Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, November 8, 2014

አቶ መለስ የሕይወታቸው ፍፃሜ የሆነባት የቤልጅየም ዋና ከተማ ብራስልስ ከመላው አውሮፓ በመጡ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ ተናጠች



አቶ መለስ የሕይወታቸው ፍፃሜ የሆነባት የቤልጅየም ዋና ከተማ ብራስልስ ከመላው አውሮፓ በመጡ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ ተናጠች
 ብራሰልስ በሁለት እግሯ ቆመች ማለት ይቻላል።ኢትዮጵያውያን ከኦስሎ፣ ከስቶኮሆልም፣ ከበርሊን፣ ከቦን፣ከሙኒክ፣ከፍራንክፈርት፣ከጄኔቫ፣ከለንደን፣ ከአምስተርዳም፣ ከያው ከብራሰልስ……ከመላው አውሮጳ የተገኙበት ደማቅ ሰልፍ ነበር።
ሰልፈኞቹ ከቀኑ 7፡00 እስከ 10፡30 ድረስ በአውሮጳ ህብረት ጽህፈት ቤት ፊትለፊት የተቃውሞ መርሀ-ግብራቸውን ካጠናቀቁና ደብዳቤያቸውን ለኮሚሽኑ ጽህፈት ቤት ካስገቡ በሁዋላ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞችን ምስል አንግበው አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀዩን ሰንደቅ እያውለበለቡ እና “ኢትዮጵያ ሀገሬን” እየዘመሩ ብራሰልስ ወደሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሰልፍ ተመሙ።
አካባቢው የኤምባሲዎች አካባቢ ከመሆኑ አኳያ የሌሎች ሀገራት ባንዲራዎች በየኤምባሲዎቹ ቅጥር ግቢ ይውለበለባል። የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ግን አይታይም። እታች ወርዶ በመስቀያው ብረት ስር እንደ ገመድ ተቋጥሮ እንዲቀመጥ ተደርጓል። ይህ ለምን እንደተደረገ ከግምት በስተቀር እስካሁን በግልጽ የታወቀ ነገር የለም።አንዳንድ ሰልፈኞች፦”እንደ ዲሲው ከሚያወርዱብን አስቀድመን ራሳችን እናውርደው ብለው ይሆናል” እያሉ ሲናገሩ ሰምቻለሁ። ብሎአል  ጋዜጠኛ ደረጀ ሀብተወልድ ።

አትዮጵያኑ የ አውሮፓ ህብረት ዋና ጽ ሕፈት ቤ ት ፊትለፊት በተደ ረገው በዚሁ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ የታሰሩት ውድ ኢትዮጵያውያን ን በሙሉ ስም በመጥራት መንግሥታቱ አንድያስፈቷቸው ጠይቀዋል ።
የብራሰልስ ከተማ መንገድም ለጊዜው ተዘግቶ ታይቷል ።


Ethiopian protesters shut down busy street in Brussels



No comments:

Post a Comment

wanted officials