Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, March 4, 2015

የዓረና-መድረክ ኣባል በፖሊስ ድብደባ ደረሰባቸው


የዓረና-መድረክ ኣባል በፖሊስ ድብደባ ደረሰባቸው













ቐሺ ሕሉፍ ኸሕሳይ ይባላሉ። በምዕራባዊ ዞን ቓፍታ ሑመራ ወረዳ በረኸት ከተማ(ቀበሌ) ኑዋሪ የሆኑት የዓረና-መድረክ ኣባል ናቸው።

በፎተው እንደሚታዩት የዓረና-መድረክ ኣባል በመሆናቸው ብቻ ይህ ዘግናኝ ድብደባ ደርሶባቸው በከፍተኛ ጉዳት ላይ ይገኛሉ ።




በ17/ 2007ዓ/ም ማታ 1 ሰዓት ኣከባቢ የፖሊስ ድምብ ልብስ የለበሱ ሰዎች በድንጋይ ደጋግመው በመምታት ሞታል ብለው ሄደዋል

የታጠቁ ሰዎች ሰው እርዳታ እንዳያደርግ የተከላከሉ ሲሆን ባኣካባቢው ሰዎች ድጋፍ ህወቱ ሊተርፍ ችሏል::

ቐሺ ሕሉፍ ኻሕሳይ 2006 ዓ/ም በቀበሌው ህዝብ ፊት ቀርበው “..ይህ ሰውየ ዓረና ነው፣ በቤታቹ ቃጠሎ እንዳያደርስባቹ፣ እንዳይሰርቃቹ..” ወዘተ የመሳሰሉ የስም ማጥፋት ዘመቻና ማስፈራርያ ከሌሎች3 የዓረና ኣባላት ጋር ደርሶባቸው ነበር።

ኣቶ መዓሾ ኣስመላሽ የተባለ የቀበሌ ኣመራርም ሰበካ ጉባኤ(የቤተክርስትያን ሃላፊዎች) በመሰብሰብ “…ቐሺ ሕሉፍ በዓረናነት ስለተጠረጠረ እንዳይቀድስ ..” የሚል ትእዛዝ ባስተላለፈው መሰረት ከቅዳሴ ታገዱ።

ቐሺ ሕሉፍ የካድሬው እገዳ ተከትለው ወደ ቀበሌው ፖሊስ ኣቤቱታ በማሰማታቸው የቅስና ምስክር ወረቀታቸው እንድያመጡ በታዘዙት መሰረት ምስር ወረቀታቸው ለፖሊስ በማስረከብ ፍትህ እንዲያገኙ ጥረት ኣደረጉ።
ፖሊስም በተረዋ ምስክር ወረቀታቸው ለሁለት ሳምንት ይዞ ያለ ምንም መፍትሄ ኣቆየባቸው።
የምስክር ወረቀቱ ለማስመለስም ተጨማሪ ክስ ኣስፈለጋቸው። ፖሊስ በስንት ውጣ ውረድ ወረቀታቸው የመለሰላቸው ሲሆን ከዚህ በሗላም ስንት ዛቻ ደረሳቸው።

ዘግናኝ ድብደባ የተፈፀመባቸውም ከዚህ ሁሉ ውጣ ወረድና ማንገላታት በሗላ ነበር። ህግ ባለበት ሃገር የሰው ልጅ እንዲህ ተቀጥቅጦ ይጣላል እንዴ…?

በሉ ያገራችን ሰዎች ..! ታፍሩበት ትኮሩበት ዘንድ ይሄውላቹ የኛ ዲሞክራሲ፣ የኛ ፍትህ፣ የኛ ነፃነት።

ይህ ኣስቃቂ ተግባር ሁሉም ዜጋ ሊቃወመው ይገባል።

ነፃናታችን በእጃችን ነው..!

No comments:

Post a Comment

wanted officials