ሰሜናዊውን የአፍሪቃ ንፍቀ ክበብ ይዞ ወደ ጣሊያን በባህር ላይ ጉዞውን ያመራው የነበረው ጀልባ ከመጠን በላይ በማሳፈር ከያዛቸው የምስራቅ እና የሰሜን አፍሪካ ሰደተኞች አሳፍሮ ይጓዝ የነበረው ጀልባ በወቅታዊ ተፈጥሮ አደጋ የባህር ማእበል ከመነሳቱ ጥቂት ሰአታት ቀደም በማለት ስደተኞቹን በህይወት የማትረፉን ለመረጃ ማእከሎች ገልጾአል ።ይሄው የነፍስ አድን ሰራተኞች ቡድን በአሁን ሰአት በሰፊው እየተንቀሳቀሰ ያለው የህገ ወጥ ስደተኞችን አደን አስመልክቶ ሲናገር እነዚህ ከሁለት መቶ በላይ የሚሆኑት ስደተኞች ከጥቂት ሰአታት ቆይታ በኋላ ቢሆን የተገኙት ማናቸውንም በህይወት ላናገኛቸው እንችላለን ሲል ገልጾአል ።ህገወጥ ደላሎችንም በመያዝ ወደ ፖሊስ ምርምርራ እንደላካቸው ገልጾ ፣ብዛት ያላቸው ዜጎት ከኢትዮጵያ ኤርትራ እና ሶማሊያ እንዲሁም ከሴሪያ እንደሚገኙበት አክሎ ገልጾአል ። ከዚህን ጊዜ በኋላ ከፍተኛ ቁጥጥር እንደሚያደርግ የገለጸው የአደጋ ጊዜ ተጠሪው ኮማንደር ለእነዚህ ሰዎች የህይወት መጥፋት እና መሰደድ ጭምር የሃገሮቻቸው መንግስት ተጠያቂ ነው ሲሉ ለአጃንስ ፍራንስ ፕረስ ገልጸዋል ።ለወደፊቱም ከፍተኛ የሆነ ትኩረት ለዜጎቻቸው ቢሰጡ መልካም ነው ሲሉ ምክራቸውንም ለግሰዋል።