Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, November 21, 2014

የፀገዴ ወረዳ ህዝብ አማራ እንጅ ትግሬ አይደለንም በማለት ተቀዋውሞ እያካሄደ ነው።

ዜና
የፀገዴ ወረዳ ህዝብ አማራ እንጅ ትግሬ አይደለንም በማለት ተቀዋውሞ ያካሄደ ነው።
ህዳር 06 /03 /2007 ሌሊት ሙሉ የፀገዴ ወረዳ በቅስቀሳ በራሪ ወረቀት ተጥለቅልቆ አድሯል። በራሪ ወረቀቱ እኛ የፀገዴ ህዝብ የጎንደር አማራ እንጅ ትግሬ አይደለንም ትግሬ ያልሆነውን በሃይል ማንነታችን ጠፍቶ የማንፈልገውን እንድንሆን ተገደናል።ይህንንም በዝምታ የማናልፈውና ማንነታችን የማስከበሩን ትግል እጠናክረን እንቀጥላለን። መላው የፀገዴ አማራ በያለህበት ተነስ ተደራጅ ታጠቅ ታገል፣ የሚል ፁሁፍ ነው። ፁሁፉን የወያኔ ካድሬወች እንዳገኙት በዘመቻ እየሰበሰቡና ህዝቡ የወሰደውንም እየቀሙ ሲሆን፣ የወረዳው አስተዳዳሪም ፓምፕሌቱን ለክልልና ለፌደራል በፋክስ መላኩ ታውቁአል።
ይህንን የህዝብ ቁጣ ተከትሎ በአሁኑ ሰዓት ወደ ፀገዴ በርከት ያለ የፀጥታ ኃይል ከጎንደርና ከትግራይ እየገባ ሲሆን እስካሁን በርካታ ሰው የታሰረ መታሰሩ ሲታወቅ፤ ህዝቡም በተለያየ መንገድ እየተመካከረ ወደ በረሃ ወጥቷል። ለለውጥ የሚታገሉ ሃኃሎች የህዝቡን ጥያቄ በመመለስ አብሮነታቸውን ማስመስከር ያስፈልጋል።
“የተበተነውን ፓምፕሌት ያንብቡት”

No comments:

Post a Comment

wanted officials