Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, November 18, 2014

መንግስት የ9ኙን ፓርቲዎች የአደባባይ ስብሰባ መከልከሉ ትግሉን እንደማያቆመው ፓርቲዎቹ ገለጹ

መንግስት የ9ኙን ፓርቲዎች የአደባባይ ስብሰባ መከልከሉ ትግሉን እንደማያቆመው ፓርቲዎቹ ገለጹ

ኀዳር (ስምንትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-በሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪነት 9 የፖለቲካ ድርጅቶች በጋራ የጠሩት የአደባባይ ስብሰባ በገዢው ፓርቲ የጸጥታ ሃይሎች እንዲበተን ከተደረገ በሁዋላ ድርጅቶቹ ባወጡት መግለጫ ” መንግሥት ከገባበት ከፍተኛ የፍርኃት ስሜት ለመውጣት ያስቀመጠው የሴራ
መፍትሄ  መስዋዕትነቱን ይጨምር እንደሆን እንጂ፣ ትግሉን አያቆመውም” ብለዋል። ፓርቲዎቹ ለአንድ ወር ባወጡት የስራ መርሃ ግብር መሰረት ከአራት ኪሎ እና አካባቢው ህዝብ ጋር በአደባባይ በቤልኤር ሜዳ ለመገናኘትና በምርጫ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት ቢያቅድም ፖሊስ ስብሰባው እንዲካሄድ መፈቀዱን
አላውቅም በማለት በትኖታል። ፓርቲዎቹ ባወጡት መግለጫ በፖለቲካ ስብሰባ ስርአት አዋጅ ቁጥር 3/1983 የሚጠየቀውን አሟልተው ለከንቲባ ጽ/ቤት የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ደብዳቤ ቢያስገቡም ፣ ከጽ/ቤቱ የተሰጠው መልስ ግልጽ አለመሆኑን፣ በአዋጅ ከተመጠው ጋር የሚቃረን መሆኑንና
ለስብሰባው እውቅና ለመንፈግ የቀረበው ግልጽ ሆኖ አልቀረበም በሚል የመልስ ደብዳቤ መጻፋቸውን ገልጸዋል። የመስተዳድሩ ጽ/ቤት መልስ ከተጻፈለት በሁዋላ ምንም አይነት ደብዳቤ ባለመጻፉ ዝግጅቱን በተባለው እለት ለማካሄድ በስፍራው መገኘታቸውን ገልጸው ይሁን እንጅ፣ መንግስት በህገ መንግስቱ የተቀመጡትን መብቶች በመጣስ ስብሰባው እንዳይካሄድ ማድረጉን ገልጸዋል።
አመራሩ ሂደቱን ከትግሉ ዓላማና መርህ ፣ለዓላማው ማስፈጸሚያ በተከታታይና በቀጣይነት በታቀደው ሰላማዊ ትግል ላይ ከሚያስከትለው አሉታዊ ተጽዕኖ፣ ለእንዲህ ዓይነቱ ሴራ ከተደረገው ዝግጅትና በፖሊስ በኩል ከታየው የ‹‹ጭንቅ›› ስሜትና ተደጋጋሚ ውትወታ ካለበት ኃላፊነት ጋር በማገናዘብ  የዕለቱ ፕሮግራም በሰላም እንዲጠናቀቅ የማረጋጋት ተግባር በማከናወን ህዝቡን በሠላም እንዲሰናበት መደረጉን ፓርቲዎቹ ገልጸዋል።
የዕለቱ ውሎ ገዢው ፓርቲ የደረሰበትን  የፍርኃት እርከን የሚመለክትና ደፍሮ ባይናገረውም በተግባር በሠላማዊ ህዝባዊ ንቅናቄዎች የቱን ያህል እንደሚሸበር በተግባር ያረጋገጠበት ነው የሚለው የፓርቲዎች መግለጫ፣ በስብሰባው ላይ የተገኙ ኢትዮጵያዊያን ያሳዩት ቆራጥነትና ለመብታቸው ለመቆም ያላቸው ጽናትና የቱንም ዋጋ ለመክፈል ያላቸው ዝግጁነት ለቀጣዩ ትግል ከፍተኛ ሥንቅ እንደሚሆን ገልጸዋል።
“በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ  አገራችንን ከወረደችበት አዘቅት እኛም ከሚደርስብን ጭቆናና ሥቃይ ለመውጣትና የዜግነት ክብራችን ለማስመለስ በሚደረገው ቀጣይና ተከታታይ ሠላማዊ ትግል ለምናቀርበው ጥሪ አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ “የሚሉት 9 ፓርቲዎች፣ ትብብሩን ያልተቀላቀሉ ፓርቲዎች፣ ወደ ጋራ መድረኩ በመምጣት እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials