Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, November 11, 2014

የሚታሰሩ ኢትዮጵያውያን በምርመራው መጀመሪያ የኢሜልና የፌስ ቡክ የይለፍ ቃሎችን ይጠየቃሉ


ከማዕከላዊ አብሽቅ ቀልዶች አንዱ
በሽብር ስም ተከሰው ማዕከላዊ የሚታሰሩ ኢትዮጵያውያን በመረጃነት ከሚቀርቡባቸው ነገሮች ዋነኛዎቹ ኢሜልና ፌስ ቡክ ላይ ተለዋውጠዋቸዋል ተብለው ‹‹የሚተነተኑ›› መልዕክቶች ናቸው፡፡ በምርመራው መጀመሪያም የኢሜልና የፌስ ቡክ የይለፍ ቃሎችን ይጠየቃሉ፡፡ አልሰጥም ብሎ ‹‹ህግ›› ጠቅሶ የተከራከረ አሊያም ያንገራገረ ደግሞ በማዕከላዊ ቋንቋ ተነግሮት ይሰጣል፡፡
ነገሩ ማዕከላዊ ብቻ ሳይሆን በተራ ክስ አሊያም በዕለታዊ ጉዳይ በየ ቀበሌው የሚታሰሩ ኢትዮጵያውያንም ገና አንሰጥም ሳይሉም ቢሆን ጠረጴዛ ተደብድቦ ነው የፌስቡክና የኢሜል የይለፍ ቃሎቻቸውን የሚጠየቁት፡፡ ይህን እኔም በአንድ ወቅት ለመታዘብ ችያለሁ፡፡
እውነታው እንዲህ ሆኖ እያለ ግን ማዕከላዊ ውስጥ አብሽቅ ቀልድ ይቀለዳል፡፡ ይህ ከስር የምታዩት መጠይቅ በሽብርተኝነት ተከሰው ማዕከላዊ የሚገቡ ኢትዮጵያውያን የፌስቡክና የኢሜል የይለፍ ቁልፋቸውን ሰጥተው ኢሜልና ፌስቡካቸው ‹‹ካለ አስገዳጅና ተጽዕኖ›› ሲበረበር ምስክር ነን የሚሉ ደህንነቶች የሚሰጡት ቃል ነው፡፡
ይህ እንግዲህ አብሽቅ ከሆኑት የማዕከላዊ ቀልዶች መካከል አንዱ መሆኑ ነው፡፡ ሌላውን ቂሊንጦ አሊያም ቃሊቲ በማቅናት እነ ሀብታሙን፣ እየ የሸዋስን፣ ዞን ዘጠኞችን፣ እነ ውብሸትን፣ እስክንድርን፣ አንዱ ዓለምን...... መጠየቅ ይቻላል፡፡
Source FB Getachew Shiferaw

No comments:

Post a Comment

wanted officials