ ስለሆነ ቀጥሎ ባለዉ ሐተታ እንደሚያብራራዉ ይህ ኅብረተሰብ እዉነተኛዉ ኢትዩጵያዉ ሆኖ ለመገኘት በቅቷል፡፡
እንግዲህ ማንኛዉም ግለሰብ ወንድ ሆነ ሴት በዚህ ኢትዩጵያዊነት አምኖ የዚህ ኅብረተሰብ አባል ለመሆን በፍጹም ነፃነት ፈቃደኛ ሲሆን የሚፈጸምለት ስርዓት አለ፡፡ ይኸዉም ከመንፈስ ቅዱስ ህይዎት የሚያበቃዉን ፀጋ የሚጎናጽፍበት ልዩ ስርዓት ነዉ፡፡ እርሱም በሃይማኖት እዉቀት በእዉነተኛ ንስሓ በክርስትና ጥምቀትና በቅዱስ ቁርባን ምስጢራ ይፈጽማል፡፡ ለዚያ ግለሰብ ይህ ስርዓት እንደተፈጸመለት ወዲያዉኑ ያ ግለሰብ ዐምሐራ ሆነ ፤ ክርስቲያ ሆነ ወይ ኢትዩጵያዊ ሆነ ማለት ነዉ፡፡ ዐምሐራነት በኃላ በስጋ ጋብቻ ጭምር እስኪዋሃዱበት ድረስ በቅድሚያ እንዲህ በመንፈስ የሚወለዱበት ስለሆነ ጎሳ ወይም ብሄር አለመሆኑ በዚህ ይታወቃል፡፡
በዚህ ጌዜ ያ ግለሰብ ኢትዩጵያዊነት በሚያስተማምን ቃል ኪዳን ለዘላዓለም የሚያጎናፅፈዉን ያን በመለኮታዊ ፀጋ የተገኘዉን ሰብዓዊ ነፃነት እንዳይቀዳጅ ከልክሎት ከኖረዉ ከጠባብ ብሄረኝነትና ከጎሠኝነት ከቋንቋና ከአምልኮ ባዕድ ቁራኝነት፤ ከአጓል አስተሳሰብም ቀምበር ተላቅቆ ከእዉቀት ብርሃን የወጣለትና የነፃነትን አክሊል የተቀዳጀዉ ኅብረተሰብ አባል ለመሆን የበቃ ይሆናል፡፡
ይህ ዐምሐራ የመሆን ምሥጢር ኢትዩጵያዊ ከመሆን ጋር የሚመሳሰልና እንደ ኢትዩጵያዊነት ሁሉ ያልተቋረጠ ትንግርታዊ ሂደት ያለዉ ሆኖ ኖርዋል፡፡ ዐምሐራ ሆነ ማለት ከላይ እንደተወሳዉ ኢትዩጵያዊ ሆነ እንደማለት ብቻ ሳይሆን በአሁኑ ጊዜ በፍጥረት ዓለሙ ዘንድ በይበልጥ እዉቅና እንዳገኘዉና በመጨረሻ ዘመን የሰዉን ዘር እንደገና አዋህዶ ፍጽም አንድ እንደሚያደርገዉ እንደ አዲስ ኪዳኑ ስያሜ ክርስቲን ሆነ ማለትም ነዉ፡፡ በዚህ መሠረት ዐይነተኛዉ (ማለት አማናዊዉ ወይም እዉነተኛዉ) ዐምሐራ ይህም ዐይነተኛዉ ኢትዩጵያዊ ወይም ዐይነተኛዉ ክርስቲያንም፤ ዐይነተኛዉ ዐምሐራ ነዉ፡፡እንዲህ ከሆነ እነዚህ ሶስት ስያሜዎች ማለትም ዐምሐራነት፤ ኢትዩጵያዊነት እና ክርስቲያንነት በምስጢርና በትርጓሜ ይዘታቸዉ አንድ ሌላዉን ሊተካ የሚችል የተመሳሳይነትና የተወራራሽነት ባሕርይ ያላቸዉ ቃላት መሆናቸዉ በግለጽ ይረጋገጣል፡፡
ለዛሬዉ ኢትዩጵያዊ ትዉልድ የዘር ግንድ የሆነዉ የጥንቱ የዐምሐራ ኅብረተሰብ የኢትዩጵያ ነባር ባለገሮች ከሆኑ ኀዳጣን (ቁጥራቸዉ አናሳየሆነ) እና ብዙኃን ( ቁጥራቸዉ በርካታ የሆነ) ብሄረሰቦች ተዉጣጥቶና ተዋሕዶ የተገኘ መሆኑ ከላይ ተመልክቷል፡፡
የዚህ ጥንታዊ ኅብረተሰብ አባሎች የሆኑት እንያ አባቶችና እናቶች ለቅዱስ ኪዳን አምላክ ለልዑል እግዚአብሄር ፈቃድ ራሳቸዉን በሐይማኖት በማስገዛት ዘላለማዊ በረከትና ፀጋ ለልጅ ልጆቻቸዉ እንደሚያቀዳጅ የተማመኑበት የኢትዩጵያዊነትን መሠረት በበለጠ አጽንተዉ ለመቀጠል በስምምነት የሠጡት ዉሳኔና ዉሳኔዉን በስራ ላይ በማዋል የፈጸሙት ገድል ለዚህ ግዳጃቸዉ ከከፈሉት መስዋዕትነት ጋር እጅግ ብልሆች ፤አርቆ አስተዋዩችና ቆራጦች ለመሆናቸዉ በቂ ማስረጃ ሆኗቸዋል፡፡
እስቲ ዛሬ የትኛዉ ኢትዩጵያዊ ነዉ ወየም ከላይ በጥቂቱ በተወሱትና ከየራሳቸዉ ጠባብ ብሄረኝነት ጋር ተቆራኝተዉ በሚገኑት ጎሳዎች ዉስጥ አባል ከሆነዉ ግለሰብ መካከል እንኳ ሳይቀር የትኛዉ ነዉ እንኳንስ ከአንድ ነጠላ ጎሳ ይቅርና ከሁለት ወይ ከሶስት ጎሳዎች ብቻ የተወልድኩ ነኝ በማለት በሙሉ አፉ ደፍሮ ሊናገር የሚችል? ማንም ሊኖር ከቶ አይችልም፡፡ ምክኒያቱም ያ ኢትዩጵያዊ ወይም የጎሳ አባል ወንድ ሆነ ሴት በወላጆቹ የትዉልድ ግንድ በኩል በጥቂቱ ወደ ኃላ ሄድ ብሎ አያቶቹን፤ የቅድማያቶቹንና የምንዝላቶቹን የዘር ሐረግ ቢስብ ራሱን የኅብረብሄር ፍሬ ማለት አያሌ ጎሳዎች የተዋሃዱበት ቅይጥ ፍጡር ሆኖ ያገኘዋል፡፡ ዐምሐራ ወይም ኢትዩጵያዊ ከሚያሰኙት ዓበይት ባሕሪያት መካከል ደግሞ ይህ የኅብረ ብሄር ፍሬነት አንዱ አይነተኛዉ ባህርይ መሆኑን በትኩረት መመልከት ነዉ፡፡
የዚህ እዉነት አማናዊነትና እርግጠኝነት ባሁኒ ጊዜ በኢትዩጵያ ምድር እንዲሁም በሃገር ዉስጥ በሚኖሩትና በዉጭ አህጉር ተበትነዉ በሚገኙት ኢትዩጵያዉንና ኢትዩጵያዊዉያን ዘንድ ሰፍኖ በሚታየዉ ሁኔታ ጎልቶና ገዝፎ ይታያል፡፡ ይህዉም ዓይነተኛዉ ( እዉነተኛዉ) የዐምሐራዉ ኅብረተሰብ ኢትዩጵያ በእግዚአብሄር መንግስትነት ስር ተዋህዳ የኖረች የማትከፋፈል አንዲት አካል መሆኑን በማመን በጎሳ ወይም በዘር መለያየትን የሚቃወም በመሆኑ ነዉ፡፡
እንዲያዉም ኢትዩጵያዊነት ከዚህ የበለጠና የመጠቀ የጠለቀ ፤የሰፋም ባህርይ አለዉ፡፡ ይኸዉም ለኢትዩጵያ እንዲሁም ላለፉትና ለዛሬዎቹ ወደፊቶቹም ኢትዩጵያንና ኢትዩጵያዉያት ብቻ ላይ ተለይቶና ተወስኖ የተሰጠ፤ እየተሰጠ ያለና የሚሰጥም አለመሆኑ ነዉ፡፡ ስለሆንም ዐምሐራን በመላዉ ዐምሐራ ወይም በሃገር አቀፍ ደረጃ አማራ ክልል ማለት ዐምሐራን ከመሠረታዊ የኢትዩጵያዊነት ባሕር አዉጥቶ እንደ ጎሣ ማስቆጠር የኢትዩጵያ የደም ጠላቶች በሚያዉጠነጥኑት ሴራና በሚያካሄዱት ዘመቻ ዉስጥ ተባባሪ ደጋፊና መሣሪያ መሆን በግለጽ አረጋግጦ የሚያሳይ የክህደትና የአመጽ ተግባር በመሆኑ ነዉ፡፡ ስለዚህ ዐምሐራ ኢትዩጵያዊነትን ሕያዉ ለማድረግ ለመጠበቅና ለማስፋፋት በድርጅታዊ ሆነ በብሄራዊ ደረጃ የሚታየዉን የተዛበ አሠራርና ጉዳይ የሚመለከታቸዉ ወገኞች በሙሉ በብሩቱ አስበዉበት ስለ እዉነተኛ ኢትዩጵያዊነት ዐምሐራ ማስተካከልና ማብቃት ይገባቸዋል፡፡
ኢትዩጵያ ለዘላለም በክብር ትኑር!!

No comments:

Post a Comment

wanted officials