ለርዕሰ መምሀራን፣ ምክትል ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የደመወዝ ጭማሪ ተደረገ
የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሠማ ጊዜያዊ ኮሚቴ ባገኘው መረጃ መሠረት ለርዕሰ መምሀራን፣ ምክትል ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የደመወዝ ጭማሪ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲቪል ሰርቪስ ኤጀንሲ በ14/9/06 ዓ.ም ለሁሉም ክፍለ ከተሞች በላከው ደብዳቤ እንዳስታወቀው ከሆነ የርዕሰ መምሀራን፣ ምክትል ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ደመወዝ ላይ ጭማሪ እንዲደረግ በዚህም የተነሳ ለምሳሌ መሪ ርዕሰ መምህር እና ከፍተኛ ሱፐርቫይዘሮች አሁን ከሚያገኑት ደመወዝ ከፍተኛ ጭማሪ ተደርጎ 7768 (ሰባት ሺህ ሰባት መቶ ስድሳ ስምንት) የኢትዮጵያ ብር እንዲከፈላቸው የተወሠነ ሲሆን መሪ ምክትል ርዕሰ መምህራን ደግሞ 5554 (አምስት ሺህ አምስት መቶ አምሳ አራት) ብር እንዲከፈላቸው ተወስኗል፡፡
የደመወዙን ጭማሪ አስገራሚ የሚያደርገው በአሁኑ ሠዓት ከመምህሩ በላይ በኑሮ ውድነቱ እየተሰቃየ ያለ የመንግስት ሠራተኛ እንደሌለ እየታወቀ መምህራንን ያገለለ የደመወዝ ጭማሪ ማድረግ እጅግ አሳዛኝ ሲሆን ይህንን የተመለከቱ አንዳንድ መምህራን ለኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሠማ እንደገለፁት ከሆነ መንግስት በመምህራን እና በትምህርት ጥራት ላይ እየፈፀመ ያለውን አሻጥር ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
ለርዐሰ መምህራኑ ደመወዝ መጨመሩ ተገቢ ሆኖ ሳለ ከ1200 ብር ጀምሮ እየተከፈለው ያለውን መምህር ችላ ማለት ከጀርባው ሌላ እኩይ አላማ እንዳለው ማሳያ ነው፡፡ መንግስት የመምህራኑን ድምፅ ለማፈን ከሚጠቀምባቸው ኃይሎች መካከል ዋነኞቹ የሆኑት ርዕሰ መምህራን እና ሱፐር ቫይዘሮች ሲሆኑ እነርሱን በማስደሠት መምህራኑን ደፍጥጬ እይዛለው የሚል ኋላቀር አስተሳሰብ ውስጥ እንደገባ ማሳያ ሆኗል፡፡
ክቡራን የኢትዮጵያ መምህራን ሆይ
ከዚህ የበለጠ ምንም አይነት መዓት አይመጣም ይህ ከጫካ ይዞት በመጣው አስተሳሳብ ሐገር እየመራ ያለን አምባገነናዊ መንግስት በጋራ እስካልታገልን ድረስ ከዝንብ ማር እንደማይጠበቅ ሁሉ ከወያኔም መልካም ነገር ስለማይጠበቅ መጪው ጊዜ አስፈሪ ነው ስለሆነም በጋራ ከመሞታችን በፊት ስለሐገራችን፣ ስለሙያችን፣ ስለእራሳችንና ስለቤተሠቦቻችን እንዲሁም ስለቀጣዩ ትውልድ ብለን ወያኔ ኢህአዴግን ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ተጠቅመን ልንቃወመው እና ወያኔን ከመርዳት ልንቆጠብ ይገባል፡፡

የታሪክ ተወቃሽ ከመሆን እንዳን
ክብር ለኢትዮጵያውያን መምህራን
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
ሠኔ 15/2006 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ክብር ለኢትዮጵያውያን መምህራን
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
ሠኔ 15/2006 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
No comments:
Post a Comment