ህወሀት የትግራይ ክልልን የግል ሜዳው በማድረግ ስለሚቆጥር ክልሉ ከፓርቲው የተለየ ባንዲራ እንዳይኖረው እስከማድረግ መድረሱ የሚታወቅ ነው፡፡
ከትግራይ ክልል ውጪ ህወሀት አልጋ ሆኖ የማያውቅ ቢሆንም የህትመት ውጤቶች በትግራይ ብርቅ ሆነው ህዝቡ ከህወሀት ውጪ እንዳይሰማ ፕሮፌሰር መስፍን ባንድ ወቅት እንዳሉት ከአንድ ፋብሪካ እንደ ወጣ ምርት አንድ አይነት አስተሳሰብ እንዲይዝ ህወሀት የቻለችውን አድርጋለች፡፡
በትግራይ ክልል ከህወሀት የተለየ አጀንዳ ይዞ መንቀሳቀስ የማይታሰብ ቢመስልም ስዬ ፣አስገደ ፣አስራት፣አብርሀ፣ተክሌ፣እንዲሁም አረናዎች በገዛ ሜዳው ሌላ ማልያ አጥልቀው ተጫውተዋል፡፡
በህወሀት ተጠፍጥፎ የተፈበረከው ደኢህዴን በበኩሉ የደቡብ ክልልን በተለይም ወላይታን የግል ሜዳው በማድረግ መቁጠር የጀመረው አ…ቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማዕረግን እንደጨበጡ ነበር፡፡
አንድነት ፓርቲ ሐይለማርያም ጠቅላይ ሚኒስትር እንደተሰኙ በወላይታ ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ ፈቃድ አግኝቶ መንቀሳቀስ ጀምሮ ነበር፡፡ስብሰባውን ለመከታተልም ወደስፍራው ካቀኑት ሰዎች ጋር የመጓዝ እድል አጋጥሞኝ ነበር፡፡
በወላይታ መንግስታዊ ሽብርተኝነት ጥርሱን አግጥጦ መገለጡን ለመታዘብ ብዙ መጠበቅ አላስፈለገንም ነበር፡፡
ሽብሮቹን በጥቂቱ
በፖሊስ መኪና ተጭኖ የመጣው የመኪና ጎማ አስተንፋሽ
ፓርቲው ላንድ ክሩዘር መኪና ተከራይቶና የቅስቀሳ ቁሳቁሶችን አስጭኖ ወላይታ ገብቷል፡፡በከተማው የተሻለ ጥበቃ አለው ወደተባለ በቀለ ሞላ ሆቴል አልጋ ተይዞ ገባን፡፡ማለዳ ለስብሰባው ህዝቡን ለመቀስቀስ ቀጠሮ ተይዞ ሁሉም ዕረፍት ለማድረግ ክፍሉ ገብቷል፡፡
ማለዳ 12፡30 አካባቢ ከአልጋዬ ተነስቼ ሆቴሉን ለመቃኘት ወጣሁ፡፡በሸራ የተሸፈነች የፖሊስ መኪና የእኛን መኪና ተጠግታ ለመቆም በዝግታ እየተጠጋች ተመለከትኩ ፣
የተሸፈነውን ሸራ አንድ ብስል ቀይ ወጣት ገልጦ ዘሎ በመውረድ መኪናችን ስር ተንበረከከ ምን እንደሚያደርግ ካለሁበት ቦታ ለመለየት በመቸገሬ በፈጣን እርምጃ ለመጠጋት ሞከርኩ እኔ ቦታው ላይ ከመድረሴ በፊት ግን ወጣቱ ወደ ፖሊስ መኪናው ዘሎ በመግባቱ መኪናዋ ተፈተለከች፡፡
ወጣቱ ሁለት መዶሻ ያልነካቸውን ምስማሮች በመኪናችን ጎማ ላይ ሰክቶ ነበር፡፡ይህንን ድርጊት የሆቴሉ ጥበቃ በቅርበት ቢመለከቱም ምንም ማድረግ አልቻሉም፡፡
አፈና
አቶ ማሞ የተባሉ በወላይታ የአንድነት አመራር የዩኒቨርስቲ ተማሪ የሆነ ልጃቸው ታፍኖ መወሰዱ ለቅስቀሳ እንደተሰማሩ ተነገራቸው፡፡አፋኞቹ ጭምብል ያጠለቁ ገንዘብ የሚፈልጉ ተራ ወንደበዴዎች አልነበሩም ፡፡አቶ ማሞ በቅርበት የሚያውቋቸው የቀበሌ አመራሮች እንጂ፡፡ልጁ የታፈነው አባቱ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንዲያቋርጡ ለማስገደድ ብቻ ነበር፡፡
ወኖና አቶ ማሞ ተደበደቡ
ዛሬ የሰማሁት ዜና ሌላኛው ወላይታ በመንስታዊ ሽብርተኝነት መዳፍ ስር እንደምትገኝ ማሳያ ነው፡፡
አቶ ማሞ በእድሜ የገፉ በሳል ፖለቲከኛ ናቸው፡፡ማንም ይምጣ ማን በኢትዮጵያ ሰላማዊ የሚሰኝ የስልጣን ሽግግር ሳይመለከቱ እግዜር እንዳይወስዳቸው የሚጸልዩ ናቸው፡፡
ጎልማሳው ወኖ ያልተነገረለት ያልተዘመረለት የለውጥ ሀዋርያ ነው፡፡ዛሬ ራሱን ስቶ እስኪወድቅ ድረስ መደብደቡ ተሰምቷል፡፡‹‹ሀይል የኢትዮጵያ ፖለቲካ መታወቂያ መሆኑ ማብቃት ይገባዋል››የሚለው ወኖ ድብደባ ሲያስተናግድ የአሁኑ የመጀመሪያው ባይሆንም ጉዳቱ ከፍተኛ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡
—-የኢትዮጵያ አምላክ ከእነርሱ ጋር እንዲሆን ጸሎቴ ነው —-

No comments:
Post a Comment