- የሁለቱንም አንጃዎች ዜና ዝርዝር ይመልከቱት :: – ድጋሚ እርቅ ያስፈልጋቸዋል;
- ምርጫ በመጣ ቁጥር ስህተትን በመደጋገም የኢትዮጵያን ሕዝብ ትግል ማደናቀፍ ማብቃት አለበት::
- በህዝባችን ላይ እየተፈጸመ ያለው የፖለቲካ አሻጥር (ሳቦታጅ) ግልጽ መሆን አለበት::
- አዲሱ የመኢአድ አመራር ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር የተጀመረው ግንኙነት እንደሚያስቀጥል አስታወቀ
- አዲሱ የመኢአድ አመራር የፓርቲውን ማህተም ተሰርቄያለሁ ብሏል
- ምርጫ በመጣ ቁጥር ስህተትን በመደጋገም የኢትዮጵያን ሕዝብ ትግል ማደናቀፍ ማብቃት አለበት::
- በህዝባችን ላይ እየተፈጸመ ያለው የፖለቲካ አሻጥር (ሳቦታጅ) ግልጽ መሆን አለበት::
- አዲሱ የመኢአድ አመራር ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር የተጀመረው ግንኙነት እንደሚያስቀጥል አስታወቀ
- አዲሱ የመኢአድ አመራር የፓርቲውን ማህተም ተሰርቄያለሁ ብሏል
በዚህም መሰረት በአቶ አበባው መሃሪ የሚመራው መኢአድ ስልጣኑን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ በኢሓዴግ ጥርስ ውስጥ በመግባቱ ከምርጫ ቦርድ እውቅና ከመነፈጉም በላይ ከአንድነት ጋር ሊያደርገው የነበረው ውህደት በምርጫ ቦርድ እንቅፋትነት ተንጠልጥሎ የቀረ ከመሆኑም በላይ የምርጫው ውህደት በሚፈጸምበት እለት አሁን መኢአድን በአመራርነት ላይ ነኝ የሚሉት አቶ ማሙሸት የኢትዮጵያን ቴሌቭዥንን እና የደህንነት ሃይሎችን አስከትለው በመምጣት አከባቢው ላይ ችግር ተፈጥሮ እንደነበር ይታእሳል::
ይህንን ተከትሎ አቶ ሃይሉ ሻውል በተገኙበት እርቅ ተፈጸመ ቢባልም ውጥረቱ ሰፍቷል የሚሉ የድርጅቱ አባላት እየተናገሩ ነው በዛሬው እለት ነገረ ኢትዮጵያ ለምንሊክ ሳልሳዊ በላከው ዜና መሰረት እና በአቶ አበባው የሚመራው የመኢአድ ጓድ የሰጠው መግለጫ እንደሚከተለው ሰፍሯል::
ዛሬ ህዳር 4/2007 ዓ.ም በፓርቲው ዋና ጽፈት ቤት መግለጫ የሰጠው የመኢአድ አዲሱ አመራር ከመኢአድ ጋር ተመሳሳይ ፕሮግራም ካላቸውና ከሌሎቹም የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ከአሁን ቀደም አብሮ ለመስራት የተጀመረውን እንቅስቃሴ እንደሚያስቀጥል አስታውቋል፡፡
በ2003 ዓ.ም ከታህሳስ 15-17 ድረስ አይቤክ ሆቴል ጠቅላላ ጉባኤ ከተካሄደ በኋላ በፓርቲው አመራሮች መካከል ችግር እንደነበር የገለጸው አዲሱ አመራር ከዛ በኋላ አቶ አበባው መሃሪ ፕሬዝደንት የሆኑበት አካሄድ ትክክል እንዳልነበር፤ለአራት አመት ያህል በሁለቱ ቡድን መካከል የነበረው አለመግባባት በእርቅ እንደተቋጨና አቶ አበባው ኃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው እንደለቀቁ የጻፉትን ደብዳቤ ዋቢ አድርጎ ገልጾአል፡፡ በመሆኑም የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች ያለ ምንም ገደብ ወደ መኢአድ ጽ/ቤት መምጣት ይችላሉ ሲል ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
በአንጻሩ አዲሱ አመራር በህገ ወጥ መንገድ ነው ወደ ስልጣን የመጣው በሚል ቅር የተሰኙ የፓርቲው አመራሮችና አባላት ዛሬ ከሰዓት መግለጫ እንደሚሰጡ ተሰምቷል፡፡ ጉዳዩን ለማጣራት አቶ አበባው መሃሪ ጋር በተደጋጋሚ ብንደውልም የእጅ ስልካቸውን ሊያነሱ ባለመቻላቸው ሀሳባቸውን ማጠቃለል አልቻልንም፡፡
በሌላ በኩል አዲስ አመራር ማህተሙ አዲሱ አመራር ከመምጣቱ በፊት ፓርቲው ውስጥ በነበሩትና በአዲሱ አመራር ጋር ባልተስማሙ አካላት እንደተሰረቀ አስታውቋል፡፡ ‹‹ማህተሙ ከዚህ ቤት በነበሩ ሰዎች ተሰርቋል፡፡ ይህን ጉዳይ በወቅቱ ለፖሊስ አመልክተናል፡፡ በፓርቲው ማህተም እኛ የማናምንበትና ህገ ወጥ ነገር ቢሰራበት ተጠያቂ የሚሆኑት እነሱ ናቸው፡፡›› ሲሉ አዲሱ የፓርቲው ፕሬዝደንት አቶ ማሙሸት አማረ ገልጸዋል፡፡
ከዚህ በታች የመኢአድ ፕረዚዳንት አቶ አበባው መሃሪ ከስራ አስፈጻሚዎቹ ከአቶ ካሳሁን እና ከአቶ ሲራክ ጋር የሰጡትን መግለጫ በጥሞና ያንብቡ::
No comments:
Post a Comment