Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, November 22, 2014

በትግራይ የዓረና ኣስተባባሪና የማእከላይ ኮሚቴ ኣባል ታሰረ

በትግራይ የደቡባዊ ዞን የዓረና ኣስተባባሪና የማእከላይ ኮሚቴ ኣባል ወጣት ሃፍተ ግርማይ በዓዲ ሽሁ ታሰረ።
————————————
ዛሬ ዓርብ 12 / 03 / 2007 ዓ/ም ረፋድ 04:20 ሰዓት በእምባ ኣላጀ ወረዳ ዓዲ ሽሁ ከተማ የዓረና በራሪ ፅሁፍ በማደል ላይ ከነበሩ የዓረና ኣባላት የማእከላይ ኮሚቴ ኣባልና የደቡባዊ ዞን የዓረና ኣስተባባሪ የሆነው ወጣት ሃፍተ ግርማይ በፖሊስ ታስረዋል።
የእምባ ኣላጀ ወረዳ የካቢኔ ኣባላትና የዓዲሽሁ ከተማ ኣመራሮች ወረቀት እየተቀበለ የነበረው ህዝብ “…እንዳትቀቡሉ..” እያሉ ማስፈራራት፣ የተቀበለ ሰው ወረቀት እየቀሙ እየቀደዱ፣ ወረቀቱ ተቀብሎ ” ኣልሰጥም..!” ያላቸው ህዝብ በቪድዮ እየቀረፁና እያስፈራሩ፣ በዓረና ኣባላት ወከባ በመፍጠር ላይ ይገኛሉ።
የህወሓት ካድሬዎች የህብረተሰቡ የለውጥ ፍላጎት ለማፈን ከሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች ህዝቡንና የዓረና ኣባላት ማስፈራራት፣ መደብደብና ማሰር ናቸው።
የቀሩት የዓረና ኣባላትም በፖሊስና በወረዳው ኣመራሮች በራሪ ፅሑፉ እንዳያድሉ ታግተው ይገኛሉ።
የዚህ ተመሳሳይ ዓፈና ተግባር በመላው ትግራይ ዘወትር የሚፈፀም ፀረ ዲሞክራሲያዊ የህወሓት ስራ ነው።
በነገራችን ላይ የዓረና ኣባላት ዓፈናውና እንግልቱ ሳይበግራቸው በፅናት በራሪ ወረቀት ለህዝቡ ለማድረስ እየታገሉ ይገኛሉ።
የህወሓት መንግስት የትራንስፎርሜሽን እቅዱ የዓረና ኣባላት በማሰርና ደብድቦ ኣካል በማጉደል ያሳካው ይመስላል።



No comments:

Post a Comment

wanted officials