Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, June 20, 2014

በምስራቅ ጎጃም የመኢአድ አባል በካድሬዎች ድብደባ ሕይወታቸው አለፈ – ፍኖተ ነፃነት

በምስራቅ ጎጃም በነማይ ወረዳ ደንጎሊማ ቀበሌ አቶ ሞሳ አዳነ የተባሉ የመኢአድ አባል ቅዳሜ ሰኔ 7 ቀን ከቤታቸው ወደ እስር ቤት መሄድ አለብህ በሚሉ የብአዴን ካድሬዎች ድብደባ ሕይወታቸው አልፏል፡፡ ይህን ድርጊት የፈጸሙት ሁለት የብአዴን ካድሬዎች አቶ አዲሱ ጫኔና አቶ ብርሃኑ ታመነ ወደ መኖሪያቸው በመሄድ ወደ እስር ቤት ትሄዳህ በማለት ለማስገደድ ሲሞክሩ በተፈጠረ እሰጣገባ አቶ ሞሳ አዳነ ካድሬዎቹ በፈጸሙባቸው ከፍተኛ ድብደባ ወዲያውኑ ሕይወታቸው ሊያልፍ ችሏል፡፡ በተያያዘ ዜና በዚያው ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ የመኢአድ አባል አቶ ይበልጣል ወንድሜነህ ቤትህ መሣሪያ አለ በሚል ጥርጣሬ እያሳደዱዋቸው እንደሚገኙና እሳቸውም አካባቢያቸውን ጥለው እንደሸሹ የመኢአድ የሕ/ግንኙነት ኃላፊ ለፍኖተ ነፃነት ዝግጅት ክፍል ገልጸዋል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials