አንድነት ፓርቲ የ2007 ምርጫ በተቀናጀ ሁኔታ ለመምራት የምርጫ ግብረ ኃይል አቋቋመ
የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በህዳር 6/2007 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ የ2007 ምርጫ በተቀናጀ ሁኔታ ለመምራት እንዲቻል 10 አባላት ያሉት በከፍተኛ የፓርቲው አመራሮች የሚመራ የምርጫ ግብረ ኃይል አቋቁሟል። ይህ የምርጫ ግብረ ኃይል ፓርቲው በ2007 ምርጫ ውጤታማ ሆኖ እንዲወጣ አጠቃላይ የምርጫ ዘመቻውን በበላይነት የሚመራ ሲሆን፤ በተጨማረም በቅርቡ የሚጀመረው የሚሊዮኖች ድምፅ ለፍትሀዊና ነፃ ምርጫ ህዝባዊ ንቅናቄ ዘመቻ ይህ ግብረ ኃይል የሚመራውና የሚያስተባብረው ይሆናል።
በዚህ አጋጣሚ አንድነት ለምርጫው ከፍተኛ ዝግጅት በማደረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን ከዚህ በፊት ተጀምሮ የነበረው የሚሊዮኖች ድምፅ ዘመቻ የመጨረሻው ምዕራፍ የሆነው ለፍትሀዊና ነፃ ምርጫ ህዝባዊ ንቅናቄ ግቡን እንዲመታና የምርጫ ምህዳሩን እንዲሰፋና ለሁሉም ተወዳዳሪዎች የተመቻቸ እንዲሆን ለምናደርገው ትግል ህዝቡ ከጎናችን በመቆም ነፃነትና ዴሞክራሲያዊ ለውጥ በሀገራችን ለማስፈን ቆርጦ እንዲነሳ ጥሪያችን እናስተላልፋለን።

No comments:
Post a Comment