Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, November 20, 2014

በአርባምንጭ ታስረው የሚገኙ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተፈረደባቸው

ኀዳር (አስርቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-በ2006 ዓም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ረብሻ አስነስታችሁዋላ በሚል ከታሰሩት መካከል 4 ተማሪዎች በ2 አመት ከ3 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላልፏል። ሁለቱ የ4ኛ 5ኛ አመት የህክምና ተማሪዎች ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ ድገሞ የ3ኛ አመት የነርሲንግ ተማሪዎች ናቸው።
በሌላ በኩል ደግሞ መንግስት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሚከተሉትን የአለባባስና የምግብ ስነስርአት መመሪያን ተግባራዊ ለማድረግ በዛሬው እለት በአዳማ ዩኒቨርስቲ እንቅስቃሴ መጀመሩ ታውቋል። መንግስት ያወጣውን ህግ ተግባራዊ ለማድረግ በሚንቀሳቀስበት ወቅት መጠነኛ የሆነ ግርግር በዩኒቨርስቲው በር ላይ ተፈጥሯል።
መንግስት በ2003 ባወጣው መመሪያ የእስልምና እምነት ተከታይ ሴትተማሪዎች “ሂጃብ” ማድረግ የሚችሉ ሲሆን “ኒቃብ” መልበስ ግን አይችሉም። መንግስት ለጸጥታና ደህንነት ሲባል የተወሰደ እርምጃ ነው ብሎአል። ሃይማኖታዊ በአላትና ዝግጅቶችን በትምህርት ተቋማት ማካሄድ፣ በቡድን ሰበካ ማካሄድ፣ በቡድን መዘመር፣ በቡድን መጸለይና በቡድን መስገድ እንዲሁም የሃይማኖት መቀስቀሻ የሆኑና ከሃይማኖት ጋር ተያያዥነት ያላቸው የህትመትና የኤሌክትሮኒክስ ውጤቶችን በትምህርት ተቋማት ግቢ ማሰራጨትና በመቀስቀሻነት መጠቀም ተከልክሏል።  በምግብ አዳራሽ መመገቢያ ሰአት በግል የህሊና ጸሎት ማድረግ የሚቻል ሲሆን በቡድን ወይም ከአንድ በላይ በመሆን መጸለይ አይቻልም።

No comments:

Post a Comment

wanted officials