ባለፈው ወር በአፋር ክልል በአሚባራ አካባቢ ህዝብ ላይ የደረሰው የጎረፍ አደጋን ተከትሎ ከ30ሺ በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች ከአካባቢው መፈናቀላቸው ይታወሳል። ለእነዚህ ወገኖች ከተለያዩ የእርዳታ ድርጅቶች እና ከመንግስት የተላከው እርዳታ በመንግስት ኃላፊዎች ለሙስና መዳረጉን ምንጮቻችን ከቦታው ዘግበዋል።ባለፈው ሰኞ ከአዋሽ ፋንቲ አሌ ወረዳ ወደ መትሃራ በመንግሥት ኃላፊዎች ተዘርፎ ሊሸጥ የነበረና ብዛቱ በውል ያልታወቀ ብዙ ኩንታሎች የእርዳታ እህል በመኪና ተጭኖ ሲንቀሳቀስ ከሌሊቱ 6:00 ላይ በህዝብ ተቆማ በቁጥጥር ስር ውሏል።
እነዚህ ባለስልጣናት ለጊዜው የታሰሩ ሲሆን ስማቸው ከዚህ በታች በዝርዝር ይቀመጣል፦
1 – አቶ አደም መሀመድ የአዋሽ ፋንቲዓሌ ወረዳ ምክትል አስተዳደር
2 – አቶ አባህ አባ የግብርና የገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ
3 – አቶ ሙስጣፋ ሀሳን የአዋሽ ወረዳ የአብዴፓ ፓርቲ ቢሮ ኃላፊ፤
4 – ወ/ሮ ፋጡማ እብራሂም የንብረት ክፍል ቢሮ ኃላፊ ሲሆኑ እነዚህ ባለስልጣናት በጊዜው ለፖሊስ በሰጡት ቃል «የተያዝነው ጊዜ ባለፈበት እህልና እቃ ሲሆን ለመንግስትም ለመመለስ እየተንቀሳቀስን በነበረበት ሰአት ነው» ብለዋል ሲሉ ምንጮች ፓሊስን ጠቅሰው ዘግበዋል።

ይህን የህዝብ እርዳታ እንዲሸጡ ያስገደዳቸው የአፋር ክልል አፈጉባኤ የሆኑት አቶ መሀመድ አንበጣ ወደ አዋሽ በመሄድ ለወረዳው ካቢኔዎች ገንዘብ አምጡ ብለው 20,000 ብር ቢሰጧቸውም ጨምሩ ሰላሏቸው የህዝብ እርዳታ እንዲሸጡ መገደዳቸው አንድ ስሙ ሊገለፅ ያልፈለገ ሊንደብቅለት የመንግስት ሰራተኛ የላክለን መረጃ ያስረዳል።
No comments:
Post a Comment