Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, March 20, 2015

ከመላ አውሮፓ የተጠራሩ ኢትዮጵያውያን የአለም ኣቀፍ መዲና ከተማ በምትባለው ጄኔቭ ደማቅ ሰልፍ አደረጉ







በ አውሮጳ የተለያዩ ሀጋራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና አውሮጳውያን ማርች ፳  በርካታ አለም አቀፍ መስሪያ ቤቶች መናገሻ በሆነችው ጄነቫ ታላቅ ሰልፍ አካሂደዋል።

በሰልፉ ላይ ወያኔ በ ነባሩ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የ ኢትዮጵያ ባንዲራ ላይ በወያኔ የተለጠፈውን  ሰማያዊ ክብ ወስጥ የገባ ኮከብ አርማው የ ሰይጣን ምልክት ሰለሆነ እርኩስ መንፈስ ነው በማለት በማቃጠል ረክተዋል።





የኢትዮጵያን ወቅታዊ ፖለቲካ እና የሰብዓዊ መብቶች አፈና  ለዓለም ዓቀፍ ተቋማት ለማሳወቅ
በሱዳን በ ኬንያ የመን እና ሌላው አለም የሚገኙ ስደተኞች ጥበቃ እንዲያገኙ እና የሚገጥማቸውን ችግር  በተመለከተ
 ጀኔቫ ለሚገኘው የስደተኞች ኮሚሽን ለማሳውቅ ቀይ መስቀል እስረኞችን እንዲጎበኝ ለማሳሳብ በሚሉ ዋና ሶስት አጀንዳዎችን ለማንጸባረቅ የተጠራው አውሮጳ አቀፍ ሰልፍ  ዩናይትድ ኔሽን የስደተኞችከፍተኛ ኮሚሽነር ደብዳቤ የተሰጠ ሲሆኑ ነጭቹ  አውሮፓውያን ሳይቀሩ ተሰላፊዎቹ ያነገቧቸውን የ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ፤ርዕዮት አለሙ ፤እስክንደር ነጋ እና ሌሎች የሰቃይ ሰለባ ኢትዮጵያውያን  ፎቶዎች  እያዩ መደመማቸው  ተዘግቧል።


በሕወሃት ኢሕአዴግ ዘረኛ አገዛዝ በግፍ ወሕኒ ለተወረወሩ ወገኖቻችን በስዊዝ የመንግስታቱ ጽ/ቤት ደጃፍ ድምጻቸውን ለማሰማት የወጡ ኢትዮጵያውያን በርካታ ሲሆኑ በኢትዮጵያ ባንድራ ታጅበው የተለያዩ መፈክሮችን ለአለም ኣቀፉ ማህበረሰብ አሰምተዋል።ኢትዮጵያውያኑ ከ ስዊዘርላንድ ከፈረንሳይ ከ ጀርመን ከኔዘርላንድስ ከ እንግሊዝ እና ሌሎችም ሃገራት ተውጣጥተው በተለያዩ ትራንስፖርት ጄኔቭ በማምራት   ኢትዮጵያዊን ላንቺ ነው ኢትዮጵያ የሚለውን መዝሙር  እንዲሁም ኢትዮጵያ ሃገራችን የሚለው አነቃቂ ዜማ ተቀባብለው ጨፍረውበታል።
Ethiopians  rally infront of UNHCR,  Photo Abraham
ከመፈክሮቹ ውስጥም በ አማርኛ ቋንቋ ድምጽ በታሪካች ላይ መደራደር አይቻልም፤ እነ አቡበከር አሸባሪዎች አይደሉም፥ አሸባሪው ወያኔ ነው፥ሞት ለወያኔ ፤ ዘረንነት ይብቃ ፤ትውልድ ማምከን ይብቃ የሚሉት   በእንግሊዘኛ እና ፈረንሳይኛ ቋንቋ የወያኔ አምባገንን 24 አመት ይበቃል,Free political prisoners, respect human rights የሚል ሲነበብ ቆይቷል።

Ethiopians held Europe wide demonstration in Geneve
You can watch the burning ceremony of the star taking out from the Ethiopian flag at
https://www.youtube.com/watch?v=vtuTiH44pbU















No comments:

Post a Comment

wanted officials