Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, November 29, 2014

በሃረር የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታዮች የሚያመልኩበት አንድ ቤተክርስቲያን እንዲፈርስ ተደረገ

በሃረር የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታዮች የሚያመልኩበት አንድ ቤተክርስቲያን እንዲፈርስ ተደረገ

ኀዳር ፲፱(አስራ ዘጠኝቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :- ወኪላችን እንደገለጸው የመንግስት ታጣቂዎች ወደ ሰማያዊ ብርሃን ቤተክርስቲያን በመሄድ ማፍረሳቸውን ለማወቅ የተቻለ ሲሆን አንድ ፓስተር እስከባለቤታቸውና ሌላ አገልጋይ ታስረዋል። የሃረር አብያተ ቤተከርስቲያናት ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ዮሴፍ አምደማርያም ታስረው ሲፈቱ ሌላው የቤተክርስቲያኑዋ ፓስተር አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ። ቤተክርስቲያኗ በአገር አቀፍ ደረጃ ተመዝግባ የምትንቀሳቀስ መሆኗ ታውቋል።
የክልሉ አፍራሽ ግብረሃይል አባላት 30 በሚሆኑ ታጣቂዎች ታጅበው በመምጣት ቤተክርስቲያኑዋን አፍረርሰዋል። በክልሉ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታዮች ከፍተኛ ችግር እየደረሰባቸው እንደሆነ ለኢሳት ተናግረዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials