Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, November 22, 2014

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የወጣቶች ክንፍ ተመሠረተ፡

ዜና መድረክ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ የወጣቶች ክንፍ ተመሠረተ፡-



በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ /መድረክ/ አባል ድርጅቶች ውስጥ ተደራጅተው ሲታገሉ የቆዩ ወጣቶች በትናንትናው ዕለት ህዳር 7 ቀን 2007 ዓ ም ስድስት ኪሎ በሚገኘው የመድረክ ዋና ፅ/ቤት የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ አድርገው የአመራር አባለትን በመምረጥ የመድረክ የወጣቶች ክንፍ  መስርተዋል፡፡ በዚሁም መሠረት፡-
1ኛ፡- አቶ ደስታ ዲንቃ ሊቀመንበር፣
2ኛ፡- አቶ አብርሃም ሳልህ ም/ሊቀመንበር፣
3ኛ፡- አቶ አበበ ቃልሲዶ ፀሐፊ፣
4ኛ፡- አቶ ደሳለኝ መሳ የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ፣
5ኛ፡- አቶ ኪዳነ አመነ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ፣
6ኛ፡- አቶ ፍቅሩ ሙላቱ የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ፣
7ኛ፡- አቶ መሀመድ ጆዋር የፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊ እና
8ኛ፡- አቶ ተገኝ ወልዴ የውጭ ግንኙነት ጉዳይ ኃላፊ ሆነው ተመርጠዋል፡፡
ከዚህም ሌላ ለኦዲትና ቁጥጥር ኮሚቴ አባልነት፡-
1ኛ፡- አቶ እፍሬም ሁንዴ ሰብሳቢ
2ኛ፡- አቶ አዲሱ ቡላላ ፀሐፊ
3ኛ፡- አቶ ሰላሙ ቡላዶ አባል ሆነው ተመርጠዋል፡፡
በስብሰባው ከአራቱም የመድረክ አባል ድርጅቶች ከኦፍኮ፣ ከኢማዴ-ዴሕአፓ፣ ከአረናና ከሲአን  የወጣቶች ክንፍ አባላት የተወከሉ  33  ተወካዮች የተሳተፉ ሲሆን ስለሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታና በመድረክ ዓላማ ስር ከተደራጁት ወጣቶች ስለሚጠበቀው ኃላፊነትና የትግል ዝግጁነት በዶ/ር አየለ አሊቶ የመድረክ ም/ሊቀመንበርና የድርጅት ጉዳይ ሃለፊ አመካይነት ገለጻ ተደርጎ በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተካሄዷል፡፡ ወጣት ተሰብሳቢዎቹም የመድረክን ዓላማዎች ከግቡ ለማድረስ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በቆራጥነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት የመድረክን ስትራቴጂካዊ ዓላማዎች ከግቡ ለማድረስ የሚችል የወጣት ኃይል በመድረክ አባል ድርጅቶች በጥሩ ሁኔታ እየተሰባሰበ መሆኑ የሚያበረታታ ቢሆንም በቀጣይም ብዙ ሊሠራ እንደሚገባ በውይይቱ ወቅት የጋራ ግንዛቤ የተወሰደ መሆኑም ታውቋል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials