የቦሌ ሁለተኛ ደረጃ ት/.ቤት ተማሪዎች የህዝብን ጥያቄ አነሱ።
የቦሌ ሁለተኛ ደረጃ ት/.ቤት ተማሪዎች የህዝብን ጥያቄ አነሱ። በርካቶች ታፍሰዋል። ታስረዋል በዛሬው እለት በቦሌ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በመሰባሰብ ፈተና ከጨረሱ በኋላ ከጠዋት ጀምረው አቤቱታቸውን ሲያሰሙ እንደነበር በቦታው ሁኔታውን የተከታተለው ጥላዬ ታረቀኝ ለምንሊክ ሳልሳዊ ባደረሰው መረጃ ገልጽዋል። ኑሮ ተወደደ ቤተሰቦቻችን በጭንቀት እያሳተማሩን ነው ፡፤ ምግብ ውሃ መብራት የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተው እንደነበር ተዘግቧል። ነጻነት እንፈልጋለን ኑሮ እየመረረን ነው ከብድናል ይእሚሉ ተማሪዎችን ለምበተን ከ100 በላይ የፌዴራል ፖሊስ ወደ ትምህርት
ቤቱ በመግባት ከ40 በላይ ተማሪዎችን አፍሶ የወሰደ ሲሆን ተማሪውን ከግቢ በማስወጣት በቡድን ተሰብስበው የቆሙ ተማሪዎችን ሲያፍስ እና ስበትን ይነበር ሲሆን በርካታ ተማሪዎች ወደ ቦሌ መድሃኒያለም ቤተክርስቲያን ሸሽተው መሄዳቸው እና መሸሸጋቸው ተጠቁሟል። የኢትዮጵያ ህዝብ በኑሮ ውድነት ምክንያት በከፈተን ድእረጃ በመማረሩ ወጣቶች በወያኔ ላይ ጥርሳቸውን የነከሱ ሲሆን በድንገት አድፍተው የለውጥ አብዮት ያመጣሉ በሚል ወያኔ በስጋት በመራዱ የጸጥታ ሃይሎቹን እያሰማራ በመደብደብ እና በማሰር ላይ ሲገኝ በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል ተማሪዎች ላይ የተፈጸመው ተጠቃሽ ነው።
No comments:
Post a Comment