Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, March 16, 2015

ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ በብጣቂ ወረቀት ከዩኒቨርስቲ ተባረሩ እርሳቸው ግን <አሁን ገና ኢትዮጵያዊ ሆንኩ › እያሉ ነው


እርሳቸው ግን አሁን ገና ኢትዮጵያዊ ሆንኩ ፣ምከንያቱም ኢትዮጵያዊ መብቴ የሚረገጥ ማለት ነውና››እያሉ ነው
---
‹ዳኛቸው፣ ዩኒቨርስቲውን እንደ ደጀንና ገዥ መሬት ተጠቅሞ መድፍ ሲተኩስብን ቆይቷል›› ሲሉ የነበሩ ህወሓቶች አሁን አንጀታቸው ቅቤ ሳይጠጣ አይቀርም፡፡የፍልስፍና ምሁሩን ከዩኒቨርስቲው ማባረር ችለዋልና፡፡ስንብታቸውን አስመልክቶ ዳኛቸው ለአዲስ አድማስ እንደተናገሩት ‹‹ውሳኔው ፖለተካዊ መሆኑነን ማንም አይስተውም››፡፡
አደባባይ በመውጣት ሀሳባቸውን በመግለጽ ተለይተው የሚታወቁት ዳኛቸው በዩኒቨርስቲው ለሰባት ዓመታት አስተምረዋል፡፡ ዶክተሩ በአደባባይ በሚያደርጓቸው ተሳትፎዎች ደስተኛ ያልነበሩት ህወሓቶች ለዳኛቸው በሚቀርቧቸው ሰዎች አማካኝነት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ካልሆነም አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ሲወተውቷቸው ቆይተዋል፡፡
ከወራት በፊት በዩኒቨርስቲው የሚያቆያቸውን ኮንትራት ለመፈረም ሲንቀሳቀሱ ዶክመንታቸው ከዩኒቨርስቲው መዝገብ ክፍል ተፈልጎ መጥፋቱ ሰዎቹ ሊያባረሯቸው እንደወሰኑ ፍንጭ እንደሰጣቸው በወቅቱ መናገራቸው አይዘነጋም፡፡
በዩኒቨርስቲው ለሰባት ዓመታት ላስተማሩ መመህራን የሚሰጠው የእረፍት ጊዜ ተፈቅዶላቸው እረፍት ለመውጣት ሲጠባበቁ በብጣቂ ወረቀት መሰናበታቸው እንደተነገራቸው የሚገልጹት ዳኛቸው ‹‹አሁን ገና ኢትዮጵያዊ መሆኔን አወቅኩ ምክንያቱም መበቴ ተረገጠ››በለዋል፡፡
ዶክተር መረራ ጉዲና ትናንት ምሽት በተላለፈው የምርጫ ክርክር ወቅት‹‹ኢህአዴግ ምሁራንን አይወድም››በማለት መናገራቸውን የሚያስታውሱ የዳኛቸው ስንብት መንስኤ ምን እንደሆነ በደንብ ይገነዘቡታል፡፡
Like ·  · 

No comments:

Post a Comment

wanted officials