Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, June 8, 2014

ሚሊዮኖች ድምጽ – ኢሕአዴግ የቁጫ ሕዝብን መብት እንደገና ረገጠ – የቁጫው ሰልፍ ታገደ

የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ በሚል መርህ በቁጫ ሊደረግ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ መተላለፉ ታወቀ። ከአዲስ አበባ የቅስቀሳ መኪና፣ ሜጋፎኖች፣ በራሪ ወረቀቶችና ፖስተሮች ይዞ ወደ ቁጭ የሰማራዉ ቡድን ከትላንት በስቲያ ሰላም በር ከተማ የደረሰ ሲሆን፣ ከዞኑና ወረዳዉ የአንድነት አመራርና አባአት ጋር በመሆን፣ ትላንት በማለደ ወደ ቅስቀሳ በሚሰማራበት ጊዜ፣ ፖሊሶች ቅስቀሳዉን አስቆመዋል። ከአዲስ አበባ የሄደው ቡድን እንዳለ እና የወረዳው አስተባባሪዎች በሙሉ ታስረዉ ዉለዋል።kucha1
Kucha
የቁጭ ህዝብ በአገዛዙ ላይ ከፍተኛ ብሶት ያለው እንደሆነ ይታወቃል። ከጥቂት ሳምንታት በፊት ወደ 400 የሚሆኑ የወረዳው አባዎራዎች እስከአሁን ድረስ በእሥር ላይ እንዳሉ ይታወቃል። የሕዝቡን ብሶት የሚያወቁት የወረዳዉ ባለስልጣናት አስቸኳይ ስብሰባ ትላንት ጠርተው፣ ከዞኑ መመሪያ ካላገኝን የታሰሩትን አንፈታም በሚል ቀኑን ሙሉ ሕግ ወጥ በሆነ መንገድ የሰልፍ ቅስቀሳ እንዳይኖር አድርገው ዉለዋል።
ትላንት ሲመሽ፣ ከአዲስ አበባ ለቅስቀሳ የተሰማሩ የአንድነት አባላትን ፣ በጉልበትና በወታደር አጅበው ከወረዳው እንዲወጡ አድርገዋቸዋል። በሕዝቡና በባለስልጣናቱ መካከል ከፍተኛ ዉጥረት የሰፈነ ሲሆን፣ ከቁጫ ወረዳ እንዲወጡ የተገደዱት፣ ከአዲስ አበባ የሄዱ የአንድነት አባላት ይዘው የመጡትን የቅስቀሳ መኪናና ሜጋፎኖች ይዘው ወደ አዳማ ናዝሬት ተሰማርተዋል።
የአንድነት ፓርቲ ላለፉት አንድ አመት በደሴ ሁለት ጊዜ፣ በአዲስ አበባ ሁለት ጊዜ፣ በባሕር ዳር ሁለት ጊዜ፣ በጋሞ ጎፋ፣ በጂንክ፣ በፍቼ፣ በወላይታ ሶዶ፣ በጎንደር፣ ፣ በአዳማ ሰልፎች ያደረግ ሲሆን፣ እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ በአዳማ እንዲሁም በደብር ማርቆስ ነገ ሰልፍ ያደርጋል። በመቀሌ ለሳምንት ከፍተኛ ቅስቀሳ ሲደረግ ቆይቶ፣ ሰልፉ ነገ ሊደረግ ዛሬ ፣ «መቀሌ እንኳን አንድነት ቅንጅትም አልደፈራትም» በሚል እበ አባይ ወልዱ የአንድነት የቅስቀሳ መኪናዎችን በማገት፣ የአመራር አባላቱን ሁሉ በማሰር ሰልፉ እንዲጨናገፍ ማድረጋቸው፣ በተመሳሳይ ሁኔ በባሌ/ሮቢ ሰልፉን ካደረጋችሁ ከፍተኛ ደም መፋሰ ይኖራል የሚል ዛቻ ባለስልጣናቱ በማቅረባቸው፣ ለሕዝብ ደህንነት ሲባል ሰልፉ ነገ ሳይደረግ መቅረቱ ይታወሳል።
የሚሊዮኖች ንቅናቄ ነገ ከሚደረጉት የደብረ ማርቆስና የአዳማ ሰልፍ ቀጥሎ በነቀምቴ፣ በድረዳዋ፣ በአዋሳ፣ በመቀሌ፣ በደብረ ታቦር፣ በወገራ፣ በአርማጭሆ፣ በአሶሳ ፣ በለገጣፎ እና ለሁለተኛ ጊዜ በጂንካ ሰልፎች ለማድረግ እቅድ አለው

No comments:

Post a Comment

wanted officials