Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, November 22, 2014

የሸንጎው ከፍተኛ አመራር ምክር ቤት ስብሰባ የህዝቡን ትግል ለማጠናከር የሚያሰቸሉ ተጨማሪ ውሳኔወችን በማስለላለፍ ተጠናቀቀ

የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሽንጎ (ሽንጎ) ከፍተኛ የአመራር ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ቅዳሜ ሕዳር 6፣ 2007 ( ኖቨምበር 15፣ 2014) በተሳካ ሁኔታ አካሂዷል።
በዚህ ስብሰባ የህወሀት/ኢህአዴግ አገዛዝ በሀገራችን እና በህዝባችና ላይ እያካሄደ ያለውን ቀጣይ አሰቃቂና ሀላፊነት የጎደለው ተግባሮች በዝርዝር በመመመርመር ይህ የግፍ ስርአት ተወግዶ አንድነቷ በተረጋገጠ ኢትዮጴያ ስር የሁሉም ዜጎች ሙሉ ዴሞክራሲአዊ መብት ተከብሮ፣ የህግ የበላይነት ሰፍኖ ለመኖር የሚያስችል ህገመንግስታዊ ስርአት እውን ለማድረግ የተጀመረው ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማድረግ አማራጭ የሌለው ጉዞ እንደሆነ አጽንኦት ሰጥቷል። ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ፡
•ከሽንጎ የተለያዩ ቋሚ ኮሚቴወች የቀረበውን የስራ አፈጻጸም ሪፖርት መርምሮ ቀጣይ የሆነ አመርቂ ስራን ለመስራት የሚያስችለውን የያንዳንዱን ኮሚቴ የስራ እቅድ አጽድቋል፡
•ሸንጎው የሀገር ቤት ትግሉን ለማጠናከር የሚያካሂደውን የተለያዩ ግንኙነት እና እርምጃ አጠናክሮ እንዲቀጥል መመሪያ ስጥቷል።
•ባሁኑ ሰአት በሀገራችን ውስጥ የሚካሄደውን የመገናኛ ብዙሀን አፈናና በውስጥም በውጭም የሚታየውን የነጻ ሚዲያ ተግዳሮት ከተመለከተ በሗላ ይህ የሚዲያ አፈናና ሞኖፖሊ በህዝቡ ትግል ላይ ያለውን እንደምታ በማገናዘብ አማራጭ የዜና ማሰራጫ ሊጠናከርበትና ሊዳብር የሚችልበትን ጥናቶች መርምሮ በዚህ አኳያ በሽንጎው በኩል የአቅም ግንባታ ተግባሮች እና አስቸኳይ እርምጃወች እንዲወሰዱ መመሪያ ሰጥቷል፡:
•በዲፕሎማቲክ እንቅስቃሴውም እስካሁን የታዩትን አበረታች እንቅስቃሴወች ከመረመረ በሓላ በዚህ አኳያ የሚካሄደው ስራ ሁሉ በተጠናከረ መልክ በተሌያዩ የአለም ክፍሎች ተቀናጅቶ እንዲካሄድ የሚያሰችል መመሪያ ሰጥቷል።
•ለ2007 በመላ ሀገሪቱ ሊካሄድ የታቀደውን ብሄራዊ ምርጫ በተመለከተም በሰላማዊ መንገድ በሀገር ውስጥ መስዋእት በመክፈል በመታገል ላይ የሚገኙት ሁሉ የገጠሟቸውን ቀጣይ ተግዳሮቶች ከመረመረ በኋላ ይህ ምርጫ ነጻና ፍትሀዊ ለመሆን እንዲችልና ለህዝባችንም የነጻነት ትግል አስተዋጽኦው ከፍ እንዲል ቀደም ሲል ያወጣውን እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ የሀገር ቤቱን ትግል ለመደገፍና ለማጠናከር የተቀናጀና ጠንካራ እንቅስቃሴ እንዲደረግ ተጨማሪ መመሪያ ሰጥቷል፡፡
•ሽንጎው ቁልፍ በሆኑ የሀገሪቱ ጉዳዩች ላይ በጥናት ላይ የተመረኮዘ የፖሊሲ አማራጮችን ለማቅረብ አስቸኳይ እርምጃወችን እንዲወስድ ውሳኔ አስተላላፏል፡ አስፈላጊ ሆኖ በሚገኝበት ቦታ ሁሉ ቀደም ሲል አዘጋጅቶ ለህዝብ ይፋ ባደረገው አቅጣጫ (ሮድ ማፕ) ላይ አስፈላጊ የሆኑ ማሻሻያዎችን ለማካሄድ የሚያስችል መመሪያ ሰጥቷል፡:
•የሽንጎውን ራእይ ተግባራዊ ለማድረግ በቀጣይነት መካሄድ ያለበትን አጠቃላይ የአቅም ግንባታ ስራን በተመለከተ ሽንጎው የሚያካሂደውን ግምገማ ባስቸኳይ በማጠናቀቅ አስፈላጊ ሆነው የሚገኙ ማጠናከሪያዎችም ተግባራዊ እንዲደረጉ መመሪያ ሰጥቷል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

No comments:

Post a Comment

wanted officials