በኢትዮጵያ የሚደረገውን መጪውን ምርጫ ተከትሎ በርካታ የሚዲያ አውታሮችን በመዝጋት አመቱን የጀመረው የኢህአዴግ አስተዳደር፤ አሁን ደግሞ ተቃዋሚዎችን በአገር ጠላትነት በመፈረጅ የሚስጥር ሰነድ አውጥቶ ለአባላቱ አሰራጭቷል። የትግራይ ህዝብ ግኑኝነት ቢሮ በትግርኛ ፅፎ ያሰራጨው ጽሁፍ “ዓመታዊ ትልሚ ንኡስ ውዳበ፣ ፕሮፖጋንዳ ክትትል ፀላእቲ” ( ዓመታዊ እቅድ ንኡስ ድርጅት ፣ ፕሮፖጋንዳ የጠላቶች ክትትል)፤ “ቢሮ ርክብ ህዝብን መንግስትን (የህዝብና መንግስት ግኑኝነት ቢሮ)”፤ 2007 ዓ/ ም
ሓምለ 2006 ዓ ም የሚል ነው።
በርእሱ ላይም ሆነ በውስጥ ገጾች እንደተገለጸው ከሆነ፤ ተቃዋሚዎችን “ፀላእቲ” ወይም ጠላት የሚል ስያሜ በመስጠት ተቃዋሚዎን ጠላት አድርገርው መፈረጃቸው በግልጽ ተቀምጧል። ይህ አይነቱናካሄድ ወይም ወገንን በጠላትነት የመፈረጅ አሰራር በህወሃት ዘንድ የተለመደ ቢሆንም፤ ይህ ለመጀመሪያ ግዜ በጽሁፍ የተሰራጨው ሰነዳቸው የተጋለጠበት ነው። ለዚህም የተቃዋሚ ድርጅቶች፣ ሌሎች የኢህአዴግ ድርጅቶች እና ምርጫ ቦርድ ይህም ጽሁፍ ሊገመግሙት ብሎም አቋም ወስደው ማስተካከል እንዳለባቸው እናምናለን።
ሰነዱን በሚገባ ከተከታተልነው፤ ይህ እቅድ ለተቃዋሚ ድርጅቶች የሚከታተልና የሚያጠፋ “የጠላቶች ክትትል” የሚል በመንግስት በጀት የሚንቀሳቀስና በትግራይ ክልል ህዝብ ግኑኝነት ቢሮ የሚመራ ነው።
ልዓመታያ ልዓብድስ ሎሚ እምኒ ይድብሪ እዩ ዋ…! ደቂ ዓደይ…! እዞም ሰባሲ ጨሪሶም ከይተፀለሉ ሓደ ምኽሪ ደኣ ንምከር።
ሰነዱን ወደ አማርኛ እና እንግሊዘኛ በመተርጎም ይተባበሩ። (ሰንደ እና ዜናውን በቅድሚያ ያሰራጨውን አምዶም ገብረስላሴ በዚህ አጋጣሚ ነናመሰግናለን።)
EMF
No comments:
Post a Comment