Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, November 29, 2014

አንድ የአርበኞች ግንባር አባል በእስር መቀጣቱ

አንድ የአርበኞች ግንባር አባል በእስር መቀጣቱ

ኀዳር ፲፰(አስራ ስምንትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :- አርበኛ ጋሻው ሽባባው በሰሜን ጎንደር ዞን አዳርቃይ ወረዳ ከመንግስት ታጣቂ ሃይሎች ጋር ለ4 ወራት ሲፋለም በቁጥጥር ስር መዋሉን ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት የገለጸ ሲሆን፣ በዚህም ድርጊቱ የ4 አመት ከ8 ወር እስራት እንደፈረደበት ገልጿል።
አርበኞች ግንባር በወቅቱ ባደረገው ተደጋጋሚ ጥቃት ከ60 ያላነሱ የመንግስት ወታደሮችን መግደሉን አስታውቆ ነበር። መንግስት ምንም አይነት ጦርነት እንዳልተደረገ ሲያስተባብል ቢቆይም ከሁለት ወር በሁዋላ በጸረ ሰላም ሃይሎች የተደረገውን ወታደራዊ ጥቃት መመከቱንና ከፍተኛ ድል ማግኘቱን ገልጿል።
መንግስት ተመሳሳይ ጥቃት ይፈጸም ይሆናል በሚል ስጋት ሰሞኑን ጦሩን ወደ ድንበር አካባቢ እያንቀሳቀሰ ይገኛል።  መንግስትን በሃይል እናስወግዳለን በማለት ከሚንቀሳቀሱ ሃይሎች መካከል አርበኞች ግንባር፣ ግንቦት7 እና የአማራ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ውህደት ለመጀመር መስማማታቸው ይታወቃል። የእነዚህ ሃይሎች መዋሃድ በአካባቢው ላይ የሚፈጥረው የጸጥታ ስጋት ያሳሰበው ብአዴን ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ፣ ህዝቡ ጸረ ሰላም ሃይሎችን በንቃት እንዲጠብቅ ተማጽኗል። በጠረፍ አካባቢ ያሉ ታጣቂዎች የጦር መሳሪያቸውን እየተቀሙ ሲሆን፣ የመከላከያ ሰራዊት አባላትም መረጃ ያቀብላሉ በማለት የሚጠረጥሩዋቸውን እዬያዙ በማስር ላይ ናቸው።

No comments:

Post a Comment

wanted officials