Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, November 21, 2014

አጭበርባሪው ፓስተር ዳዊት

 ዳዊት ሞላልኝ ይባላሉ:: ግልጋሎታቸውን የሚሰጡት ኤፍ ቢ አይ በሚል ስያሜ የሚታወቀው ድርጅታቸው ነው:;
ቀድሞ በወጣትነቴ የማይገባኝን ደሞዝ አገኝ ነበር :; እኔ ነኝ ያልኩ ባለሙያ ነበርኩ የሚሉት ፓስተሩ በአብዛኛው ተከታዮቻቸውን እያሳቁ እያዝናኑ በማስተማር ይታወቃሉ:: <ፓስተሩ> በ 18 አመት ያህል የትዳር ቆይታም አላቸው:;
ዛሬ እኝሁ <ፓስተር> ከ ተከታዮቻቸው ዘንድ ዙሪያውን የሚነገርባቸው ( unverified) የሆነ አንድ ነገር አለ::
..ሰውየው የባለ ብዙ ሃብት እና ብር ባለቤት እንደሆኑ …
ስለዚሁ ጉዳይም ሲነሳ በ እርግጥም ይላሉ <ፓስተር > ዳዊት ሞላልኝ ስለሁኔታው በስብከታቸው መሃል በስጨት ብለው ሲያብራሩ ….< ጠጣ ጠገበ ፎቅ ቤት ሰራ ሲባል እንደው ደስ አለኝ እና አንድ ዜማ መጣልኝ …. (በዜማ) ጦሜን እንዳላደርኩ ሳይበላ አንጀቴ_____ደግሞ ጠገበ አሉኝ ተመስገን አባቴ…..እኛ ያላማረብን ማን ይመርበት እኛ ያልጠገብን ማን ይጥገብ? ሟርተኛ የክፋት አሰራር ወሬኛ መንፈስ ዛሬ ይገለበጣል!!!በጣም ነው ሚያስደንቀኝ…70 ሺ ነው ደሞዙ 40 ሺ ብር ነው ደሞዙ..ምንድን ነው ይሄ? ይሄ ለ እግዚአብሄር ሰዎች 70 ሺ ቁምነገር ነው?ምን ይላሉ እነዚህ …ቆይ ቆይ በጌታ..እኔ ኳስ አያለሁ :;የቼልሲም ደጋፊ ነኝ:: ዳዊት በሳምንት እስከ 40 ሺ ብር ገቢ ያገኛል ይሉኛል:; የማንችስተሩን ሩኒን ታውቁታላችሁን ? አዎ…ሩኒ በሳምንት እስከ 360 ሺ ፓውንድ ይከፈለዋል :: ቢጫወትም ባይጫወትም…ተሰብሮ ቢቀመጥ እንክዋ ..ገቢው ሲታሰብ በወር በ ኢትዮጵያ 40 ሚሊየን ብር ድረስ መሆኑ ነው….ሩኒ ኳስ ነው ሚያባረው…እኔ የማባርልህ ሰይጣንን ነው:: በሳምንት 40 ሺ አይደለም ሌላ ባገባስ ….ጌታን ይህም ያንሰኛል ነው ምላችሁ…ጨምራችሁ መኪና አለው ምናምን ትላላችሁ …አሁን በቀደምለት ከ ቦስትዋና ነው የመጣሁት…የኮሌጅ ተማሪዎች ከትምህርት ሲወጡ በመኪናቸው ይሄዳሉ:: መኪና ማለት እግር ነው ሌላ ነገር አይደለም ….> ይቀጥላል
በ እርግጥ የሚባለው ነገር እውን ከሆነ <ፓስተሩ> ለተጨማሪ ገቢ የሚጠበቅባቸው ቅርንጫፎቻቸውን ብቻ ማስፋት ነው የሚሉ ወገኖች አሉ
አንዳንዶች ጉዳዩን አገር ውስጥ ገቢ አንድ ነገር ሊለው ይገባል ሲሉ ተቀሪዎች ደግሞ
ነገርዬውን መንፈሳዊ ነኝ ከሚል ሰው የማይጠበቅ….እኛ ብዙ ለፍተን ይላገኘነውን <ፓስተሩ> ላይ ማየታችን ያስተዛዝባል ሲሉ ተደምጠዋል::
የሆኖ ሆኖ የ<ፓስተሩ> አላቸው የተባለው ገንዘብ ከ እውነት የራቀ እንዳልሆነ ራሳቸው መድረክ ላይ በመሃላ የተናገሩት ሲሆን ወደፊት በጉዳዩ ላይ አዲስ ነገር ከተፈጠረ ማንኛውንም ትችትም ሆነ አስተያየት ተከታትዬ ይዤ መጣለሁ ::
ሊንኩን በመንካት ያዳምጡት
የዋሁ የአገሬ ህዝብ ንቃ ከተኛህበት ወያኔ በተለያዬ ምክንያት በኢኮኖሚ እያላሸቀክ እያለ ያንን ችግር ለመርሳት መደበቂያ እና መጽናኛ ፍለጋ ቢሄድ ፓስተር ዳዊት ተቀብሎ እንደካዋስ ያንደባልልካል አይን ያወጣ ብዝበዛ ንቃ ንቃ ንቃ

No comments:

Post a Comment

wanted officials