አንድነት ፓርቲ በመጪው ዕሁድ ሰኔ 1 ቀን 2006 በደብረማርቆስ፣ በአዳማ/ናዝሬት እና በቁጫ/ሰላም በር ከተማ የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት በሚል መሪ ቃል ለሚያካሂደው የተቃውሞ ሰልፍ፤ የቅስቀሳ ስራውን የሚያስተባብሩ ሶስት ቡድኖች ከትላንት ጀምሮ ከዋናው ጽ/ቤት መንቀሳቀስ ጀምረዋል፡፡ ዛሬ በቁጫ/ሰላም በር ከተማ የሚደረገውን ቅስቀሳ የሚያስተባብረው ቡድን ወደ ስፍራው አቅንቷል፡፡ በደብረ ማርቆስና በአዳማ የተጠናከረ ቅስቀሳ ከተሰራ በኋላ የፖሊስ የተሟላ የዕውቅና ማስረጃ የያዙት 10 የአንድነትን ደብረ ማርቆስ ላይ እንሁም 9 የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላትን ደግሞ አዳማላይ አስሯል፤ በተጨማሪም የአንድነት ፓርቲ የአዳማ ከተማ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆነው አቶ ተስፋዬ ዋቅቶላን ከሌሎች አመራሮችና አባላት ተነጥሎ እንደታሰረም ለወቅ ተችሏል፡፡
No comments:
Post a Comment