Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, November 11, 2014

ፌስቡክ፤ መረጃዎችን አሳልፌ እንድሰጣቸው የሚጠይቁኝ መንግስታት በዝተዋል አለ






ፌስቡክ ከተለያዩ የአለማችን አገራት መንግስታት የተጠቃሚዎቹን የግል መረጃዎች አሳልፎ እንዲሰጣቸው የሚያቀርቡለት ጥያቄዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን አስታወቀ፡፡


ታዋቂው የማህበራዊ ድረገጽ ፌስቡክ ከተለያዩ የአለማችን አገራት መንግስታት የተጠቃሚዎቹን የግል መረጃዎች አሳልፎ እንዲሰጣቸው የሚያቀርቡለት ጥያቄዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን አስታወቀ፡፡ከተለያዩ የአለም አገራት መንግስታት የሚቀርቡለት ተመሳሳይ ጥያቄዎች ባለፉት ስድስት ወራት በ25 በመቶ እንደጨመ በድረገጹ ላይ የገለጸው ፌስቡክ፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ 34 ሺህ 946 የመረጃ ጥያቄዎች እንደቀረቡለት አስታውቋል፡፡
ድረገጹ እንዳለው፤ የተለያዩ አገራት መንግስታት በፌስቡክ ተጠቃሚዎች ላይ በተለያዩ ምክንያቶች ክትትልና ምርመራ ለማድረግ የሚያግዛቸውን መረጃዎች ለማግኘት ጥያቄ ማቅረባቸውን ቀጥለዋል፡፡መንግስታት የሚያቀርቡትን መሰል ጥያቄዎች በመቃወም በተደጋጋሚ በአሜሪካ ለሚገኝ አንድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቤቱታ እያቀረበ እንደሚገኝ ያስታወቀው ፌስቡክ፣ ፍርድ ቤቱ የአሜሪካ መንግስት በህገወጥ መንገድ ያገኛቸውን የተጠቃሚዎቹነረ መረጃዎች እንዲያስመልስለት አቤት እያለ መሆኑንም ገልጿል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ታዋቂው ድረገጽ ጎግልም፣ የተጠቃሚዎቹን መረጃዎች አሳልፈው እንዲሰጡት በተለያዩ አገራት መንግስታት የሚቀርቡለት ጥያቄዎች ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በ15 በመቶ መጨመራቸውን ባለፈው ወር ማስታወቁን ሮይተርስ አስታውሷል፡፡
መንግስታት ለወንጀል ምርመራ የሚያቀርቡለት የመረጃ ጥያቄዎች ባለፉት አምስት አመታት በ150 በመቶ እንደጨመረ ነው ጎግል ያስታወቀው፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials