ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ በአካባቢው የሰፈሩ የፌደራል ፖሊስ አባላት በህዝቡ ላይ የሚወስዱት እርምጃ እየተባባሰ መጥቶ ረቡዕ ሌሊት ለሃሙስ አጥቢያ ፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የፌደራል ፖሊሶች ወደ አንድ ወጣት መኖሪያ ቤት ሰብረው በመግባት እርሱንና እናቱን በአምስት አምስት ጥይኦች በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለው ወደ ካምፓቸው አምርተዋል። የከተማው ህዝብ ተቃውሞውን ለማሰማት ሃሙስ ጠዋት ወደ አደባባይ ቢወጣም የጠበቀው የፖሊስ ዱላ ነው።

ድርጊቱ ያስቆጣቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ከቀበር በፊት የተቃውሞ ሰልፍ ቢያደርጉም፣ በፖሊሶች ዱላ ተደብድበው ተበታትነዋል። ጅማ ጧት አካባቢ በተኩስ ስትናወጥ መዋሉዋንም ነዋሪዎች ተናግረዋል። በጉዳዩ ዙሪያ አንድ የጅማ ነዋሪ አነጋግረናል ከአንድ ሳምንት በፊት አንዋር የተባለ ወጣት በጩቤ በአሰቃቂ ሁኔታ ከተገደለ በሁዋላ ህዝብ ድርጊቱን ለመቃወም ወደ አደባባይ ቢወጣም በተመሳሳይ መልኩ በፖሊሶች ተደብድቦ ተባሯል።
ከአንድ ወር በፊት ደግሞ ኬኔዲ መንገሻ የሚባል አዲስ ቅጥር የመንግስት ሰራተኛ በፖሊሶች ተገድሏል። በአካባቢው የሰፈረው የፌደራል ፖሊስ በህዝቡ ላይ የሚወስደው እርምጃ መጨመሩ ህዝቡ በስጋት እንዲኖር አድርጎታል። ነዋሪዎች እንደሚሉት ሁኔታው ከአቅማቸው በላይ እየሆነ ነው።
የመረጃ ምንጩ በጉዳዩ ዙሪያ ከከተማው ፖሊስ ለማጣራት ያደረገው ጥረት እንዳልተሳካ ተጠቁሟል፡፡
ምንጭ፡-ኢሳት ሬዲዮና ቴሌቪዥን
No comments:
Post a Comment