Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, June 1, 2014

የመከላከያ ሰራዊት መኮንኖች በአዛዦቻቸው ላይ ውጥረት ፈጥረዋል Defence forces in Chaos

የመከላከያ ሰራዊት መኮንኖች በአዛዦቻቸው ላይ ውጥረት ፈጥረዋል ጄኔራል አበባው ታደሰን እና የብኣዴን መኮንኖችን ያገለለ ስብሰባ መካሄዱ ጥያቄ አስነስቷል


mekelakeya
 በወያኔ የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ውጥረት መፈተሩን ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ተሰምቷል:: በወታደራዊ ጥቅማ ጥቅም እና በህገመንግሥቱ ዙሪያ ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥ አካል መጥፋቱ እና ዝም መባሉ ዉስጥ ውስጡን እየተብላላ ያለው የመኮንኖቹ ጥያቄ እንዳይፈነዳ የተሰጋ ሲሆን ከፈነዳ ሰራዊት ለሶስት ቦታ እንደሚከፈል ለምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮቹ ጠቁመዋል::

መኮንኖቹ በትምህርት በስራ እና በማእረግ እድገት በቤተሰብ እንክብካቤ በደሞዝ ጭማሪ እና በሕገመንግስታዊ የህዝብ መብቶች ዙሪያ ጥያቄ ያነሱ ሲሆን ወታደራዊ ጥቅማ ጥቅሞች ለአንድ ብሄር አባላት ብቻ ተመድበው እየተሰራባቸው ነው ከተማ ውስጥ ታጥቀው የመሸጉ እና ህዝብን እያጠቁ የሚገኙት የአንድ ብሄር አባላት ናቸው እንዱሁም ከሃገራዊ ጥቅም ይልቅ የፓርቲ ጥቅም እየተስተዋለ ነው: ወታደሩ የጦር ሳይንስን እና ዲሲፕሊን በጎደለው መልኩ እየተስተዳደረ ነው በሰራዊቱ እና በሃገሪቱ ሁሉ ወቅታዊ ጉዳዮችን ሽፋን እና ማዘናጊያ በማድረግ የሙስና እና የዘረፋ መስፋፋት መልስ ሊያገኝ ይገባዋል ጄኔራል መኮንኖች አላቸው የተባለው ንብረት ይጣራ በሃገሪቱ የፖለቲካዊ እና የኢኮኖሚ ጥያቄዎች ሊመለሱ ይገባል የሚሉ እና ተመሳሳይነት ያላቸውን ጥያቄዎች ማንሳታቸው ታውቋል::የመከላከያ አባላቱ በኑሮ ውድነት እና በተቃዋሚዎች ህገመንግስታዊ መብቶች ላይ ያነሱት ጥያቄ አዛዦቹን ያስደነገጠ ከመሆኑም በላይ በአንድ ብሄር ላይ የተመሰረተ አስተዳደር እስከመቼ የሚለውም ጥያቄ መመለስ አለበት በሚል የእግር እሳት እየሆነባቸው ነው::

ይህ ከዚህ ቀደም የተጀመረው እና አሁንም በሰሜን እዝ እና በምስራቅ እዝ የተከሰተው የሰራዊቱ ህገመንግስታዊ ጥያቄ እና የጥቅማ ጥቅም አቤቱታ በመላው ሃገሪቱ ተስፋፍቶ በሁሉም የሰራዊት እዞች ውስጥ ጥያቄው መነሳቱን ምንጮቹ አመልክተዋል:: በተለያዩ ጊዜያት እየተንከባለለ የመጣው ይህ የሰራዊቱ አቤቱታ እጅግ አደገኛ አዝማሚያ እያሳየ ሲሆን በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ አስተዳደር እንዲወገድ እና ህገመንግስታዊ መብቶች እንዲከበሩ ጥያቄዎች ገፍተው መምጣታቸው ሲታወቅ ከፍተኛ የሕወሓት ጄኔራሎች በየቀኑ ካለማቋረጥ ምስጢራዊ ስብሰባዎችን እያደረጉ ከመሆኑም በላይ ከየእዙ የሚመጣላቸው ሪፖርት መፍታት የሚቻልበትን ጉዳይ እየተወያየ መሆናቸውን ከዚህ ቀደም ምንጮቹ ገልጸው ነበር::

ሌ/ጄ ሳሞራ የኑስ ጡረታ ወቶ በምትኩ የብኣዴን ሜ/ጄ አበባው ይተካሉ ሲባል ወያኔ በድንገት የመለስ የቅርብ ሰው የነበሩትን እና በአንድ ወቅት የአማር ክልል አቶ አያሌው ጎበዜን ላንቻ አከባቢ በመኖሪያ ቤታቸው ለ3 ወር አግተው ሲያሰቃዩ የነበሩት ሌ/ጄ ዮሃንስ ገብረመስቀልን በማእረግ ሾሞ ሳሞራ የኑስን ለመተካት የሚያደርገውን ሩጫ የብኣዴን አባላት መቃወማቸውን ተከትሎ ጄኔራል አባባውን ጨምሮ የብኣዴን መኮንኖችን ያገለለ የሕወሃት አባላት የሆኑ ጄኔራሎች ብቻ የተሳተፉበት በትግሪኛ የተመራ ስብሰባ መደረጉን ውስጥ አዋቂ ምንጮቹ ተናግረዋል:: በስብሰባው ላይ ቀሪ ከፍተኛ ባለማእረግ መኮንኖች እና የመምሪያ ሃላፊዎች ለምን አልተሳተፉም የሚል ጥያቄ ከአንድ ስማቸው ካልተጠቀሰ ብርጋዴር ጄኔራል መነሳቱን ምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮቹ ጠቁመዋል::

ይህ ስብሰባ ዋና አትኩሮቱ የነበረው በብሄር አደና ላይ ሲሆን እንደ ምንጮቹ መረጃ በአማራ እና በኦሮሞ መኮንኖች እየተመራ ያለውን የለውጥ ጥያቄ በማክሸፉ ዙሪያ እንደነበር እና አሁንም በስፋት የሕወሓትን የፓርቲ አቋም የሚቀበሉ እና የጥቅም ተጋሪ የሆኑ ሰዎችን ለመሾም የታቀደ ሲሆን እንዲሁም ከፖለስ ሰራዊት በከፍተኛ የማእረግ ሹመት ወደ ጦር ሰራዊቱ ለማምጣት የታሰበ ሲሆን በወታደራዊ ደህንነት ዙሪያ ሌላ ተጨማሪ ሰልጣኞችን ከፖሊስ ወስዶ በማሰልጠን ወደ ሰራዊት ማዘዋወር የሚሉ ውይይቶች ተካሂደውበታል:: አሁንም ስብሰባው የቀጠለ ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን እንለቃለን::

No comments:

Post a Comment

wanted officials