Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, November 20, 2014

ነፃነት ይቅደም

አንዳንዶች እንደሚሉት ሳይሆን በህወሃት የሚመራው የኢትዮጵያ ገዢ መደብ በተናጠልም ሆነ በቡድን ደረጃ ተዳክሟል።በምድር ላይ ያለው እውነታ ይህንን ያመላክታል።ስርአቱ በመርበድበድ (in a state of panic ) ላይ መሆኑን የሚጠቁሙ ብዛት ያላቸው ምልክቶ እየታዩ ነው::
1.ከ 23 አመታት በኋላ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ሰብስቦ ስለአብዮታዊ ዲሞክራሲ መስበክ፤
2.ከ~95 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ 1.5% ብቻ የኢንተርኔት ተጠቃሚ በሆነበት “በፌስቡክና ትዊተር ሀዝቡ በተሳሳተ መረጃ እንዳይወናበድ በአግባቡ ለመጠቀም” በሚል ሰበብ ስልጠና መስጠት፤
3.ባንዲራችንን ጨርቅ (rag ) ነው እንዳላሉ ዛሬ ባንዲራ “ተዋረደ ተረገጠ” ብሎ ያዞ እምባ ማንባት፤
4.ኤርትራ የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ስለነበረች የኤርትሪያ ጥያቄ ከቅኝ ግዛት ነፃ የመውጣት ጥያቄ ነው ሲሉ ቆይተው ዛሬ ከ40 አመት በኋላ ቃላቸውን አጥፈው የኢትዮጵያን ህዝብ ለማጭበርበር “በኤርትራ ጉዳይ የያዝነው አቋም በጉዳዩ ላይ ተገቢ ጥናትና ምርምር ሳይደረግ ነው ” ማለት፤
5.ትናንት “የአሰብ ወደብ ጉዳይ ከሸቀጥ ተለይቶ አይታይም” እንዳላሉ ዛሬ “ወደብን ገዝቶ ከመጠቀም በዘለለ አኳሃን መነጋገር አስፈላጊ ነው” ብሎ ማውራት፤
6.እየተጠናከረ የመጣውን የዲያስፖራን ተቃውሞ ” የሚቋቋም ግብረሃይል እንዲመሰረት” ጥሪ ማቅረብ;….ወዘተ ከብዙ የመርበትበት ምልክቶች ጥቂቶቹ ናቸው።
ይህማለት ደግሞ ሥርአቱ መግዛት አቅቶት በራሱ በሚወድቅበት ደረጃ ላይ ደርሷል ማለትም አይደለም።የግድ የሚገፈትረው የተባበረ ጡንቻ ያስፈልገዋል።
የተቃዋሚ/የአማርጭ ሃይሎች ትግሉ በተጠናከረ ሁኔታ እንዲቀጥልና የገዢው ቡድን መግዛት አቅቶት እስኪወድቅ ከመጠበቅና ሊከሰት ከሚችል ቀውስ አገሪቱን ለማዳንና ህዝቡን ለመታደግ የተያዘው ትግል ተጠናክሮ መቀጠል የኖርበታል።
መደረግ/መጠናከር ከሚገባቸው ውስጥ ጢቂቶችን መጥቅስ ቢያስፈልግ፤
1. ከኔ ሌላ አዋቂ የለምና እኔን ብቻ አድምጡኝ/ተከተሉኝን ማቆም።
2. በፖለቲካ ፓርቲዎችና በሌሉችም ህዝባዊ ድርጅቶች መሃከል አስፈላጊ ያልሆነ ውድድሮችን መግታት፤
3. አገርውስጥም ሆነ ካገር ውጭ ያሉት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ህዝባዊ ድርጅቶች ህብረተሰቡን ለውይይት ሲጠሩ ከመድረክ ላይ በሚቀርቡት ገለጻውችና በህወሃት ውንጃላዎች የሰብሰባውን ሰአት ከማባከን እንዴት ስርአራቱን ማስወገድ እንደሚቻል ለታዳሚዎች ሰፊ የውይይት ጊዜ መስጠት።ይህ ደግሞ የህብረተሰቡን ተሳፎ ከመጨመሩም ሌላ የትግሉ በለቤትነትን ያጥናክራል፤
4.በፖለቲካ ፓቲዎችና በሌሉችም ህዝባዊ ድርጅቶች አባላት መሃከል የመደማመጥ፤የመቻቻል፤ችግሮችን በጊዜ የመፍታት፤በብዙሃን የበላይ ነት የመመራት፥ወዘት ባህልን ማዳበር። ይህ ደግሙ በበኩሉ የድርጅቶችን ዲሞክራሲአዊ አሰራርን፤ጠንካራ ድርጅታዊ ሰነ-ምግባርን፡ ያጠናክራል።አባላት በሆነ ባልሆነ ባኮረፉ ቁጥር በድርጅቶቻቸው ስሞች ላይ ዲን D) በመቀጠል ሌላ አዳካሚ ድርጅት እንዳይ መሰርቱ ያደርጋል (በአሁኑ ወቅት አንዳንድ ድርጅቶች ባልጠፋ ስም የመጀመሪያውን የድርጅታቸውን ስም እንደያዙ እስከሶት እንደተከፈሉ እየሰማን ነው)፤
5.ከተቻለ ወህደትን አሊያም ግንባር በመፍጠር ጡንቻቸውን ማጠናከር።በጋራ ሊያስማማን በሚችል ላይ በማተኮርና በልዩነት ላይ በመቻቻል ከሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በጋራ ለመስራት ጥረት ማድረግ ያ ካልተቻለ ደግሞ መጠላለፍን መቆም ይበጃል።ወደጎን መጎሻሸም ማብቃት አለበት። ለህወሃት እንጂ ለማንም አይጠቅምምና፤
6.ትግሉ ያለው አገር ቤት ነው እዚህ ያለው (ዳያስፖራው)ምንም ሊያደርግ አይችልም የሚባለውን በጥሞና ማየት።በዳያስፖራው ያልታገዘ በተለይም በታዳጊ አገሮች አንድም ለውጥ አልተካሄደም። በርግጥ መሪውን (Steering wheels )ይዞ የለውጥን ባቦር የሚያሽከረክረው አገር ቤት ያለው ህዝብ መሆኑ የሚካድ አይደለም። ሆኖም ዳያስፖራው በነጻነት ሃሳቡን በሚገልጽበትና የተሻለ የምጣኔ ሃብት ባላቸው አገሮች ስለሚኖር መረጃን በማቀበልና የድርጅቶችን አቅም በመገንባት ከፍተኛ አስተውጽኦ አለው።ለዚህም ነው በህወሃት የሚመራው “መንግስት” ጥቂቶች ናቸው እያለ ነጋ ጠባ ስለ ዳያስፖራው የሚያለቃቅሰው።የፖለቲካ ድርጅቶች ለግባቸው መሳካት በሚያመነጩት አማራጭ ሃስብ ብቻ ሳይሆን በምጣኔ-ሃብትም ጠንካራ መሆን ይኖርባቸዋል። በተለይም ህወሃት ይህንን ጠንቅቆ ያውቀዋል።በታላቁ የ1984 ዓም ድርቅ ወቅት ቆሜለታለሁ ይል የነበረው ህብረተብ በረሃብ ሲያልቅ ህወሃት የርዳታ ስንዴን ለአቅም መገምቢያ ያደርግ ነበር፤የሃውዜንም እልቂት ያቀነባበሩት ከፖለቲካ ድጋፍ በተጨማሪ የምጣኔ ሃብት አቅም ግንባታን ከውጭ በእርዳታ መልክ ለማጠንክር ነው።በለስ ቀንቷቸው ቤተ መንግስቱን እንደተቆናጠጡ በ EFFORT ስም የጀመረቱ የኢኮኖምውን ዘርፍ የተቆጣጠሩት በሚያራምዱ ርዕዮታ-አለም ብቻ ያለህዝብ ድጋፍ ስልጣኑን እንደጨበጡ መቆየት የማይችሉ መሆናቸውን ስለሚያውቁ ነው፤
7.የምዕራባውያን ድጋፍ በተለይም የኢኮኖሚው ድጋፍ ባይኖረው ይህ በህወሃት የሚመራው “መንግስት” አንድቀንም ውሎ ባላደረ ነበር።ለዝህም በ97 ምርጫ ማግስት በተካሄደው ህዝባዊ ዘመቻ በተወሰነ መልኩ እርዳታ በመቋረጡ ምንያል ህወሃት እነደተደናበረ ማስታወሱ በቂ ነው።ስለዚህ ይህንን የገቢ ምንጭ (ያለ “መንግስት” ጣልቃገብነት የሚሰጠውን ሰብአዊ እርዳታን ሳይጨምር)እንዲደርቅ በማደረግ ላይ ያለው አመርቂ የሆነ ሥራ መቀጠል አላበት ።በታላቋ ቢሪታኒያ በቆራጥ አክቲቪስቶች እየተደረገ ያለውና ውጤትም ባማሳየት ላይ ያለው በሌሎችም አካባቢዎች መጠናክር ይኖርበታል።ለዚህም የዲፕሎማሲ ሥራ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።ለንደን ወይም ዋሽንግተን ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም የምዕራባዊያ መዲናዎቆች (የመንግታት መቀመጫዎች) ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል፤
8.ትግሉ ያለው አገር ቤት ነው እዚህ ያለው (ዳያስፖራው)ምንም ሊያደርግ አይችልም የሚባለውን በጥሞና ማየት።በዳያስፖራው ያልታገዘ በተለይም በታዳጊ አገሮች አንድም ለውጥ አልተካሄደም። በርግጥ መሪውን (Steering wheels )ይዞ የለውጥን ባቦር የሚያሽከረክረው አገር ቤት ያለው ህዝብ መሆኑ የሚካድ አይደለም። ሆኖም ዳያስፖራው በነጻነት ሃሳቡን በሚገልጽበትና የተሻለ የምጣኔ ሃብት ባላቸው አገሮች ስለሚኖር መረጃን በማቀበልና የድርጅቶችን አቅም በመገንባት ከፍተኛ አስተውጽኦ አለው።ለዚህም ነው በህወሃት የሚመራው “መንግስት” ጥቂቶች ናቸው እያለ ነጋ ጠባ ስለ ዳያስፖራው የሚያለቃቅሰው። የፖለቲካ ድርጅቶች ለግባቸው መሳካት በሚያመነጩት አማራጭ ሃስብ ብቻ ሳይሆን በምጣኔ-ሃብትም ጠንካራ መሆን ይኖርባቸዋል። በተለይም ህወሃት ይህንን ጠንቅቆ ያውቀዋል።በታላቁ የ1984 ዓም ድርቅ ወቅት ቆሜለታለሁ ይል የነበረው ህብረተብ በረሃብ ሲያልቅ ህወሃት የርዳታ ስንዴን ላቅም መገምቢያ ያደርግ ነበር፤የሃውዜንም እልቂት ያቀነባበሩት ከፖለቲካ ድጋፍ በተጨማሪ የምጣኔ ሃብት አቅም ግንባታን ከውጭ በእርዳታ መልክ ለማጠንክር ነው፤
9.የምዕራባውያን ድጋፍ በተለይም የኢኮኖሚው ድጋፍ ባይኖረው ይህ በህወሃት የሚመራው “መንግስት” አንድ ቀንም ውሎ ባላደረ ነበር።ለዚህም በ97 ምርጫ ማግስት በተካሄደው ህዝባዊ ዘመቻ በተወሰነ መልኩ እርዳታ በመቋረጡ ምንያል ህወሃት እነደተደናበረ ማስታወሱ በቂ ነው።ስለዚህ ይህንን የገቢ ምንጭ (ያለ “መንግስት” ጣልቃገብነት የሚሰጠውን ሰብአዊ እርዳታን ሳይጨምር) እንዲደርቅ በመደረግ ላይ ያለው አመርቂ የሆነ ሥራ መቀጠል አላበት። በታላቋ ቢሪታኒያ በቆራጥ አክቲቪስቶች እየተደረገ ያለውና ውጤትም ባማሳየት ላይ ያለው በሌሎችም አካባቢዎች መጠናክር ይኖርበታል፤
10.የዲፕሎማሲ ሥራም ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።ለንደን ወይም ዋሽንግተን ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም የምዕራባዊያን መዲናዎቆች (የመንግታት መቀመጫዎች) ከትኩረቶቹ ውስጥ መጠቃለል አለባቸው። ባልጠበቀው ሁኔታ እየተዳከመበት የመጣ ቢሆንም ህወሃት በምእራባዊአያን ድጋፍ ስልጣን ላይ ለመቆየት በዲፕሎማሲ ስምና ሎቢዎችን በመቅጠር የህዝቡን ገንዘም ሲያፈስ ሰንብቷል።ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው እንደሚባለው አንዳንድ የውጭ ዜጎች ከህወሃት በላይ ለህወሃት ስከራከሩ ለግል ጥቅም (self-interest)ሲባል ሲዋሹ ተደምጠዋል። ህዝቡ ግን የእውነት ባለቤት ነውና ከተሰራበት ውጤቱ ለትግሉ ጠንካራ ድጋፍ ይሆናል፤
11.ከዚህቀደም የተጀመረውና ከሞላ ጎደል ተግባራዊ እየሆነ ያለው የበህወሃት መራሹ “መንግስት” በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የገቢ ምንጭ የሆኑት ተቋማትና የንግድ ድርጅቶች ማዕቀብ ገንዘብን በቀጥታ ወደ አገር የመላክን ጨመሮ በተጠናከረ መልኩ መቀጠል ይኖርበታል።
አንድ ሰው በትምህርትም ሆነ በልምድ ያካበተውን እውቀት እንዳለውና ህብረተሰቡን ለማገልገል ፍቃደኝነቱን ማሳየቱ የሚበረታታ መሆን የኖርበታል። አንድ የፖለቲካ ፓርቲ ከሊላው ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች የተሻለ መሆኑን በርግጠኝነት መሟገቱም እንከን አይኖረውም። ጤናማ ውድድር ለህብረተሰብ እድገትና ለለውጥ አስፈላጊነውና።ይህም ደግሞ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ስላሉ የሚሆን ሳይሆን ባለዕውቀቱም ሆነ የፖለቲካ ፓርቲውም በተግባር አሳይተው ህብረተሰቡ ሲቀበላቸው ብቻ ነው ።ህብረተስቡ ሊመስክርላቸው የሚችለው ደግሞ በነጻ ሃሳቡን ለመግለጽ ሲችል ነው ።በሃገራችን ነባራዊ ሆኔታ ሃሳብን በነጻነት ለመግለጽ የታደሉት ጥቂቶች ብቻ ስለሆኑ ከሁሉም ቅድሚያ ሊሰጥ የሚገባው (precondition) ለነጻነት መሆን አለበት።ነጻነት መቅደም አለበት።ባሁኑ ሰአት ለህዝባችን ከነጻነት ሌላ ሁሉም የቅንጦት ( luxury ) ነው። ህዝቡ በቃኝ ካለ ቆይቷል።አዎ በቅቶሃል አንተን ነጻ ለማውጣት ከጎንህ ነኝ ብሎ በተግባር የሚያሳይ እንጂ ከላይ ለመጥቀስ የሞከርኩትን የቅንጦት ጊዜ ተግባራት የሚከናወኑትን ማየትም ሆነ መስማት አይሻም።ለህዝቡ ምላሽ ለመስጠት ደግሞ ከምን ጊዚም የተሻለ ወቅት አሁን ነው የሚል እምነት አለኝ።ስለዚህ እውነት ከልባችን ህዝባችንንና ሃገራችንን ነጻ ለማውጣት ቆርጠኞች ከሆን እላማችን (target) ነጻነት ሆኖ ለዚያ የተቻለን ሁሉ ማድረግ ይኖርብናል።ለተግባራችን መሳካት የፈጣሪያችን እርዳታ አስፈካጊነት ጥርጥር ስለሌለው እንደእእምነታችን ጸሎት/ዱአ ማድረግ ይገባናል።
ፈጣሪያችን ኢትዮጵያን ከነህዝቦቿ ይባርካት። አሚን።
ባህር ከማል
bahirk@hotmail.com

No comments:

Post a Comment

wanted officials