Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, June 14, 2014

የትግራይ ብሄርተኝነት እንዴት ወደ ፋሽስት ስርዓትነት እያመራ እንደሆነ ለማሳየት እንሞክር (ክፍል 1) (ዶ / ር አሰፋ ነጋሽ)


የትግራይ ብሄርተኝነት እንዴት ወደ ፋሽስት ስርዓትነት እያመራ እንደሆነ ለማሳየት እንሞክር (ክፍል 1)  
(ዶ / ር አሰፋ ነጋሽ)
. የሰው ልጆች አብረው በማህበረሰብ ለመኖር ይቻላቸው ዘንድ ለአብሮ መኖር ፀር የሆኑ ምግባሮችንና ባህሪዎችን ማስቀረት መቻል አለባቸው  . አለበለዚያ ማህበራዊ ኑሮ ሊታሰብ አይችልም  . ሰውን ከእንሰሳየሚለየው ከስሜት ባሻገር የማሰብና የማመዛዘን ክህሎቱ ነው  ህሊና አንድ ሰው በጎና ክፉውን; መጥፎና ጥሩውን; ትክክለኛና ሃሰተኛውን ነገር ለይቶ እንዲያውቅ የሚያስችለውን ችሎታ ወይም ክህሎት አመልካች ነው.  የሰው ልጅ የማሰብና የማሰላሰል ልዩ ችሎታ ስላለው በሚኖርበት ማህበራዊ ስፍራ የሚከሰቱትን ነገሮች ሊገነዘብና ሊዳኝ ይችላል.  ልጅ ሲያድግ በጎውና ክፉውን እየለየ የሚያውቀው ከአሳዳጊ ቤተሰቦቹ, ከጎረቤቱ, በሚኖርበት አካባቢ ከሚገኙ ሰዎች, ተቇሞች, ትምህርት ቤት, መስጊድ , ቤተ ክርስቲያን ወዘተ ነው.  የህሊና ዳኝነትና ለሱ መገዛት መቻል የአንድን ሰው ነፃ መሆንና በራሱ ነፃነት በጎናክፉውን የመወሰን ችሎታን ያሳያል.  በጎሳ ብሄርተኝነት የተለከፈ አንድ ሰው አንደ ራስ - በቅ (self reliant) ሰው በራሱ ሀሳብና ፈቃድ ተመርቶ ማህበራዊ ህይወቱን ሊመራ አይችልም. በዚህ አይነት በጎሳ ብሄርተኝነት አይምሮአቸው የተመረዙ ሰዎች የግል ማንነታቸው መገለጫ የሆነውን እንደ ሰው የማሰብ ችሎታቸውን ለጎሳ መሪዎቻቸው አሳልፈው ስለሚሰጡ የአንድ በጎሳ ብሄርተኝነት አስተሳሰብ የተመረዙ ሰዎች በሙሉ የጎሳ መሪዎቻቸው የሚነግሯቸውን እየሰሙና እየተከተሉ እንደ አንድ ሰው ወይም እንደ ጎሳ መሪያቸው ማሰብ ይጀምራሉ.  ይህ ፈረንጆች "group thinking" የሚሉትና የአንድ አክራሪ የጎሳ ድርጅት ተከታዮች አንድ ወጥ የሆነ አስተሳሰብ (homogenization of thought) ተሸካሚዎች የሚሆኑበት ሂደት ነው.  በዚህ ምክንያት በአክራሪ የጎሳ አስተሳሰብ የተመረዙ ሰዎች በጎሳ መሪዎቻቸው ትዕዛዝ (ውሳኔ) ህይወታቸውን እንዲመሩ ይደረጋል.  የጎሳ መሪዎቹ የወደዱትን ይወዳሉ የጠሉትን ይጠላሉ.  የጎሳ መሪዎቹ የመረጡለትን ነገር ሁሉ አንድ ሰው ለመቀበል ይገደዳል.  ምን እንደሚያስብ; ከማን ጋር ቡና መጣጣት እንዳለበት; ከማን ጋር መወያየት; ማንን ማፍቀር ማንን መጥላት; በየትኛው የፖለቲካ ስብሰባ ላይ መሳተፍ ወይም አለመሳተፍ እንደሚገባው ወዘተ የጎሳ መሪዎቹ ይነግሩታል.  በዚህ አይነት የግል ማንነቱን ያጣ ሰው ይሆናል.  በአለም ላይ ሰዎች የጎሳ ብሄርተኝነትን, አክራሪ የሃይማኖት ፍልስፍናን ወዘተ በመሣሠሉ መርዘኛ አመለካከቶችን በሚያራምዱ ፍልስፍናዎች ምክንያት የህሊና ዳኝነት ችሎታቸውንም ሆነ ክህሎታቸውን አሽቀንጥረው የጣሉበት ሁኔታ እንደነበረ ታሪክ ዘግቧል.  ለምሳሌ በናዚ ጀርመን ውስጥ ሰዎች እንደ ሰው ለህሊናቸው መገዛትን አቁመው ህሊና ቢስ በመሆን በጥላቻ የሰከሩ መሪዎቻቸውን እነ ሂትለርን; በጣሊያን እነ ሞሶሎኒን በጭፍን የተከተሉበት ሁኔታ እንደነበር በ ሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት አይተናል.  በዚህ ወቅት በናዚ ፍልስፍና መስፋፋት የተነሳ ብዙ ጀርመኖች ህሊናቸውን ስተው የሂትለር ፖርቲ ደጋፊና አጫፋሪ ሆነው ስለነበር ከብዛኞቹ የጀርመን ተወላጆች ሰው የሚያሰኛቸውን የህሊና ዳኝነት ክህሎት አሽቀንጥረው በመጣል የግል ማንነታቸውን አጥተው የናዚን ፋሽስት የፖለቲካ ፍልስፍና ስርዓት ተከታዮችና አቃፊ ደጋፊዎች ሆነው ነበር.  የናዚም ሆነ የፋሽስት አክራሪ የጎሳ ብሄርተኝነት ተከታዮችን ከሰውነት ተራ በመውጣት የግለሰብ ማንነታቸውን አጥፍቶ እንደ እንሰሳት መንጋ የአንድን የጎሳ ድርጅት መሪዎች በጭፍን እንዲከተሉ ያደርጋል.  እነዚህ በመሪዎቻቸው ሀሳብና ትዕዛዝ በጭፍን የሚመሩ ህሊና ቢስ የተደረጉ በጎሳ ብሄርተኝነት ስሜት የሰከሩ የአንድ ጎሳ ተወላጆች የሆኑ ጀሌዎች መሪዎቻቸው አድርጉ ያሏቸውን ነገሮች ሁሉ ካለ አንዳች ማወላወልና ማንገራገር ይፈፅማሉ.  በዚህ አይነት ህሊናቸውን ያጡ ጀሌዎች በበዙበትና ስልጣን በተቆናጠጡበት ሃገር ውስጥ ሊከሰት የሚችለው አደጋ የብዙ ንፁሃን ዜጎችን ህይወት ሊቀጥፍ ይችላል; ሀገርን ያፈርሳል; ህዝብን ይበትናል.  ትላንት የናዚ ጀርመኖች ፍልስፍና ገዥና ዋና አስተሳሰብ (dominant ideology) በነበረበት ግዜ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አይሁዳዊያን, እስላሞች, ጂፕሲዎች ወዘተ በገፍ እየተነዱ ሲፈጁ አብዛኛው የጀርመን ህዝብ ድርጊቱን ሳይቃወም እንዲያውም ሲደግፍ ታይቶ ነበር.  በዛን ጊዜ በርካታ ጀርመናዊ በናዚ ጭፍን የጀርመን የበላይነት ፍልስፍና (Germany over all ) ወይም ጀርመን ከሁሉ በላይ በሚለው የአርያን የዘር የበላይነት በሚያንፀባርቅ አስተሳሰብ አይምሮው ተመርዞ ነበር.  በዚህ ምክንያት የጀርመን ህዝብ በጎውና መጥፎውን የሚለይበትን ህሊናውን አሽቀንጥሮ በመጣል የራሱን ማንነት አሳልፎ ለናዚ መሪዎች በገፀ - በረከትነት ሰጠ.  
ዛሬ በኢትዮጲያችን ተመሣሣይ ሁኔታ እየታየ ነው ብዬ እሞግታለሁ.  የወያኔ ድርጅት ትግል ሲጀመር የዚህን ድርጅት እኩይ አላማ በመቃዎም የተገረፉ, የተገደሉ, የተሰደዱ የትግራይ ተወላጆች እንዳሉና ለነዚህም ከፍተኛ አክብሮት እንዳለኝ ልገልፅ እፈልጋለሁ.  ለሀገራቸው ያደረጉትንም ውለታ አልረሳም.  ይሁን እንጂ ለ 17 አመታት በጦርነት እንዲሁም ላለፉት 38 አመታት ወይም 39 አመታት በፀረ ኢትዮጲያ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ውስጥ አብዛኛው የትግራይ ተወላጅ በተለይም ቀለም ቆጠረ የሚባለው ክፍል በዛሬው ወቅት የመርዘኛው የትግራይ ብሄርተኝነት ሰለባ በመሆን የዚህ ያለው ፀረ ኢትዮጵያ የሆነ የወያኔ አገዛዝ ደጋፊና አቃፊ ከሆነ ውሎ አድሯል.  በዚህ ምክንያት የወያኔ ስርዓት በሌሎች የኢትዮጲያ ጎሳዎች ላይ የሚፈፅመውን ግፍ ከመቃወም ይልቅ በርካታ የትግራይ ተወላጅ ይህንን የወያኔን ስርዓት በፅናት ከሚቃወሙ ኢትዮጲያውያን በተቃራኒ ጎን መቆምን መርጧል.  ይህንን ገደምም ጠመምም ሳላደርግ ባለፉት 21 አመታት ስናገር እንደቆየሁት ዛሬም በናንተ ፊት በአደባባይ እናገራለሁኝ.  የዚህንም አደገኛ አዝማሚያ አውዳሚ ፍፃሜ አመለክታለሁኝ.  እስቲ በቅድሚያ የቀድሞ የወያኔ ትግሬዎች መሪ መለስ ዜናዊ ለትግራይ ህዝብ ካደረገው እጅግ እብሪትና የማን አለብኝነት ከተጠናወተው ንግግሩ አንዱን ጠቅሼ የትግራይ ብሄርተኝነት ከምን አደገኛና ወደ ሗላ ሊመለስ ከማይችልበት ጫፍ እንደደረሰ መስረጃ አቅርቤ ላስረዳ ልሞግት .  ይህ ከዚህ በታች የምጠቅስላችሁ ንግግር መለስ ዜናዊ መቀሌ ውስጥ የወያኔን የድል በዓል ሲያከብር በመቶ ሺዎች ለሚቆጠር የትግራይ ህዝብ ካደረገው ንግግር ነው:
"ይህ ህዝብ እንኯን የሌሎች ባዕዶች ያልሆነ.  እንኯን ከእናንተ ተፈጠርን.  ይህ የእያንዳንዱ ታጋይ እምነት ነው.  እንኯን ከእናንተው ማህፀን ተፈጠርን.  እንኯን የኛ ሆናችሁ. እንኯን የሌላ የባዳ አልሆናችሁ.  እንኯን በማዶ እያየናችሁ የምንቀናባችሁ አልሆናችሁ. "
በዛው እለት በተያያዘ ንግግሩ መለስ ለትግራይ ወጣቶች እንዲህ ብሎ መልዕክቱን አስተላልፎ ነበር:
". እናንት ወጣቶች እዚህ ያላችሁበት መድረክ እንድትደርሱ ሲባል ታላላቆቻችሁ ላባቸውንና ደማቸውን አፍስሰዋል  . ታላላቆቻችሁ በየጉራንጉሩ በየሸለቆውና በየተራራው ቀርተዋል  ታላላቆቻችሁ አጥንታቸው በየተራራው ተበትኗል.  አጥንቶቻቸው በየተራራው የተበተነበት ምክንያት ትግራይ እንድትለማ በሚል ነው.  እነኚህን አጥንቶች እንዳትረግጧቸው እንዳታረክሷቸው; ሁኔታውን ካመቻቹላችሁ በሗላ እንዳትከዷቸው ሌት ተቀን መጣር ይኖርባችሗል.  "
ይህ ንግግር አንድ በብሄርተኝነት የሰከረ እነ ሂትለር ካደረጏቸው የእብሪት ንግግሮች የላቀ ነው. ዛሬ በዚህ የተቀሰቀሱ ልባቸው ያበጠ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ተፈጥረዋል.  
ዛሬ የወያኔ ትግሬዎችና በስራቸው ያሰለፏቸው የጎሳ ተከታዮቻቸው በአብዛኛው ህሊና እንዳለው ግለሰብ በጎውንና ክፉውን አመዛዝኖ ፍርድ ከመስጠት ይልቅ በወያኔ ድርጅት ትዕዛዝ እንደ መንጋ በጀሌነት የሚመሩ ፍጡራን ሆነዋል.  የአንድ ጎሳ ተወላጆች የራሳቸው ጎሳ ተወላጆች የሆኑ ሰዎች በሌሎች ከነሱ ጎሳ ውጪ ባሉ ተወላጆች ላይ የሚፈፀሙትን ማናቸውንም ህሊና ያለው ሰው ማየት የሚችለውን ጥፋትና ግፍ ለማየት ይሳናቸውና የጎሳ መሪዎቻቸው የሚሏቸውን እየሰሙ ይህን ግፍ ለሚፈፅሙት የጎሳ መሪዎቻቸው ጭፍን ድጋፋቸውን ሲሰጡ ይህ ሁኔታ ለአንድ ሃገር ታላቅ አደጋን ይጋብዛል.  የጎሳ ፍጅት (Genocide) መነሾም ይሆናል.  በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ የታጠቁ የትግራይ ተወላጆች በሃይል ከጎንደር ተቆርሶ ወደ ትግራይ ክልል የተጠቃለለውን ለም መሬት ይዘው አሻፈረኝ ያለውን ነባሩን ህዝብ ገድለው ከፊሉን የተወለደበትንና ያደገበትን ቀዬ ጥሎ ወደ ሱዳን, አዲስ አበባና ጎንደር እንዲሰደድ ማድረጋቸው የወያኔ ትግሬዎች የተፀናወታቸውን ህሊና ቢስነትና አመለካከታቸው በጎሳ አስተሳሰብ የተመረዘበትን ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል.  በቅርቡም የወያኔ ትግሬዎች መንግስት ታሪካዊውን የዋልድባን ገዳም የትግራይ ክልል አካል ነው በማለት በገዳሙ ውስጥ የነበሩትን የትግራይ ቀሳውስትና መነኮሳት በጎሳ ስሜት ቀስቅሶ ከጎኑ በማሰለፍ የወሰደው ገዳሙን የመቆጣጠር እርምጃ ይህንኑ ህሊና ቢስነትና የአንድ አናሳ የጎሳ ተወላጆችን እብሪት የሚያሳይ ድርጊት ነው.  እንደ ኢትዮጲያ ግፍ ሞልቶ በፈሰሰበት ሀገር ውስጥ ይህ አይነቱ ጭፍንነት ሗላ ጎሳን መሠረት ላደረገ ከፍተኛ ፍጅት (Genocide) የሚዳርግ ነው.  , የወያኔ ዛሬ የአማራን ህዝብ ከሶማሌ ከቤኒሻንጉል ከደቡብና ከኦሮሚያ ክልል እንዲዎጡ የተደረገበት በፋሽስቱ የጣሊያን የወረራ ግዜ እንኯን ያልተፈፀመ ዘግናኝ ድርጊት ሲፈፀም የዚህን የአማራ የጎሳ ጥቃት እያስፈፀሙ ያሉት የወያኔ ትግሬዎች መንግስት ትግሬዎች መንግስት ከላይ እስከታች የዘረጋው የስለላ መረብ አዛዦችና የወታደራዊ ጭፍሮቻቸው እንደሆኑ አንዘንጋ.  ~ ~
በክፍል ሁለት የወያኔ መንግስት አንዳንድ ፋሽስታዊ ጠባዮችን እንመለከታለን.

No comments:

Post a Comment

wanted officials